አዲስ አበባ በሚገኘው አይሲቲ ፓርክ ውስጥ ከፍተኛ መረጃ የመሸከም አቅም ያላቸው የመረጃ ማዕከላት (ዳታ ሴንተር) ሊገነቡ ነው፡፡
ዊንጉ አፍሪካ በተሰኘ ድርጅት የሚገነቡት እነዚህ የመረጃ ማዕከላት ግንባታ ፕሮጀክት በፓን አፍሪካ ፕሮጀክት ስር የታቀፈው ዕቅድ አንዱ አካል ነው ተብሏል።
ግንበታቸውም የሚከናወነው አዲስ አበባ በሚገኘው አይ ሲ ቲ ፓርክ ውስጥ 15 ሺህ ስኩዌር ሜትር ስፋት ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ድርጅቱ በቀጣይ ተመሳሳይና ሁለተኛ ፕሮጀክቱን ከአዳማ ከተማ በ96 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ ለመገንባት ዕቅድ እንዳለውም ተነግሯል፡፡
የእነዚህ መረጃ ማዕከላት ወይም ዳታ ሴንተር ግንባታ በሀገሪቱ ለሚገኙ ለይዘት አቅራቢዎች የግንኙነት መረብ፣ የክላውድና ለፋይናንስ ተቋማት እና ድርጅቶች ደህንነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ የሰርቨር አገልግሎት ለመስጠት እንደሚስችል ድርጅቱ ገልጿል፡፡
እንደ ድርጅቱ ተባባሪ መስራችና ሀላፊ አንቶኒ ቮስካሪደስ ገለጻ ከሆነ ይህን የመረጃ ማዕከል በኢትዮጵያ ለመገንባት ፍላጎት ያሳደረበት ዋና ምክንያት በኢትዮጵያ የመረጃ ማዕከል አቅርቦት ዝቅተኛ መሆኑና የሀገሪቱ ሲስተሙን ለማግኘት ያላት ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ መሆኑም በመረጃው ላይ ተመላክቷል፡፡
ይህን የመረጃ ማዕከል በኢትዮጵያ መገንባታችን አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ብቻ ሳይሆን በዘርፉ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ራዕይና ትልም ላላቸው ባለተሰጥኦ ኢትዮጵያውያን ወጣት ስራ ፈጣሪዎች የተረጋጋ ስርዓት ለመዘርጋት ያስችላል።
እንዲሁም ሀገሪቱ ለምታካሂደው ሁሉን አቀፍ የልማት እንቅስቃሴ እና በማህበራዊ አገልግሎት ፕሮግራሞች ላይ ጭምር ለመሳተፍ ያለው ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ሲሉ የድርጅቱ ሀላፊ ተናግረዋል፡፡
ድርጅቱ ቀደም ሲል በጅቡቲ ጂቡቲ ከተማ እና በኬኒያ ናይሮቢ ከተማ በተመሳሳይ ስራ ላይ ተሰማርቶ ስራዎችን የሰራ ሲሆን በቀጣይ በዛምቢያ፣ ታንዛንያ፣ ሞዛምቢክና ዩጋንዳ የመረጃ ማዕከል ለመገንባት ዕቅድ እንዳለውም አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ በኢትዮጵያ ራክሲዮ፣ ሬድ ፎክስ የኔትዎርክ ሶሉዩሽን እና ስኩቲኤክስ የተባሉ ሶስት ተጨማሪ ካምፓኒዎችን በዛው በአይሲቲ ፓርክ ውስጥ መገንባት የሚያስችለውን የቦታ ርክክብ ማድረጉንም ጨምሮ መግለጹን ያስነበበው ዳታ ሴንተር ዳይናሚክስ የተባለ ድረ-ገጽ ነው፡
ኢፕድ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   እኛ የምንመርጠው አባትና አያቶቻችን የመረጡትን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *