“Our true nationality is mankind.”H.G.

“የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች በከተማዋ አስተዳደር ስር ባሉ የጤና ተቋማት በሙሉ ነፃ ህክምና እንዲሰጥ መወሰኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።

የከተማ አስተዳደሩ 80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን ምክንያት በማድረግ ከነፃ ህክምና አገልግሎቱም በተጨማሪ ጀግኖች አርበኞች ማህበር የጠየቀው መሬት እንዲሰጠው መወሰኑንም ምክትል ከንቲባዋ ማስታወቃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

በበአሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጣልያን ኢትዮጵያን ዳግም ለመውረር ጥረት ባደረገበት ጊዜ ጀግኖች አባቶች እና እናቶች አይበገሬነታቸውን ያስመሰከሩበትን ድል የሚታሰብበት በዓል ነው ብለዋል።

Related stories   የሲኤንኤን ዘጋቢ ኒማ- በተወነችው ተውኔት ውስጥ ዳግም ሞት የተፈረደባቸው ዜጎች

ጣልያን ኢትዮጵያውያንን በዘር፣ በኃይማኖት እና በአካባቢ የመከፋፈል ሴራ ተጠቅሞ ኃይላችንን በማሳነስ ድል ለማድረግ ሙከራ አድርጎ የነበረ ቢሆንም፤ ጀግኖች አርበኞች የጠላትን ሴራ ቀድመው በመረዳታቸው ውጥኑ ሊከሽፍ እንደቻለ ወይዘሮ አዳነች አስታውሰዋል።

ጀግኖች አርበኞች ባደረጉት ማስተዋል የተመላበት ትግል ትውልዱ አንገቱን ቀና አድርጎ የሚሄድባት፣ የሚኮራባት አገር እንዲኖረው አድርገዋልም ነው ያሉት።

ኢትዮጵያውያን ከጀግኖች አርበኞች መማር ያለባቸው የጠላትን የመከፋፈል ሴራ በማስተዋል እና አንድነትን ማጠናከር መሆኑንም ገልጸዋል። በስነ-ስርአቱ ላይ ወጣቶች ፉከራ እና ሽለላ ያቀረቡ ሲሆን የማርችባንድ ትርኢትም ቀርቧል።

Related stories   ኤፒ ለቅጥፈቱ ይቅርታ አልጠየቀም – ምርጫ ተራዘመ፤ለምን?

የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለ80ኛ ዓመት የአርበኞች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ፕሬዚደንቷ በመልዕክታቸው፤ የጥንት ኢትዮጵያ አርበኞች አገራችን ነጻነትዋን ጠብቃ እንድትኖር አድርገዋል ያሉ ሲሆን፤ ዛሬም አገርን ለመጠበቅና ለመገንባት አርበኝነት ከሁላችንም ይጠበቃል ብለዋል፡፡ ያለፈውን ጀግንነት የምናቆየው ለዚህ ከተነሳን ነው ሲሉም በትዊተር ገጻቸው መልዕክታቸውን አስፍረዋል፡፡

 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0