“Our true nationality is mankind.”H.G.

መንግስት ሰማ፤ ዓለም ሊያስተባብለው የማይችለው ጭፍጨፋ የሃኪሞች የመጨረሻ ምርመራ ተጠናቆ ይፋ ሊሆን ነው

. በማይክድራ ተጨማሪ 117 የመቃብር ጉድጓዶች ተገኝተዋል
በትግራይ ” የህግ ማስከበር ዘመቻ” ከተተናቀቀ በሁዋላ የዓለም ሚዲያዎች ፍጹም ቁብ ያልሰጡትና ወደ አንድ ወገን ያጋደለ ሪፖርት በማቅረብ ዘመቻ ላይ የተጠመዱ ሚዲያዎች ወደ አዲስ አበባ ማቅናታቸውን ተከትሎ ከስማ በለው ተላቀው ሃቁን እንዲዘግቡ መንግስት ሲደርስበት የነበረውን ጫና ተቀብሎ ዝግጅት ማተናቀቁ ተሰማ። ተግባሩ የሚዲያ ዘመቻውን ያመታጥነዋል ተብሎ ግምት አግኝቷል።
በትግራይ አስቀድሞ ከነበረው የምግብ እጥረትና 1,2ሚሊዮን የሚሆኑ የሲፍቲ ኔት ወይም የስንዴ ደሞዝተኞች ቀለብ በጊዜ ሊደርሳቸው አለመቻሉ የረሃብ አደጋ ማስከተሉ ሰፊ የሚዲያ ዘመቻ አግኝቷል። የትባበሩት መንግስታትና የአውሮፓ ህብረት ሳይቀሩ ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። ሃላፊዎቻቸውንም ወደ ኢትዮጵያ እየላኩ ነው።
የግንኙነት መስመሮቸው መበጣጠስ፣ የመረጃ ዳታቸው ፣ የመብራትና ኢንተርኔት አገልግሎት መውደምና የያዙት ገንዘብ መዘረፉ ባንኮች ስራ እንዳይጀመሩ ማድረጉ የትግራይን የረሃብ ቀውስ አባብሶታል። ጉዳዩን በቅርብ ሆነው የሚከታተሉ እንዳሉት 1.3 ቢሊዮን አዲሱ የብር ኖትና ቀደም ሲል ህዝብ የሚቆጥበውና የመንግስትና የግል ተቋማት የሚያንቀሳቅሱት ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ተዘርፏል። ዝርፊያው የተፈጸመው ደግሞ በትህነግ አመራሮችና የቅርብ ሃይሎች ነው። ይህ ተዳምሮ የትግራይን ቀውስ የከፋ እንዲሆን ቢያደርገውም ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች መንግስትን ለጉዳዩ ተጠያቂ አድርገው ዘገባቸውን ገፍተውበታል።
ይህ በንዲህ እንዳለ ነው መንግስት በትግራይ አብዛኛው ክፍል ኬላ መነሳቱን፣ አብዛኛው የትግራይ ክልል ለእርዳታ ተጋባር ዝግጁ መሆኑንን ያፋ ያደረገው። ከመንግስት የሚወጡ መረጃዎችና የተባበሩት መንግስታትና አንዳንድ እርዳታ ሰጪዎች እንደሚሉት እርዳታ እየሰጡ ይገኛሉ። የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደረም የዘገባዎች መጋነን አግባ አለመሆኑንን በመጥቀስ መረጃ መስጠቱን ተከትሎ አንቱ የተባሉ ሚዲያ መሪዎች ” የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዶ/ር ሙሉ ስልታናቸውን ለቀቁ” እስከማለት ደርሰዋል። ማንኛውንም ዘገባ ሲሰሩ ሃሳብ እንዲሰጡ አያደርጓቸውም።
በመንግስት በኩል ሃቁን ከማሳውቅና ከማስተባበል አንጻር ድክመት እንዳለ ቢነገርም፤ አንዳንድ ወገኖች ” መንግስት የጦርነቱን ስያሜ የህግ ማስከበር ” እተብሎ ዓለም እንዲቀበለው ከማድረግ ጀምሮ የተሳካ ስራ መስራቱ ይናገራሉ።
የድጋፉም ይሁን የትችቱ አስተያየት የመንግስት የሚዲያ ዘመቻ ከትህነግ ደጋፊዎች ጋር ሲተያይ ጉድለት እንደነበረበትና ይህ ጉድለት አሁን ድረስ እንዳልተስተካከለ ስምምነት አለ። ለዚህም ይመስላል መንግስት ስህተቱን በማረም አማባሳደሮቹን፣ ዲፕሎማቶቹንና ወዳጅ አገራትን በማነቃነቅ አዲስ ዘመቻ የጀመረው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ትህነግ ፈጸማቸው የሚባሉትን ወንጀሎች ይፋ የማድረጉም ስራ እየተሰራ ነው።
የማይካድራ ጭፍጨፋ ሙሉ የምርመራ ውጤት ከሀኪሞች እንደተገለጸ ለዓለም ይፋ እንደሚሆን ይፋ የሆነው ዛሬ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በትግራይ የትህነግ ሃይል የፈጸማቸውን ወንጀሎች ለቅሞ በማውጣት ለዓለም ሚዲያዎች ለማሳየት ስራ መጠናቀቁም ተሰምቷል።
ፋና እንዳለው በማይካድራ ጭፍጨፋ ከተሳተፉት 279 ተጠርጣሪዎች መሀል ያልተያዙትን ለማደንና ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቀዋል። ፋና ይፋ ባያደረገውም ይህ የሚሆነው ሰሞኑንን ወደ አገር ቤት የሚገቡትን የውጭ ሚዲያዎች ወደ ስፋራው የመውሰድና ምስክርነት የማሰጠት፣ ይህንኑ ምስክርነት አንድ ወገን ደግፈው በጻፉበትና ባወሩበት ደረጃ እንዲዘግቡ የማስቻል ስራ ይሰራል። ሚዲያዎቹ ወደ መቀሌ ማምራት ቢፈልጉም ማይካድራን እንዲያካትቱ እንደሚደረግ ሰምተናል። ከታች ፋና የሚከተለውን ዘግቧል።
ከማይካድራ ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ የአካባቢው ወጣቶች ሙሉ የምግብ አቅርቦት ተሟልቶላቸው ፀጥታን ታስከብራላችሁ በሚል ተመልምለው ስምሪት እንደተሰጣቸው ተገለፀ፡፡ ጭፍጨፉውን የሚያከናውኑበት ስለታማ ነገሮችም ቀድሞ ታድሏቸው እንደነበረ ተገልጿል። በጉዳዩ ላይ በተደረገ ምርመራ ጭፍጨፋው ብሄር ተኮር እና በአብዛኛው ወንዶች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል፡፡
በሂደቱም 10 ሴቶች መደፈራቸው ነው የተነሳው። ከጭፍጨፋው በኋላም በተለያዩ ቦታዎች ላይ ከ117 በላይ ጉድጓዶች መገኘታቸውን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የሙስናና የተደራጁ ወንጀል ጉዳዮች ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ፍቃዱ ፀጋ እና የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራልና የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም መንግስቴ በጋራ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል፡፡
ሙሉ ውጤቱም በምርመራ ስራው ላይ ከተሳተፋ ሀኪሞች ሲገለፅ ይፋ እንደሚደረግ ተነግሯል ። በማይካድራ ጭፍጨፋ ከተሳተፉ 279 ተጠርጣሪዎች ውስጥ 36ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል፡፡ ቀሪዎቹ በስደተኛ ስም ወደ ሱዳን ገብተዋልም ነው የተባለው፡፡ ምርመራው አሁንም ያልተጠናቀቀና በተቋቋመው ግብረ ሀይል አማካኝነት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑም ተገልጿል ።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   “…ለዛሬ ብለን ነገን ከምናበላሽ፣ ለነገ ስንል ዛሬን እንሠዋ” አብይ አህመድ
0Shares
0