በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያዊያንን የመመለስ ስራ ተጀምሯል፤ የመጀመርያዎቹ 296 ኢትዮጵያውያን ወንድ ስደተኞች በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቋል ተብሏል።
በሳምንት ውስጥ 1 ሺህ ኢትዮጵያውያንን ለመመለስ ስራው መጀመሩን በሀገሪቱ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
ወደ ሳዑዲ አረቢያ ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች ሲገቡ ተይዘው በሳዑዲ አረቢያ የተለያዩ የስደተኞች ማቆያ ጣብያ ውስጥ የሚገኙና ላለፉት ወራት ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ወደ ሀገር መመለስ ያልቻሉ የነበሩ ዜጎችን በስፋት ወደ ሀገር የመመለስ ስራ መጀመሩ ኤምባሲው አስታውሷል።
በዚሁ መሰረት በጅዳ ሹሜሲ የህገወጥ ስደተኞች ማቆያ ውስጥ የነበሩ የመጀመርያዎቹ 296 ኢትዮጵያውያን ወንድ ስደተኞች በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል ተብሏል።
ይህ ዜጎችን የመመለስ ስራ መንግስት ከሳዑዲ አረቢያ ወገን ጋር ባደረገው ስምምነትና በተቀመጡ አቅጣጫዎች መሰረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኤንባሲው ጠቁሟል።
በዚህም በየሳምንቱ 1 ሺህ ተመላሾች ወደ ሀገር የሚገቡ ሲሆን ወደፊት በመንግስት በኩል በሚሰጡ አቅጣጫዎች መሰረት የተመላሾች ቁጥር ይጨምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
(ኢ ፕ ድ)

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *