“አብይ አህመድ ሰው ናቸው። አብይ አህመድ ሰው ላይ ሊደርስ የሚችለው ሁሉ ይደርስባቸዋል። በመሆኑም ቢታመሙ፣ ጉዳት ቢደርስባቸው አይገርምም። ላለፉት ሶሰት ዓመታት ጉያቸው ውስጥ በተሰገሰጉ እንግዴ ልጆች የደረሰባቸውን መከራ፣ ሴራና በሕዝብ ላይ ሲፈጸም የቆየውን፣ አሁንም እየሆነ ያለውንና አገሪቱ ከገባችበት የባንዳዎችና የውክልና ዘመቻ አንጻር ምንም ዓይነት ዜና ቢሰማ አይገርምም” ሲሉ አስተያየት የሰጡ አሉ።
ሰሞኑንን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን አስመልክቶ ሲወርድ ለነበረው ሟርት ጽህፈት ቤታቸው ባጭሩ “የሃሰት ወሬ” ሲል ምላሽ ሰጥቷል። ጽህፈት ቤቱ ይህን ከማለቱ በፊት ግን ለበርካቶች የሚያሳዝን፣ እርባና የሌለው መረጃዎችን መመልከት ግድ ነበር። ይህ ግዴታ ቀዳማይ እመቤት ዝናሽ ያስገነቧቸውን ዘመናዊ ትምህርት ቤቶች እንኳን ከህዝብ ስሜት አንጻር እንዳናጣጥም ጋርዶናል።
ዛጎል የተለያዩ አዝናኝና አሳዛኝ የመረጃ አይነቶችን በማሰባሰብ ለልምድ እንዲሆን አዘጅታለች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ” በሚሊዮን የሚቆጠር ጉንዳን መሸከም ” ሲሉ ምሳሌ ያቀረቡበትን የሃላፊነታቸውን አሳር የተረዱ ” ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጤነኛ ሆነው መኖራቸው እንጂ ቢታመሙና እረፍት ቢያደርጉ አይገርምም” ይላሉ። ሃዘኔታቸውንም ይገልጹላቸዋል።
አቶ ጥበበ ገላዬ ለፍቶ አዳሪ የጅግጅጋ ነዋሪ ናቸው። ” እኚህ ሰውዬ ፈርዶባቸዋል” ሲሉ ይጀምራሉ። አስከትለው ” እርሻ ሲጎበኙ፣ ከተማ ሲያጸዱ፣ አትክልት ሲያጠጡ … ፎቶ ይወዳሉ” እያሉ ይሰድቧቸዋል። ኢትዮጵያ ልትፈርስ ደርሳ ” ኢትዮጵያን እናድን” የሚሉ ባንዲራ ለብሰው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሲያዋርዱ እንደሚውሉ ጠቅስው ህይወታቸው እንደሚያሳዝናቸው አመልክተዋል።
ሰለሞን ሃይሌ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆን መርካቶ በግል ስራ ይተዳደራል።” እኔን የገረመኝ ‘ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰላም መሆናቸውን እንዳጣራ በጠየቃችሁኝ መሰረት ምንጮቼን ጠይቄ ደህና መሆናቸውን አረጋግጫለሁ የሚሉት ናቸው”
አቶ ታዬ ደንደአ በፊስ ቡክ ገጻቸው ” ሰላም ነው” ሲሉ ጻፉ። ወዲያው ስድብ ወረደባቸው አንዱ ” እናንተ ከሱዳን ጋር ሆናችሁ ኢትዮጵያን የምትወጉ” ሲል ዘለፋቸው። ብልጽግና ፓርቲ ከሱዳን ጋር መክሮ ኢትዮጵያን እየወጋ እንደሆነ አስተያየት የሰጠው ሰው ብልጽግና የሚመራው መንግስት የሱዳን ስትራቴጂካል አጋር የሆነውን ወያኔንን እንዴትና ለምን ታሪክ እንዳደረገው እንዴት እንደሚያዩት አግኝቶ ማናገር አልተቻለም።
የቫይበር አካውንታቸውን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስል ያስጌጡ አዛውንት እናት ” ልጄን ምን ነካው? ምነው እምዬ ማሪያም” ሲሉ ሃዘን እንደገባቸው ይናገራሉ። እኚህ እናት ለረዥም ጊዜ የተለየቻቸውን ልጃቸውን ከእስር ቤት አስወጥቶ ያመጣላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ምንም እንዲነካቸው አይፈልጉም።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ደህንነት አስመልክቶ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ የሀሰት እንደ ሆነ ሁሉም ሰው እንዲገነዘብ ለማሳሰብ እንወዳለን። We ask members of the public to be vigilant about fake news circulating about Prime Minister Abiy Ahmed’s well being on social media.
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ህይወት አደጋ ውስጥ እንደነበረ የሚጠቁሙ መረጃዎች ዓለምን ከማዳረሳቸው በላይ፣ በአገር መከላከያ አባላት ዘንድም ግርታን ፈጥሮ እንደነበር፣ ወዲያውኑ መረጃ በአግባቡ እንዲደርስ ተደርጎ መስተካከሉን የሚጠቁሙ ወገኖች በአንድ ነገር ይደሰታሉ።
አብይ አህመድ በስራ ላይ ሆነው ሳለ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ” ወሬው ሃሰት ነው” ማለቱ ሕዝብ እንዲረጋጋ ታስቦ ቢሆንም አብዛኛው ህዝብ ሟርቱንም ሆነ የሟርቱን ማስተባበያ አይሰማም። ከ120 ሚልዮን ሕዝብ ውስጥ ምን ያህሉ ይህን መረጃ ተቋድሶታል? ምን ያህሉ አምኗል? ምን ያህሉ … በሚል ሂሳብ  ሲሰላ ደስታን እንደሚሰጣቸው የሚጠቁሙ ክፍሎች ” ሁሌም አብዛኞች የአጥፊዎችን ሃሳብ ስለማይጋሩ እስከዛሬ ኖረናል። ወደፊትም ይቀጥላል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ግን ማንም ባሟረተ ቁጥር ማስተባበያ መስጠቱን ያቁም” ብለዋል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ አቅል ያጣ ፍላጎት ግን ምንድን ነው!?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *