አፍሪካ ልማት ተማሪዎች ሊግ 32ኛዋን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ከፍተና ያለውን የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት እንደሚቸልም ይፋ አደረገ። ነገ በስካይ ላይን ሆቴል በሚደረገው ሽልማት አዳኔች አቤቤ የአፍሪካ ለማት ተማሪዎች ሊግ የማራር ብቃት / አርበኝነት ሽልማት LEADS AFRICA’S PATRIOTIC LEADERSHIP AMAZON ይበረከትላቸዋል።

የሊጉ ዋና ጸሃፊ ሚር ኦሲሲዮጉ ኦስሊክኒየ  በስልክ ለኢትዮ 12 እንዳስታወቁት የአዲስ አበባ የመጀመሪያዋ ሴት ከንቲባ ለዚህ ሽልማት የበቁት በተለያዩ የሃላፊነት መደብ ላይ ሆነው ” አርበኛነት የተላበሰ የአመራር ብቃት በማሳየታቸው ነው”ብለዋል። አያይዘውም ለዚህ የላቀ የአመራር ስብ ዕናቸው የድርጅታቸውን LEADS AFRICA’S PATRIOTIC LEADERSHIP AMAZON ሽልማት እንዲያገኙ መወሰኑንን የሚያበስሩት በታላቅ ኩራት እንደሆነ አመልክተዋል።

በቆፍጣናነታቸው በአገር ውስጥ የሚታወቁትና ቀደም ባሉት ዓመታት በነበሩባቸው ሃላፊተቶች ከአገልግሎት ፈላጊዎች፣ ከስራ ባልደረቦቻቸውና ከመንግስት ከፍተኛ አለቆቻቸው ምስጋና የሚቀድምላቸው አዳነች አቤቤ ሲቶችን ወደ አመራር ለማምጣት እያደረጉ ያለው እንቅስቃሴም የሊድስ አመራሮችን ቀልብ ስቧል። ሃምሳ ከመቶ ካቢኔዎቿን ሴት ያደረገችው ኢትዮጵያ እንደ አዳንች አቤቤ ባሉ የአመራር አርበኞች ይበልጥ ሴቶች ወደ አመራር ይመጣሉ የሚልም ተስፋ አለ።አዳነችም እሳቸውን የሚመሳሰሉ አመራሮችን ስለሚፈጥሩ ይህ የአመራር አርበኛነት ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ከስልክ ምልልሱ ለመረዳት ተችሏል።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

የወ/ሮ አዳነች አቤቤን የአምራር ብቃት በገቢዎችና ጉምሩክ፣ እንዲሁም በጠቅላይ አቃቤ ህግ መንበራቸው ላይ በብቃት የታየ መሆኑንን ያመከቱት የሊድስ ዋና ጸሃፊ በዚህ ሁሉ የሃላፊነት መንገዳቸው የላቀ አመራር ባለቤት በመሆናቸው ጥንታዊቷን ከተማ ለመምራት ብቁ ሆነው እንዲመረጡ እንዳስቻላቸው ገልጸዋል። አያይዘውም ” ይህ ለአፍሪካ ሴቶች ኩራት ነው። ከፍተኛ የማጣቀሻ ምንጭም ያደርጋቸዋል” ሲሉ አወድሰዋቸዋል።

ወይዘሮ አዳነችን ላበረከቱት ተግብራና ተነሳሽነት እውቅና ለመስጠት ሽልማቱ እንድተዘጋጀላቸው ያስታወቁት ጸሓፊው “ ወ/ሮ አዳነች አቅሙና ችሎታው ስላላቸው ሴቶችን ከማብቃት አንጻር፣ ለአህጉራችንም ሆነ ለኢትዮጵያ ሰፊ ስራ እንደሚሰሩ እናምናለን” ሲሉ ለወድፊቱ ስራቸው በክፈተኛ ደረጃ ሊበረታቱ ይገባል የሚል እምነት መያዙን ገልጸዋል።

ሊድስ እንዳሳወቀው ምክትል ከንቲባ አዳነች ነገ ማርች 28 በስካይ ላይን ሆቴል የአመራር ብቃት እውቅና ሽልማታቸውን ይወስዳሉ።


 • አዳነች አቤቤ የላቀ/ የአርበኛነት የአመራር ሽልማት እንደሚሸለሙ የአፍሪካ የልማት ተማሪዎች ሊግ አስታወቀ

  የአፍሪካ ልማት ተማሪዎች ሊግ 32ኛዋን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ከፍተና ያለውን የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት እንደሚቸልም ይፋ አደረገ። ነገ በስካይ ላይን ሆቴል በሚደረገው ሽልማት አዳኔች አቤቤ የአፍሪካ ለማት ተማሪዎች ሊግ የማራር ብቃት / አርበኝነት ሽልማት LEADS AFRICA’S PATRIOTIC LEADERSHIP AMAZON ይበረከትላቸዋል። የሊጉ ዋና ጸሃፊ ሚር ኦሲሲዮጉ ኦስሊክኒየ  በስልክ […]
 • ከትግራይ ተሰውረው አዲስ አበባ በወንጀል ተሰማርተው የነበሩ135 ተጠርጣሪዎችን ጨምሮ በጥቅሉ 359 ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ተያዙ

  የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ባከናወነው ሰፊ ዘመቻ ተደራጅተው በርፊያና በግድያ የተሰማሩ፣ በግል አሸከርካሪዎች ላይ አፈና የሚፈጽሙ ህገወጥ መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የነበሩ 359 ተጠርጣሪዎችን በሕዝብ ጥቆማና አደን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ። ሙሉ መግለጫው እንደሚከተለው ይነበባል።የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና […]
 • ስዩም ተሾመና ሙክታሮቪች ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላድብደባ ደረሰባቸው፤

  የሰላ ትችት በመሰንዘር የሚታውቀት ስዩም ተሾመና ሙክታሮቪች ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ሰዎች ታፍነው ድብደባ እንደተፈጸማቸው ተሰማ። ስዩምና ሙክታሮቪች በትላንትናው እለት፣ ከምሽቱ አንድ ሰአት ግድም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የግድያ ሙከራ እንደተፈፀመባቸው የገለጹት የአይን እምኞች እንደሆኑ አርአያ ተስፋ ማርያም ነው። አንድ አምቡላንስ እነስዩም የተሳፈሩበትን መኪና መንገድ ዘግቶ ካስቆማቸው በሁዋላ አንዱ […]
 • ዶ/ር ዳንዔል- በማይካድራው ጭፍጨፋ የትህንግ አመራሮች ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስለመኖሩ መረጃ የለም

  ” ይህ አስተያየት እኮ ነው” አሉ ዶክተር ዳንዔል በቀለ ” በእኔ አስተያየት ግን ሙሉ በሙሉ ስህተት ነው” ሲሉ እንደማይቀበሉት አስታወቁ። አከሉና በማይካድራው ጭፍጨፋ የትህንግ አመራሮች ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስለመኖሩ መረጃ እንደሌለ “እኛ የሰብአዊ መብት ምርመራ ሥራ የምንሰራው ለተወሰነ የፖለቲካ ጥቅም፣ ለተወሰነ የፖለቲካ አጀንዳ፣ ለተወሰነ የፖለቲካ ፍላጎት ብለን ሳይሆን ለሰብአዊ […]

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *