” ይህ አስተያየት እኮ ነው” አሉ ዶክተር ዳንዔል በቀለ ” በእኔ አስተያየት ግን ሙሉ በሙሉ ስህተት ነው” ሲሉ እንደማይቀበሉት አስታወቁ። አከሉና በማይካድራው ጭፍጨፋ የትህንግ አመራሮች ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስለመኖሩ መረጃ እንደሌለ “እኛ የሰብአዊ መብት ምርመራ ሥራ የምንሰራው ለተወሰነ የፖለቲካ ጥቅም፣ ለተወሰነ የፖለቲካ አጀንዳ፣ ለተወሰነ የፖለቲካ ፍላጎት ብለን ሳይሆን ለሰብአዊ መብት አጀንዳ ብቻ ብለን ነው።” ሲሉ አመለከቱ።

አርት ቲቪ በአርትስ ወቅት ፕሮግራሙ እንግዳ ያደረጋቸው ዶ/ር ዳንዔል ይህንን ያሉት እሳቸው የሚመሩት ኮሚሽን የተወላገደ አቋም ይዞበታል በተባለው የማይካድራ ጉዳይ ሲጠየቁ ነው ከላይ በተባለው መልኩ ምላሻቸውን የጀመሩት። ዶክተሩ “ለነጮች ያደራችሁ” በሚል እንደሚወቀሱ ከጠያቂው ሲነሳላቸው መቅመቻቸውን እያስተካከሉ ነበር ምላሻቸውን አስተያየቱን እንደማይቀበሉት በማመልከት የጀመሩት።

በማይካድራ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ በግልጽ አካባቢውን ሲያስተዳድር፣ በነበረው ወይም በወቅቱ ስራ ላይ በነበረው ሃይል ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎችና ሳምሪ በሚባል የወጣቶች ቡድን ወይም ኢመደበና አደረጃጀት እንደተፈጸመ በመጀመሪያ ደረጃ ኮሚሽናቸው ሪፖርት ማድረጉን በግልጽ አስታወሱ። አያያዙና ” ከዛ አልፎ ሲተረጉሙት ከህወሃት መመሪያ በቀጥታ ተሰጥቷቸው ነው …” በሚል በትርጉም እዛ ደረጃ እንደወሰዱት ገልጸው ” እኛ ግን እንደሱ አንሰራም” ሲሉ ዋናውን የመነጋገሪያ አጀንዳና የኮሚሽናቸውን አቋም ይፋ አደረጉ።


የሰብአዊ መብት ኮሚሽን “የግፍ ደረጃ መዳቢ” – የማይካድራ ምርመራ ላይ ደባ እየተሰራ መሆኑ ተሰማ፤ ኮሚሽኑ ምላሽ ከለከለ


ኢትዮ 12 ሰሞኑንን በተከታታይ የማይካድራ ጭፍጨፋ ሪፖርት ላይ ደባ እየተፈጸመ እንደሆነ ጥቆማ ስለደረሰን ለኮሚሽኑ ጥያቄ አቅርበን ምላሽ መነፈጋችንን፣ በማይካድራ ጭፍጨፋ ሪፖርት ዙሪያ ደባ እየተሰራ መሆኑንን መዘገባችን ይታወሳል።

” የትዕዛዝ ሰንሰለቱ ምን አልባት እስከ ላይኛው አካል ድረስ የሚደርስ ከሆነ፤ የት ድረስ እንደደሚደርስ በማስረጃ የተደገፈ ነገር ካለ፣ ያንን የንደርስበት በማስረጃ የምናረጋግጠው ከሆነ ባረጋገጥን ጊዜ እንለዋለን… ” ሲሉ በቀጣዩ ሪፖርት ሊካተት እንደሚችል የገለጹት በጭፍጨፋው የትህነግ አመራሮች በግልጽ እጃቸው እንዳለበት እየታወቀ ስማቸው የማይተቀስበትን ምክንያት ተከትሎ ለተነሳባቸው ” ለነጭ አዳሪ” የሚል ይዘት ያለው ትችት ምላሻቸውን ምክንያታዊ ሲያደርጉ ነው።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

Read also this

በማይካድራ የጅምላ መቃብር ተገኘ፤ በህወሓት የተገደሉት ቁጥር ከ1300 እንደሚበልጥ ተነገረ

የማይካድራ ከተማ ከንቲባን አቶ ቸሩ ሀጎስ የቀበሌ 01 ሊቀመንበር አብሪሁ ፋንታሁን እና የከተማዋን ነዋሪዎች ጠቅሶ  ጌቲ ኢሜጅስ በምስል አስደግፎ ባሰራጨው መረጃ ላይ እንደተገለጸው፤ እአአ ማርች 5/2020 በአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን የጅምላ ቃብ ውስጥ ከ1300 በላይ የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑ ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል።

የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑት እነዚሁ ሟቾች ህወሓት ሳምሪ በሚል ባደራጃቸው ወጣቶች፣ ሚሊሻዎች እና በፖሊሶቹ አማካኝነት የተገደሉ መሆኑን ታዋቂው ዓለምአቀፍ ሚዲያ ጌቲ ኢሜጅስ በዘገባው ጠቅሷል።

ሟቾቹ በአከባቢው ላሉ ባለሀብቶች በጉልበት ስራ ተቀጥረው የሚሰሩ ንጹሀን መሆናቸውን ያስታወሰው ዘገባው፤ ገዳዮቹ ቤት ለቤት እየሄዱ የአማራ ብሄር ተወላጆችን እየመረጡ ጭፍጨፋውን መፈጸማቸውን ገልጿል።

አብዛኛዎቹ ሟቾች በስለታማ መሳሪያዎች ተጨፍጭፈው የተገደሉ ሲሆን፤ በዚህ ጭካኔ ከተሞላበት ጥቃት ነፍሳቸው የተረፈችው ደግሞ በጥይት እንደገደሏቸው ነው ዘገባው ያስታወቀው።

ሟቾቹ በወቅቱ በየመንገዱ ዳር፣ በውሃ መፈሳሻ ቦይዎች፣ በህወሓት አመራሮች በተቆፈሩ ጉድጓዶች እና በእርሻ ቦታዎች ላይ ተጥለው እንደተገኙም ገልጿል።

በማይካድራ አካባቢ አሁንም ድረስ የሟቾች አስከሬን በተለያዩ ቦታዎች እየተገኘ መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ


“ምርመራውን በሰራን ጊዜ ከዛ ባለፈ በመርመራ ያረጋገጥነው ነገር ስለሌለ የምንናገረው እስከ ደረስንበት ደረጃ ያለውን ነው የምንናገረው ” ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ከዛም ተቃውሞ የተነሳበትን ክፍል በቀጥታ ባይገልጹም ” የፖለቲካ ተንታኞች” ሲሉ ጠርተው ለመናገር ብዙም ማስረጃ ሳያስፈልጋቸው ትንተና ሊሰጡ እንደሚችሉ አመልክተዋል።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

” እኛ ግን በማስረጃ ተመስርተን ነው የምንሰራው፤ ስለዚህ በማስረጃ ያላረጋገጥነውን ነገር አንናገርም።… በጠቅላላው ህብረተሰብ አረዳድ ደረጃ ፣ እንደሌላው ተንታኝ ሁላ ደግማችሁ ተናገሩት ልንባል አንችልም” የሚል ምላሽ ሲሰጡ ቀደም ሲል ” በውቅቱ አካባቢውን ሲያስተዳር የነበረው ሃይል ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎችና ሳምሪ የተባለ የወጣቶች ቡድን በግልጽ ጭፍጨፋውን እንደፈጸመ ሪፖርት አድርገናል” ካሉት ጋር አያይዞ ጠያቂው እርስ በርስ የሚጣላ ትንተና ሲሰጡ እንደነበር ለማጥራት አልሞከረም።

በወቅቱ አካባቢውን ሲያስተዳድር የነበረው ትህነግ መሆኑ እየታወቀ፣ የጸጥታ መዋቅሩና የወጣቶች አደረጃጀቱ ባለቤትና ደሞዝ ከፍሎ የሚመራው ህወሃት ስለመሆኑ ቅንታት ብዥታ በሌለበት ሁለታ ኮሚሽነሩ ማስረጃ የለንም ለማለት ያነሳሳቸው ምክንያት ቀድሞ ሲነሳ የነንበረውን ጥርጣሬ የሚያጎላ እንደሆነ ተጠቁሟል። ከዚያም በላይ ዛሬም ሪፖርቱ ሊዘገይ የቻለበትን ምክንያት አልገለጹም።

ትግራይ ለተፈጸመው ያልተገባ ተግባር መንግስት በቀጥታ ድፈሩ፣ ንጹሃንን ግደሉ፣ ሴቶችን አሰቃዩ የሚል መመሪያ በቀጥታ ስለመስጠቱ ምንም ማስረጃ ባለቀረበበት ሁኔታ እሳቸው የሚመሩት ኮሚሽን በማይካድራው እጅግ የከፋ በተባለው የስለት ጭፍጨፋ ዶከተሩ ህወሃትን ለማራቅ የሄዱበት መንገድ ወደፊት የሚቀርበውን የማጠቃለያ ሪፖርት ከወዲሁ ጥያቄ ውስጥ የሚከት ሆኗል።

ኮሚሽናቸው ስራውን የሚሰራው በማስረጃ እንደሆነ፣ አሰራሩም ተቀባይነት ባለው ሳይንሳዊ የምርመራ ስልት የሚመራ መሆኑንን፣ እንዴት ምርመራና ትንተና እንደሚሰራ የተቀመጡ መመዘናዎች መኖራቸውን በማስታወስ ትችቱን ፖለትካዊ እንደሆነ አስመረውበታል። በተወሰነ ደረጃ የምርመራ ስራን ካለመረዳት ወይም የሰብአዊ መብት ስራው የተለያዩ አካልት ካላቸውና ከሚፈልጉት አስተሳሰብ ጋር ሲገናኝ የመቀበል፣ ሳይገናኝ የመግፋት ዝንባሌ እንዳለም አመልክተዋል።

 • ከትግራይ ተሰውረው አዲስ አበባ በወንጀል ተሰማርተው የነበሩ135 ተጠርጣሪዎችን ጨምሮ በጥቅሉ 359 ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ተያዙ

  የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ባከናወነው ሰፊ ዘመቻ ተደራጅተው በርፊያና በግድያ የተሰማሩ፣ በግል አሸከርካሪዎች ላይ አፈና የሚፈጽሙ ህገወጥ መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የነበሩ 359 ተጠርጣሪዎችን በሕዝብ ጥቆማና አደን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ። ሙሉ መግለጫው እንደሚከተለው ይነበባል።የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና […]
 • ስዩም ተሾመና ሙክታሮቪች ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላድብደባ ደረሰባቸው፤

  የሰላ ትችት በመሰንዘር የሚታውቀት ስዩም ተሾመና ሙክታሮቪች ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ሰዎች ታፍነው ድብደባ እንደተፈጸማቸው ተሰማ። ስዩምና ሙክታሮቪች በትላንትናው እለት፣ ከምሽቱ አንድ ሰአት ግድም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የግድያ ሙከራ እንደተፈፀመባቸው የገለጹት የአይን እምኞች እንደሆኑ አርአያ ተስፋ ማርያም ነው። አንድ አምቡላንስ እነስዩም የተሳፈሩበትን መኪና መንገድ ዘግቶ ካስቆማቸው በሁዋላ አንዱ […]
 • ዶ/ር ዳንዔል- በማይካድራው ጭፍጨፋ የትህንግ አመራሮች ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስለመኖሩ መረጃ የለም

  ” ይህ አስተያየት እኮ ነው” አሉ ዶክተር ዳንዔል በቀለ ” በእኔ አስተያየት ግን ሙሉ በሙሉ ስህተት ነው” ሲሉ እንደማይቀበሉት አስታወቁ። አከሉና በማይካድራው ጭፍጨፋ የትህንግ አመራሮች ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስለመኖሩ መረጃ እንደሌለ “እኛ የሰብአዊ መብት ምርመራ ሥራ የምንሰራው ለተወሰነ የፖለቲካ ጥቅም፣ ለተወሰነ የፖለቲካ አጀንዳ፣ ለተወሰነ የፖለቲካ ፍላጎት ብለን ሳይሆን ለሰብአዊ […]
 • “አማራ እና ኦሮሞን በካራ ሌላውን ብሄር በጥይት”

  ምንም እንኳን ሰልፍ ባይወጣላችሁ፣ ፈረንጅ ባይጮህላችሁም ከሌሊት አውሬ የተረፈ አስክሬናችሁን አሞራ ሲራኮትበት፣ ደማችሁን ውሻ ሲልሰው አይቻለሁ እና መቼም ልረሳችሁ አልችልም። ሲል ይጀምራል እማኙ ወታደረ ዘርዩን ኑሪ አቦቴ። “አማራ እና ኦሮሞን በካራ ሌላውን ብሄር በጥይት” እንደ ወንጀለኛ የፊጥኝ ታስረው በጥይት ተደብድበው ተረሽነዋል። ለሀገሬው ነዋሪ ክብር እና ሉአላዊነት ልጅነታቸውን በቀበሮ […]

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *