በትግራይ ክልል የተካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ በጁንታው አባላት ጉዳት ደርሶበት ከጥቅም ውጭ ሆኖ የነበረው የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና ተደርጎለት በዛሬው እለት አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገለጸ።
በትግራይ ክልል በጁንታው አማካኝነት ጉዳት የደረሰባቸውን የመሰረተ ልማት አገልግሎቶች በፍጥነት ጠግኖ ወደ ስራ ለማስገባት ከፍተኛ ስራ በፌዴራል መንግስት እየተከናወነ መሆኑንም የትግራይ ብልጽግና ከፍተኛ አመራር ዶክተር አብርሃም በላይ ለኢትዮፕያ ፕሬስ ድርጅት አስታውቀዋል።
እንደ ዶክተር አብረሃም ገለጻ፤ የፌዴራል መንግስት ባደረገው ከፍተኛ ጥረት በጁንታው አማካኝነት ጉዳት ደርሶበት የነበረው የኤሌክትሪክ መስመር በመጠገኑ በዛሬው እለ የአደዋ ከተማ የመብራት አገልገሎት አግኝታለች።
አብዛኞቹ የትግራይ ኣካባቢዎች የመብራት አገልግሎት አግኝተዋል ያሉት ዶ/ር አብረሃም፤ የተቀሩት ማለትም አክሱም፣ሽሬና ሑመራ በአጭር ግዜ የመብራት አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በሀገር መከላከያ ሰራዊት በተወሰደበት የህግ ማስከበር ዘመቻ ጁንታው በሽንፈት ከከተሞች ለቆ ሲወጣ በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል፤ በዋናነትም የከፍተኛ የአሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን በጣጥሷል፤ የኢትዮ ቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን አቋርጧል፤ የአክሱም አውሮፕላን ማረፊያን አውድሟል፤ በተለያዩ ከተሞች መንገዶችን ቆፋፍሯል፤ ድልድይ አፍርሷል፤ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አውድሟል፤ ዘርፏል፤ የህክምና አምቡላንሶችን ዘርፎ ወስዷል።
በተጨማሪም የህግ ታራሚዎችን በመፍታት በመቀሌ ከተማ ለቆ ለወንጀል አሰማርቷቸዋል።
SOURCE – EPA

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   “አማራ ከትግራይ ክልል ውጣ”አሜሪካ ”ግፍ” ታውቃለች? ጋምቤላ፣ ማይካድራ፣ ራያ፣ በደኖ፣ሆራ፣ ዋተር…ምን ተደርጓል?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *