በጎረቤት አገር ባሉ ባንኮች አማካይነት የብር ሂሳብ ዘውውር እንደሚደረግ ታወቆ የማስተካከያ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተሰማ። እርምጃው እየናረ ያለውን የውጭ ምንዛሬ ገበያ ያወርደዋል ተብሎ ይጠበቃል። በውጭ አገር ብር በመላክ ስራ የተሰማሩ አብዛኞቹ ” ለጊዜው አንልክም” የሚል መልስ እየሰጡ ነው።

ለዛጎል መረጃ ያቀበሉ እንዳሉት ወጋገን ባንክ ቀደም ሲል በቶጎ ጫሌ፣ ከዛም በሶማሌ ላንድ ሃርጌሳ ቅርንጫፍ ለመክፈት ቀዳሚ ነበር። በወቅቱ  የጫት ኤክስፖርት ጨምሮ ባንኩ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ይሰበስብ ነበር። በአየር በአየር ገንዘብ ሲላክ በጎረቤት አገር ባሉ ባንኮች ከተከፈተ ሂሳብ የብር ማዛወሩ ስራ እንደሚሰራ ሲታጣራ ይህን ባንክ ያካት አያካት የወሬው ባለቤት ያሉት ነበር የለም።

በውጭ አገራት ያሉ ገንዘብ ላኪ ዜጎች ለቤተሰቦቻቸው ሲልኩ፣ የውጭ ምንዛሬውን በመቀበል ብሩን አገር ቤት ላሉ ቤተሰቦቻቸው ወይም ለሚፈልጉት ሰው እንዲደርስ የሚደረገው በአብዛኛው በሶማሌ ላንድና ጅቡቲ ባሉ ባንኮች ከተከፈተ አካውንት ነው። የብሩን ዝውውር በማጥናት ምርመራ ያካሄደው መንግስት ባንኮቹ ጓዛቸውን ጠቅልለው እንዲወጡ መመሪያ መስጠቱ ታውቋል። መቼ እንደሚወጡ ለጊዜው የወሬው ምንጭ አልገለጹም።

ብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ዝውውር ገድብን አስመልክቶ ያወጣውን መመሪያ ጠቅሶ ዋዜማ ሬዲዮ የሚከተለውን ዘግቧል።ዋዜማ ራዲዮ– የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከታህሳስ 30 ቀን 2013 አ.ም ጀምሮ በሁሉም ባንኮች ተግባራዊ እንዲሆን ያዘዘው የገንዘብ ማዘዋወር ገደብ ወደ ስራ ከገባ በሁዋላ በጥቁር ገበያ ያለው የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ቅናሽን አሳይቷል። ብሄራዊ ባንኩ በአንድ ባንክ በሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማዘዋወርን አይቻልም ሲል ነው ለባንኮች መመሪያ ያስተላለፈው። ይህ መመሪያ ለሰራተኞች የሚከፈል ደሞዝንና መሰል የሂሳብ ዝውውሮችን አይመለከትም። የመመሪያው አላማም የህገ ወጥ ሀዋላ አዘዋዋሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ጫናን ማሳረፍ እንደሆነ በሀገር ውስጥ የዜና አውታሮች መዘገቡ የሚታወስ ነው።

አሰራሩ ተግባራዊ ከሆነ ከታህሳስ 30 2013 በሁዋላ ከሁለት አመት ከግማሽ በሁዋላ ለመጀመርያ ጊዜ የጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሬ መገበያያ ዋጋ ከእለት እለት ቅናሽን አሳይቷል። መደበኛ ባልሆነው የውጭ ምንዛሬ ገበያ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ54 ብር እየተገዛ በ54 ብር ከ50 ሳንቲም በላይ በሆነ ዋጋ እስከመሸጥ ደርሶ ነበር ። በዚህም ሳቢያ በባንኮችና እና በጥቁር ገበያ የአንድ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ልዩነት ከ16 ብር በላይ ሆኖ ቆይቷል።ይህም ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከበፊቱም በባሰ ሁኔታ የዋጋ ግሽበትን ያመጣ ሆኗል። በተለይ ህወሀት በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ፈጽሞ ከፌዴራል መንግስት ጋር ጦርነት ውስጥ በቆየባቸው ጊዜያት የውጭ ምንዛሬ ዋጋ በተለይም መደበኛ ባልሆነው ገበያ ንሯል።

Related stories   የፌደራልና የክልል ፖሊስ አዲስ የአደረጃጀት ሰነድ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ቀረበ

ሆኖም ብሄራዊ ባንክ በአንድ ባንክ በአንድ ሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ በባንክ ሂሳብ ገንዘብን ማስተላለፍ የሚከለክለውን ህግ ካወጣ በኋላ ባልተለመደ ሁኔታ የጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ቅናሽን አሳይቷል።

ይህን ዘገባ በሰራንበት ጥር 12 ቀን 2013 አ.ም በጥቁር ገበያ የአንድ የአሜሪካ ዶላር መግዣ 51 ብር ከ50 ሳንቲም ሲሆን መሸጫው ደግሞ ደግሞ 52 ብር ሆኗል። በመሸጫውም በመግዣውም ዋጋ ላይም በ12 ቀናት ውስጥ የ2 ብር ከ50 ሳንቲም ቅናሽ ታይቷል ። በባንኮችና በጥቁር ገበያ መካከል ያለው የአንድ አሜሪካ ዶላር ዋጋ ልዩነትም ከ16 ብር ወርዶ ከ12 ብር በታች ሆናል።

የታየው ቅናሽ መነሻም ብሄራዊ ባንክ በየጊዜው ያወጣቸው የገንዘብ ዝውውርን የሚገቱ መመሪያዎች መሆኑን ባለሙያዎች ነግረውናል። ከዚህ ቀደም በቀን ከአንድ ባንክ ከ50 ሺህ ብር በላይ ማውጣት የከለከለው ህግ በጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሬ ገበያ ላይ የተሰማሩ አካላት በባንክ ሂሳብ ገንዘብን በማዘዋወር የውጭ ምንዛሬን ለመገበያየት እንዲጠቀሙ ቢያደርጋቸውም አሁን ላይ በሳምንታዊ የባንክ ሂሳብ ዝውውር ላይም ገደብ መጣሉ መደበኛ ባልሆነው ገበያ ላይ የውጭ ምንዛሬን ለሚገበያዩ አካላት ለመገበያየት የሚያስችላቸውን ገንዘብ እንደልብ ማዘዋወር እንዳላስቻላቸው መረዳት ተችሏል። የውጭ ምንዛሬን በሚገዙትም ሆነ በሚሸጡትም በኩል የብር እንቅስቃሴ ገደቡ ጫና እየፈጠረ መሆኑም የጥቁር ገበያውን የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ዝቅ አድርጎታል።

Related stories   የ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ

በኢትዮጵያ የጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡ ሰሞን ቅናሽ ከማሳየትም አልፎ ከባንኮች የመገበያያ ዋጋም በጥቂት ሳንቲሞች እስከማነስ ደርሶም ያውቃል። ይህ የሆነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንድ ወቅት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው የውጭ ምንዛሬ በእጃቸው ያላቸው ሰዎች ለባንክ እንዲሸጡ ካስጠነቀቁ በሁዋላ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ገና ወደ ስልጣን በመምጣታቸው ሰዎችም አዲስ አይነት አሰራር ሊመጣ ነው የሚል ፍራቻ ስላደረባቸው ነበር የጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ከባንኮች ዋጋ እስኪያንስ ሰዎች እጃቸው ላይ ያለውን ምንዛሬ ለባንኮች ሲሸጡ ነበረ።

ነገር ግን ከጥቂት ቀናት በሁዋላ መደበኛ ባልሆነው የውጭ ምንዛሬ የታየው የዋጋ መውረድ መልካም ነው ሊባል ቢችልም ከባንኮችም ጋር ያለው የዋጋ ልዩነት በበቂ ሁኔታ ያልጠበበና ለገበያ መረጋጋት ዋስትና የሚሰጥ አይደለም። በተለይ ለውጭ ምንዛሬ ግኝት የሚያግዙ ስልቶች ካልተቀየሱ ኢኮኖሚው ወደባሰ ችግር ውስጥ ሊገባ እንደሚችል ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ።

ብሄራዊ ባንክ አሁን ተግባራዊ ያደረገው በሳምንት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ማዘዋወርን የሚከለክለውን ህግን ጨምሮ የብር ኖት ለውጥ ካደረገ በኋላ የተገበራቸው ህጎች የወረቀት ጥሬ ብር ዋና መገበያያ የሆነባትን ሀገር ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያላስገባ በመሆኑ ለንግዱ ማህበረሰብ ከፍተኛ ፈተናን የደቀነ ሆኗል። [ዋዜማ ራዲዮ]

 • ሀገሪቷን ከጥፋት ለመከላከል ፣ ህግን ለማስከበር ፌዴራል ፖሊስ ተግባሩን ያጠናክራል
  ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሀገሪቷን ከጥፋት ለመከላከል ፣ ህግን ለማስከበር በጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል በ19ኛ ዙር ያሰለጠናቸው 6 ሺህ 431 የፖሊስ አባላት መመረቃቸው ተመላክቷል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 792 የሚሆኑት የአፋር ክልል ልዩ ኃይል አባላት መሆናቸውም ተገልጿል። በምረቃ ስነ ስርዓቱ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍContinue Reading
 • Congolese President Presents Initiative to Resolve GERD Dispute
  Congolese President and current chair of the African Union Felix Tshisekedi presented an initiative to resolve Ethiopia’s dispute with Egypt and Sudan on the Grand Ethiopian Renaissance Dam. The initiative was announced by Tshisekedi during his talks with the Head of Sudan’s Transitional Sovereign Council Abdel Fattah al-Burhan and Sudan’sContinue Reading
 • US Special Envoy Donald Booth arrives in Juba today
  The United States Department of State has said in a press release yesterday that the US Special Envoy Donald Booth will arrive in Juba today May 8, 2021. “U.S. Special Envoy for Sudan and South Sudan Donald Booth will travel to South Sudan from May 9 to May 13, 2021.Continue Reading
 • SSOMA boycotts Rome talks due to killing of rebel commander
  The South Sudan Opposition Movements Alliance (SSOMA) affiliated with Gen. Thomas Cirillo have said that they were going to boycott the Rome peace talks which were slated to commence May 8, 2021. A statement by SSOMA seen by Radio Tamazuj over the weekend read in part, “SSOMA would like toContinue Reading

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *