የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንዳንድ የአገልግሎት ዋጋዎች ላይ ጭማሪ ማድረጉን አስታወቀ። ለቤቶች ልማት 9.5 በመቶ የነበረው የብድር ወለድ 10.5 በመቶ ተደርጓል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንዳንድ የአገልግሎት ዋጋዎች ላይ የማሻሻያ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል። ባንኩ ጭማሪውን ለማድረግ የተገደደው ባለፉት 5 ዓመታት የባንኩ እድገት በአማካይ 26 በመቶ በመሆኑ ሂደቱ እየቀነሰ በመምጣቱ መሆኑን የባንኩ ፕሬዝደንት አቶ አቤ ሳኖ አስታውቀዋል። በዚህም የኮርፖሬት ቦንድ የብድር ወለድ 8 በመቶ የነበረው 9 በመቶ ደርሷል።
ለቤቶች ልማት በ9.5 በመቶ የብድር ወለድ ይሰጥ የነበረ ሲሆን የነበረው 10.5 በመቶ ተደርጓል። ለውጭ ምንዛሪ አገልግሎትም በ90 ቀናት ወይም በአንድ ፔሬድ የነበረው 5.5 በመቶ ሲሆን አሁን ወደ 9.5 በመቶ ከፍ ማለቱ ተገልጿል።
ሆኖም ለማዳበሪያ፣ ለኤሌክትሪክ ኃይል፣ ለመድሀኒት አቅርቦት፣ ለስኳር እና ለዘይት የሚያስፈልጉ የውጭ ምንዛሪያዎች በ4.5 በመቶ ዝቅ ተደርጓል። የተደረጉት የምንዛሪ አገልግሎት ዋጋ ማሻሻያዎች ከዚህ ወር ጀምረው እንደሚተገበሩም ተገልጿል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
ምንጭ:-ኢፕድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *