“Our true nationality is mankind.”H.G.

አሜሪካ ‘ ትግራይ’ ሩሲያ በአፍሪካ ቀንድ

ልጅ ግሩም ፌስ ቡክ የተወሰደ
በአፍሪካ ቀንድ እርስ በእርስ በተያያዙ በርካታ የጥፋት ግጭቶች እና ጦርነቶች የተጎሳቆለና የተቸገረ አካባቢ ነው። አለመረጋጋት የሰፈነበት እና ሽብርተኝነት የሚስፋፋበት እጅግ አደገኛ የአፍሪካ ክፍል ነው። የአፍሪካ ቀንድ በሰፈሩት በአለማችን ታላላቆች የሚባሉት ኃይሎች መካከልም ፉክክር እያስከተለ ወደ አለመረጋጋት የሚመራና በሀገራችን ውስጣዊ ውጥረትን የሚያባብስ እንዲሁም ለረዥም ጊዜ አካባቢያዊ አለመረጋጋትን ሲያስከትል ቆይቷል። የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ከባህረ ሰላጤ ሀገሮች ጋር ያላቸውን ያልተመጣጠነ ግንኙነት ቀጣናው እንዳይረጋጋም አድርጎታል። የአፍሪካ ቀንድ ካለው ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ ዓለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ ትኩረት አግኝቷል። ጂቡቲ ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ከፈረንሳይ ፣ከጣሊያን ፣ከስፔን፣ ከቻይና፣ ከጃፓን፣ ከሳዑዲ አረቢያ፣ ከደቡብ አፍሪካ ሌሎች ሃያላን ሀገሮች የተውጣጡ እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ የወታደራዊ ኃይሎች መናሃሪያ የባህር በር ሆናለች።
በ20ኛው ክፍለ ዘመን አሜሪካ እና ሶቪዬት ህብረት በአፍሪካ ስትራቴጂካዊው ቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር እና ወታደራዊ ቁጥጥርን ለመጨመር ከፍተኛ ውድድር አካሂደዋል። ከቀዝቃዛው ጦርነት ማግስት የሶቪዬት ህብረት ድንገተኛ ውድቀት ሩሲያ በአፍሪካ የነበሯትን ዘጠኝ ኤምባሲዎችን፣ አራት ቆንስላዎችን እና በርካታ ባህላዊ ማዕከሎ እንድትዘጋ አድርጓት ነበረ። የሶቪዬት ህብረት ውድቀት የአሜሪካንን የአፍሪካ ቀንድ የበላይነት አስከተለ። የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግስት መፍረስ እና ከዚያ በኋላ የተከሰተውን የእርስ በእርስ ጦርነት ተከትሎ አሜሪካ በሶማሊያ ወታደራዊ ዘመቻን አሰማርታም ነበረ። በተጨማሪም እ.ኤ.አ. በ1998 ናይሮቢ እና ዳሬሰላም በሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ በነበረው የቦንብ ፍንዳታ እና እ.ኤ.አ. መስከረም 11 ቀን 2002 በኒው ዮርክ በተፈፀመው የሽብርተኝነት ጥቃት አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ አል ሼባብና የመሳሰኩ ቡድኖችን ለማጥፋት እንድትዋጋ ተገዳ ነበር። የዳርፉር ግጭት፣ የሶማሊያ የእርስ በእርስ ጦርነት፣ በባህረ ሰላጤው እና በየመን የባህር ወንበዴዎች ምክንያት አሜሪካ በ2001 በጅቡቲ የአሜሪካ ወታደራዊ ካምፕ እንድትከፍት ምክንያት ሆኗል። የአሜሪካ አውሮፕላኖች እና በተለይ ተዋጊ ድሮኖች በየመን እና በሶማሊያ አልሼባብ ላይ ያለሙ ጥቃቶችን ያደርጋሉ።
<ለትግራይ የተሰጠው ትኩረት>
ከቅርብ አመታት ወዲህ የአፍሪካ ቀንድ በአዲስ መልኩ ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ከፍተኛ ትኩረትና ጠቀሜታ አግኝቷል። ሩሲያ ባለፉት አስር ዓመታት ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት ጋር የነበራት የንግድ ልውውጥ አድጓል። የሩሲያ ጦር በአፍሪካ ቀንድ በተባበሩት መንግስታት ለሚመራው የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ትልካለች ነው። እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2018 (እ.ኤ.አ.) ሞስኮ የሩሲያ የባህር ኃይል ቀይ ባህር ላይ ወታደራዊ እና የባህር ላይ ሎጂስቲክስ ማዕከል ለማቋቋም በማሰብ በልዑካኖቿ ለኤርትራ መልዕክት አቅርባ ነበረ። በቪላድሚር ፑቲን ፕሬዝዳንትነት ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደገና በማደስ በአህጉሪቱ ላይ ለስላሳም ሆነ ጠንካራ ሀይልን እንደገና መጀመር ጀምራለች። ባለፈው ወር ሩሲያ የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ ማስታወቋ የሚታወስ ነው።
በቅርቡ የአሜሪካ ምክር ቤት አባል የሆኑትና የአሜሪካ መሪ ጆ ባይደን የቅርብ ወዳጃቸው እንደሆኑ የሚነገርላቸውን ሴናተር ክሪስ ኩንስ በትግራይ ስለደረሰው ሰብአዊ ቀውስና አጠቃላይ ሁኔታ፣ ከሱዳን ጋር ስላለው የድንበር ጉዳይ መግለጫ ሲሰጡ አሜሪካ ለትግራይ ህዝብ የምትጨነቅ ቢመስሉም የበለጠ ግን አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያላትን የበላይነት ለማስጠበቅ እተየጋች መሆኑን የሚያጋልጥ መልዕክት አስተላለፈው ነበረ። “…. we will work with our Gulf allies Egypt…. to stabilize the Horn of Africa and stop our enemies like Russia and Iran from getting into the region” ትርጉም (…. ከባህረ ሰላጤ አጋሮቻችን ከግብፅ ጋር እንሰራለን …. የአፍሪካ ቀንድን ለማረጋጋት እና እንደ ሩሲያ እና ኢራን ያሉ ጠላቶቻችን ወደ ቀጣናው እንዳይገቡ እናስቆማለን) ብለዋል።
አብይ አህመድን እና ኢሳያስ አፈወርቂን አምባገነን መሪዎች ብለውም ፈርጅዋቸው ከስልጣናቸው መውረድ እንዳለባቸው የሚጠቁም አነጋገር አሰምተዋል። ለዚህም መነሻው ከቅርብ ቀናት በፊት የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ መግባታቸው የ ጆ ባይደንን መንግስት ማስቆጣቱ አንድ ምክንያት ነው። አሜሪካኖች የሚሉትን ያህል ስለ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ጦርነቱ ስላስከተለው ጥፋት የሚጨነቁ ሳይሆኑ በአፍሪካ ቀንድ እንደ ሩሲያና ቻይና ካሉ ሌሎች ሃያላን የኢትዮጵያ አጋር ሀገሮች ጋር ያላቸውን ፉክክር ለማሸነፍ እየተጠቀሙበት ያለ ሰበብ ነው። ከብዙ አመታት ልምዶች እንዳየነው አሜሪካ በእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች በስለላ ድርጅቷ በሲ. አይ. ኤ.
በኩል የኤርትራንና በተለይ አብይ አህመድን ከስልጣናቸው በሃይል ለማስወገድ የሚቻላቸውን ሁሉ ሊያያደርጉ እንደችሉ እና አያድርሰው እንጂ ምናልባትም ቢሳካላቸውም እንግዳ ሊሆንብን አይገባም።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሻለቃ ሰከን ይበሉ እንጂ! – ባይሳ ዋቅ-ወያ
0Shares
0