“Our true nationality is mankind.”H.G.

ህገወጥ ሰው አዘዋዋሪ ወንጀለኞችን ለመመርመርና ማስቀጣት የሚያስችል አዲስ የሰነድ ርክክብ ተደረገ

NtJDO

በሰዎች የመነገድና ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎችን ለመመርመርና ለማስቀጣት የሚያስችል ወጥ የአሰራር ስርአት ተዘርግቶ የሰነድ ርክክብ ተካሄደ
ጥር 14/2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሚፈፀሙ በሰዎች የመነገድና ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎችን ለመመርመርና ለማስቀጣት የተዘጋጀ የአሰራር ስርአት ሰነድ ተዘጋጅቶ በሲቪ ፖል የምስራቅ አፍሪካ አስተባባሪ በሆኑት ሚስተር ማርኮን ቢፎ አስረካቢነትና በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ፍቃዱ ፀጋ አና በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ተረካቢነት በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ ርክክብ ተካሂዷል፡፡
ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ፍቃዱ ፀጋ በርክክቡ ወቅት ባደረጉት ንግግር እንዳሉት በአሁኑ ወቅት የአለም አገራትን እየተፈታተኑ ከሚገኙ ወንጀሎች ዉስጥ ዋነኛዉ በሰዎች መነገድና ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል መሆኑን አንስተዉ ይህንን ወንጀል ለመመርመርና ለማስቀጣት የሚያስችል ወጥ አሰራር መዘርጋቱ በተለይም ለመርማሪ ፖሊሶችና ለዐቃቢያነ ህግ ወንጀሉን ለመመርመር ብሎም በክስ ሂደት ዉስጥ እጅግ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለዉ በመጠቆም ስራዉን ወጥ እና የተቀላጠፈ ለማድረግም የአሰራር ስርአቱ መዘርጋቱ ፋይዳዉ የጎላ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡
አያይዘዉም በነዚህ ወንጀሎች የምርመራና የክስ ሂደት የሚሳተፉ ባለሙያዎች ይህንን የአሰራር ስርአት የእለት ተእለት መሳሪያቸዉ አድርገዉ እንዲተገብሩት በማሳሰብ ሰነዱን በመቅረፅ ሂደቱ ለተሳተፉና ድጋፍ ላደረጉ አጋር ድርጅቶች ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡
ሰነዱን በማዘጋጀት የተሳተፉትና በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ እንዳልካቸዉ ወርቁ በበኩላቸዉ በሰዎች መነገድ እና ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎች ምርመራ እና ክስ አቀራረብ ከቦታ ቦታ እና ከባለሙያ ባለሙያ የአሰራር ልዩነት እንደሚስተዋል ጠቁመዉ በዋናነት የአሰራር ስርአቱ ወጥ የሆነና ተመሳሳይ አሰራር ለመዘርጋት ታስቦ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፣ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ከሲቪ ፖል(በኢትዮጵያ የተሻለ የፍልሰት አመራር መርሐ ግብር)፣ከጂ.አይ.ዜድ፣ከዩ.ኤን..ዲሲ፣ከዩ.ኤን እንዲሁም ከጀርመን ኤምባሲ የመጡ የየተቋማቱ ተወካዮች ንግግር አድርገዋል፡፡
ቀጥሎም የአሰራር ስርአቱን አጠቃላይ ይዘት በተመለከተ የሲቪፓል አማካሪ በሆኑትና በሰነዱ አዘጋጅ በአቶ ይበልጣል ዋለልኝ አጭር ገለፃ ቀርቦ በመድረኩ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት አሰተያየታቸዉን ሰጥተዋል፣አስተያየት ሰጭዎቹ እንደገለፁትም የአሰራር ስርአቱ መዘርጋቱ ለስራቸዉ መልካም መደላድል እንደሚፈጥርላቸዉ በመግለፅ ለተግባራዊነቱም ትኩረት ሰጥተዉና በስራቸዉ ዉስጥ አካተዉ እንደሚሰተገብሩት ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር በመድረኩ የተሳተፉ ባለ ድርሻ አካላት በሰጡት አስተያየት በሁሉም ዘርፍ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ያሳየ መሆኑን ጠቁመዉ በቀጣይም ስልጠናዎች እንደሚሰጡ በመግለፅ ሰነዱን ያዘጋጁትን እንዲሁም እንዲዘጋጅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉትን አካላት አመስግነዉ መድረኩ ተጠናቋል፡፡
የአሰራር ስርአቱን በማዘጋጀት ሂደቱን በማስተባበር በዋናነት በኢትዮጵያ የተሻለ የፍልሰት አመራር መርሐ ግብር(ቢ.ኤም ኤም ) ሚናዉን የተወጣ ሲሆን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፣የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣የአዲስአበባ ፖሊስ፣የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፣ኢሚግሬሽን፣ሰራተኛና ማህበራዊ ሚኒስቴርና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላትም በዝግጅት ሂደቱ ተሳታፊ እንደነበሩ ለማዎቅ ተችሏል፡፡
ጠቅላይ አቃቤ ህግ የፌስ ቡክ ገጽ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   በሃሰተኛ ሰነድ ሾፌር ሆኖ የጫነውን ከ6 ሚሊዮን በር በላይ የምያወጣ ቡና የዘረፈው ዕምነት አጉዳይ ተፈረደበት
0Shares
0