አባዲ ዘሙ እንደ ሁግ ለጥልጥ ሃብታም ናቸው። እፊታቸው እሳቸው ሱቅ አጠገብ እይፈዘዝኩ ብዙ ጊዜ አይቻቻቸዋለሁ። ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ማለቴ ነው።

አባዲ ዘሙ ከስለው፣ ጠውልገው ከሰርጥ ውስጥ ወጡ ሲባል እውነት ለመናገር ያወኳቸው በመነጥራቸውና በሌለው እጃቸው ነበር። እኚያ በካባቢው ላለነው ሁሉ ሽቱ የሚቀቡትና ሽክ የሚሉት ሃብታም ምን አቅብጧቸው ዋሻ ለዋሻ እንደሄዱ ለማውቅ ጉጉቴ ትልቅ ነው። ቢቻል ቢቻል የፍርድ ሂደቱ ወደ ኑዛዜ ተቀይሮ ብንሰማው!!

ቦሌ ኤርፖርት አራት ሱቆች አለዎት። እያንዳንዳቸው 266 ሺህ ብር የሚከራዩ ናቸው። ሱቆቹ ዶላር ማጫወቻ እንደሆኑ እርስዎም ወዳጆችዎም ያውቃሉ። ስራው በጥቁር በመሆኑና ሰንሰለት ስላለው ምንዛሬ ስናጣ ጎራ ብለን ደጅ የጠናንበት ጊዜ ትንሽ አይደለም። ከፍለን ተጠቅመናል። ከኤርፖርትም እቃ ቀረጥ ሳይከፈልበት  … እሱ ይቅር።

ቦሌ መሓሉ ላይ አራት ዘመናዊ ቤቶች አለዎት። ቤቶቹ ሁሉም የሚከራዩት በዶላር ነው። ይህ እንግዴ እኔ ብቻ የማውቀው እንዲሁ እንደቀልድ የነገሩኝ “ንብረትዎ” ነው። ልጨመር

አንበሳ ባንክ፣ ወጋገን ባንክ፣ የቢራ ፋብሪካዎችና ኢንሹራንስ ድርጅቶች ውስጥ አክሲዮን አለዎት። በሌሎች ስምም ይኖርዎታል። በምንም ይሁን በምን፣ ምንጩ የምናውቀው ቢሆንም አርፈው መብላት እንዴት ተሳነዎ?

አቶ አባዲ ዘሙ የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ቁልፍ ሰው እንደነበሩ አይክዱም። ይህንኑ ተጠቅመው ያሻዎት ቢሮዎች እየገቡ የፈለጉትን ሰብስበዋል። መመሪያ እየሰጡና እያሰጡ ሃብት ቆልለዋል። አገር ቤት ብቻ ሳይሆን በድርጅትዎ በኩል በውጭ አገርም የውክልና ሃብት እንደሚያንቀሳቅሱ ይታወቃል። በዕድሜዎም ቢሆን ነጉደዋል። ሃብትዎ፣ ጤናዎና እድሜዎን እያወቁ ምን ፈለገው ወደ ዋሻ እንዳመሩ እኔና ጓደኞቼ ሊገባን አልቻለም።

እርስዎና ሙሉ ሽማግሌዎቹ የህወሃት አባላት ስትያዙ ወዲያውኑ በየሱቃሽን ማውራት የጀመርነው ይህ እኔ የጻፍኩትን ነው። በተለይ እኛ አንድ አካባቢ የምንሰራ ሰዎች እርስዎና ሃብትዎ ዙሪያ በስፋት አምተንዎታል። በስፋት በየቀኑ ሱቆችዎን እያየን በመገረም ደግመን ደጋገመን ተከራከረናል። ግን በመጨረሻ ያልነው ” አይ ሲጋርድ፣ የጋረደው ሚሊዮነር” ብቻ ነው።  ለምን ግን እርስዎን ብቻ ሳይሆን በርካቶችን ጋረዳቹህ? ከሰላም ከተማ ወደ ተመሰረታችሁበት ጉድባ ምን ነዳቹህ?

በመጨረሻም ከዋሻ ውስጥ እንደወጡ እግርዎ ታሞ ሲያሽዎት የነበረውን የመከላከያ ሰራዊት እንዳይዘነጉት አደራ እልዎታለሁ። ሰላምተኛዎ ነኝ። ሲረጋጋ እጠይቅዎታለሁ።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *