“Our true nationality is mankind.”H.G.

ኢትዮጵያን የምታለቅሰው በ”መሪዎቿና በውድ ልጆቿ” ነውና !! ጆሮ ያለው ይስማ!!

Ethiopie, juni 2000 Grensconflict, oorlog tussen Ethiopie en Eritrea. Photo: Petterik Wiggers/Hollandse Hoogte Ethiopia, june 2000 War between Ethiopia and Eritrea. Near Zalambessa, recaptured by Ethiopian Forces. The Ethiopians are retreating due to a shaky peace agreement. The army has enough trucks for transportation while in the Ogaden desert people are starving. Captured Eritrean tanks by the Ethiopian army. War between Ethiopia and Eritrea. Near Zalambessa, recaptured by Ethiopian Forces.

ኢትዮጵያዊ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪያችንን
… ሆኖም ሀገራችን ከውጭም ከውስጥም በጠላቶች በተወጠረችበት በዚህ ጊዜ ችግሮቻችንን ለመፍታት በአንድ ላይ መቆምና መተባበር እንደሚያስፈልገን ነጋሪ አያሻውም። በምንወስዳቸው ርምጃዎችና የኢኮኖሚውን ፈተናዎች ለመቅረፍ በምናደርገው ጥረት ሁሉ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን። 
መንግስት

“የኢትዮጵያን ጥንካሬና ልዕልና ላለማየት የተሳሉ ብዙዎች የቻሉትን ጫና ሁሉ እያጎረፉት ነው” በሚል በማጠቃለያው የቀረበው ሃረግ ልብ የሚያም የሆነባቸው ጥቂት አይደሉም። መንግስት እከሌ ከከሌ ሳይል በጥቅሉ ኢትዮጵያን ለመቅበር ጉድጓዱ በየአቅጣጫው እየተማሰ እንደሆነ ግን በግልጽ ተናግሯል።

ዛሬ የብሔራዊ ማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ያሰራጨው መግለጫ ከላይ ተስፋዎችን አሳይቶ ሲያበቃ አገራችን ላይ ሊሆን የታሰበውን ባይገልጽም እግር ተወርች መያዟን አመልክቷል። በመላው አገሪቱ መልኩን እየቀያየረ የሚካሄደው ትርምስና ሁከት አገራችንን ቋንጃዋን ለመበተስ፣ ልቧን ለመነረትና እንደ አገር እንዳትቀጥል የታለመ፣ አብልታ፣ አጠጥታ፣ ተባያቸውንና እድፋቸውን ሳይቀር አጥባ ያሳደገቻቸው ልጇቿ በየአቅጣጫው ተሽጠው ሞቷን እንዲያፋጥኑ የተደረገበት ነው።

በወሳኝና ባለቀ ሰዓት ኢትዮጵያና ህዝቧ ላይ ክህደት በመፈጸም የምትታወቀዋ አሜሪካ ፍላጎቷ በግልጽ ምን እንደሆነ ባይታወቅም ካራ ስላለች። ለኢትዮጵያ አንዳችም በጎ ነገር የሌላት የግፍ ሁሉ ማማ የሆነችው እንግሊዝ ሌት ተቀን በንዳ ፈልፍላ መከራችንን ታሳየናለች። የጽዮናዊያን ጭፍራና ባሪያ የሆኑ አገሮች ሰልፋቸውን አሳምረው እየተቀባበሉ ሞት እያወጁብን ነው።

የታሪክና የሃብታችን ዘራፊዎች የሆኑት ግብጾች ለተሸጡበት አረቦች ላይ የማሴርና የመቆለፍ ተልዕኳቸውን መደራደሪያ በማድረግ መስዋዕት እንድንሆን ተደራድረውብናል። ከርሳቸው፣ ካዝናቸውና ሰፈራቸው በሃብት ቢጥለቀለቅም፣ የአዕምሮ እከክ፣ የህሊና ድርቀትና ታሪካዊ ውርሳቸው በሆነው ባንዳነት የሚሰቃዩ እንግዴዎችን ገዝተውብናል።

Related stories   ሻለቃ ሰከን ይበሉ እንጂ! – ባይሳ ዋቅ-ወያ

ግብጾች የሚባሉት ጉድፎች የቀጠሩብን የኢትዮጵያ ልጆች ” እበትም ልጅ ይወልዳል” እንዲሉ እነሱም ሌሎችን ገዝተው ያርዱናል። ያሳርዱናል። በገሃድ አታራማሾችን እየፈለፈሉ ያነዱናል። ከሁሉም በላይ የሚገርመው ስንነድ፣ ስንሞት፣ ስንሰቀል፣ ስንወገር፣ ስንፈናቀል፣ ስንሰደድ … ጉዳዩን እንደማያውቅ ሆነው ፊልም እያሰራጩ አንዱን በአንዱ እየነሳሱ መከራችንን አራዝመውታል።

ዛሬ ሳይሆን ቀደም ሲል ዛሬ ካሉበት በረሃ ሆነው ሲውተረተሩ ” በሁለት ቢላዋ የሚበሉት” ዲቃሎቻቸው መካከላችን ሆነው ይወጉን ነበር። ስንቅና ድጋፍ እያዘጋጁ መካከላችን ሆነው ያፈርሱን ነበር። አብረውን እየበሉና እየጠጡ ያርዱን ነበር። እድሜ ለሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ያሏትን ጀነራሎች ሆን ተብሎ እንዲከሽፍ ተደርጎ በተዘጋጀ መፈንቅለ መንግስት ወጥመድ ከቶ አስበላቸው። አገራችን በማይሆኑትና በማይመጥኗት ክፉዎች እጅ ወደቀች። እንግሊዝና አሜሪካ ሌት ከቀን በክህደትና በሴራ አገራችንን በብሄር በልቶ እንድትጠፋ ለሰራት ቡድን አስረከቧት።

ዘር ሳይለይ የገራችን ሰራዊት እንደ ባዕድ ተቆጥሮ ለማኝ ሆነ። መለዮ ለባሽ መሆን አሳፋሪ እስኪሆን ድረስ በምድራቸው ተዋረዱ። ልጆቻቸው ሳይቀር የሚማሩበት ህጻናት አምባ ተዘጋ። ጀግና አገር ወዳዶች አካላቸው ጎድሎ እንዲያገግሙበት የተመሰረተው ጀግኖች አምባ ታጠፈ። እንደ ቅኝ ገዢ አገራችንን በብሄር ለይተው አባሉን። የቆየ አፈ ታሪካና መላምት በጀት መድበው በማራገብ አንድ ትውልድ አነተቡ። በጥላቻ መርዝ የታጨቀ ትውልድ አምረተው አገራችንን ዛሬ ላለችበት መከራ ዳረጓት።

Related stories   ሕዝብን ማን ይሰራዋል?

የዘረፉትን እየረጩ፣ ከተሸጡበት እየቆረሱ የነውጥ ሃይል በመፈልፈል በሁሉም መንገድ ፈተኑንን። እየተናነቀን ከንፈራችንን ነክሰን ብንቆይም አልሆነም ዳግም ካዱን። ሃያ ሶስት ዓመት በጉድጓድ ውስጥ ድንበር፣ በተለይም እነሱን ሲጠብቅ የበረውን ሰራዊት አረዱት። ሳያስበው ከፋፍለው በሉት። ስጋውን ቆራረጡት። የሱእቶቹን ጡት በጥሰው ጣሉ። አስከሬን ላይ ጉልበታቸውን አሳዩ። መሳሪያ የጣለ ወገናቸው ላይ ታበዩ። ክፉ አደረጉ። ላብቃ !! በደልን ተበድለን፣ ተገፍተንና ተከድተን ስለነበር ተገደን በገባንበት ጦርነት በፈጣሪ እርዳታ አመድ አደረግናቸው። እነዛ ክፉ መሪዎቻቸው ሲወጉን እንደነበረው ግንባራቸው ተወጋ። ዘመነ ለቅሶና ድራማ ተጀመረ!

እኛ ግን ምንድን ነን?

ይህን ሁሉ ሆነን ስናበቃ ዓለም ከጎናችን ሊሆን ሲገባው ካደን። ይባስ ብለው በግልጽ ባልተቀመጠ የድለላ ፖለቲካ ሊያጠፉን ተነሱ። በሁሉም አልሆን ሲላቸው አንድ ነብሰ ገዳይ መደቡብን። ገና ስራውን ሳይጀምር ዛተብን። ካልተደራደራችሁ እየተባለን ነው። ወገኖቻችንን ያረዱትን መስልሰው ሊጭኑብን እጅ ጥምዘዛ ላይ ናቸው። ይህ ሁሉ አደጋ አልገባ ብሎን እኛ እንባላለን።

” የቤታችንን በቤታችን” እንዳናደርግ አደባባይ ውጥተን እንታኮሳለን። በሳንጃ እንጫረሳለን። የተረፈውን በእሳት እናጋያለን። መጨረሻችን ምን ሊሆን እንደሚችል ወገግ ብሎ እየታየን አንድ መሆን አልቻልንም።

ወያኔ የሚባለው ጉድ ለሃሰት ድራማ በጀት በጅቶ፣ ተውናይ ቀጥሮ ዓለምን ሲያነሳሳና የሃሰት ትርክቱን እውን ሲያደረግ፣ እኛ በመከላከያ ደም ላይ ቁማር እንጫወታለን። ፍጹም በሚያሳፍር ደረጃ በወያኔ ፕሮፓጋንዲስቶች አሸንዳ ውስጥ እንፈሳለን።

Related stories   ሕዝብን ማን ይሰራዋል?

ሻለቃ ዳዊትን አንድ የመድረክ ላይ አነጥናጭ ተከፋይ አናገረ ብለን እናብዳለን። ይህ ከሃጂ የተናገረውን እያራገብን አገራችን ላይ ሸምቀቆ እናጠብቃለን። እራሱን “ሌባ፣ ስኳሩ አታለለኝ” ብሎ በአደባባይ መቶ ሃያ ሚሊዮን ሕዝብ ፊት ራሱን ሰድቦና ንቆ እስር ቤት የተጣለ አሽከር ቃለ ምልልስ ተደረገለት ብለን ቁጭ ብለን እንጋታለን።

መጽሃፍ ቅዱስ እየሳዩ የዛርና የውቃቢ ፖለቲካ ለሚሰብኩ ለምደኞች ጊዜ በመስጠት ልቡናችንን እንሳውራለን። ለቧልትና ክህደት ጆሯችንን በርግደን ስለከፈትን መልካም ነገር መስማትና መረዳት አልቻልንም። ቢአይን ራስን ምክንያታዊ አድርጎ መጠየቀና መመርመር ሲገባን የተነገረንን ሁሉ ቀኑንን ሙሉ እየተጋትን፣ ሃሜትና ክፋትን መለቃቀም ሱስ ሆኖብናል። ሱሱ ጥንቶብን አገራችን እያቃሰተችም መስማት አልቻልንም።

ተውደደም ተጠላም ዛሬ ጊዜው አገርን የማዳን ነው። መንግስትም ሆነ ማንም ከግሉ ይልቅ አገር ልትድን የምትችልበትን መንገድ ነው ማስቀደም የሚገባቸው። ህዝብም ቧልትና ተራ ትርክት፣ እንዲሁም የተገዙ የሚሰጡትን አጀንዳ በመተው ልቡን፣ አካባቢውን፣ ቀዬውን ሊጠብቅ፣ ለአገሩ ሁሉም ዓይነት ወታደርና ሰላይ ሊሆን ግድ ነው።

ዛሬ በቀበሌአን በሰፈር ተቧድኖ መፏከት አቁሞ፣ በሰፈርና በቀበሌ ተቧድኖ አገር መጠበቅ። ሊመጣ ያለውን ችግር መጋፈጥና አባቶቻችን ያደረጉትን በማድረግ አገር ለማቆየት መረባረብ ያስፈልጋል። ልብ ይስጠን። አገር የምታለቅሰው በመሪዎቿ በኩል ነውና ስማ!!

ሞገስ ጥግነህ

ጸሃፊውን በዝግጅት ክፍሎ አድራሻ ማግኘት ይቻላል።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0