ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

የወ/ሮ እጅጋየሁ ቃለምልልስና አስገራሚ አስተያየቶች እንደወረዱ!!

የወ/ሮ እጅጋየሁ ቃለ ምልልስ ከቁምነገር መጽሔት ጋር

 Posted by DejeS ZeTewahedo

በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክህነት አካባቢ እንደ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ አወዛጋቢ ሴት የለም፡፡ ወ/ሮ እጅጋየሁ የዝነኛው ድምፃዊ የማህሙድ አህመድ የቀድሞ ባለቤት ናቸው፡፡ ከድምፃዊው ጋር የፍርድ ቤት የፍቺ ጣጣቸው ገና አልተቋጨም፡፡ ዝነኛውን ማህሙድ ሙዚቃ ቤትን ሽጠው ብሩን ተካፍለውታል፡፡ “ እሱ ነው ይሸጥ ያለው” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ ወ/ ሮ እጅጋየሁ ከፓትሪያርኩ ጋር ስማቸው አብሮ ይነሳል፤ “ፈላጭ ቆራጭ እርሳቸው ናቸው” በሚል፡፡ ቁም ነገር መጽሔት ያተመው የሴትየዋ አስገራሚ ቃለምልልስ በከፊል ይህን ይመስላል፡፡

ጥያቄ፡- በነገራችን ላይ ወ/ሮ እጅጋየሁ እድሜሽ ስንት ነው?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- እግዜአብሄር ይመስገን 66ኛ ዓመቴን ጨርሻለሁ
ጥያቄ፡- ወደ ቅዱስ ፓትሪያርኩ ጋር እንዳትገቢ አልተባልሽም?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- በፍጹም፡፡ ማንም አላለኝም፡፡ አሁን ያልከው ጉዳይ በወቅቱ አንድ ጋዜጣ ላይ ተጽፎ አንብቤያለሁ፡፡ ከዚያ በፊት እውነተኛ ነገር ነው የሚዘግበው ብዬ የማስበው ጋዜጣ ነበር፡፡ ነገር ግን የሌለና ያልተደረገ ነገር መጻፉን ስመለከት ወደ ክስ ከመሄድ ይልቅ አዝኜበት ነው የተውኩት፡፡
በመጀመርያ ደረጃ ቤት ክህነት የምገባው እኔ ብቻ አይደለሁም፡፡ ብዙ ሴቶች ይገባሉ፡፡ እኔ ግን የትና ማን ጋር እንደምገባ ይታወቃል፡፡ የማንም ደላላና ወሬ አቀባይ አይደለሁም፡፡ ይህንን ላረጋግጥልህ እችላለሁ፡፡ ይህንን ለማድረግ እድሜዬ፣አስተዳደጌ፣ ሃይማኖቴ አይፈቅድም፡፡ በሁለት ቢላ የምበላ ሴት አይደለሁም፡፡ እኔ የምገባበት ቦታ የታወቀ ነው፡፡ ሽፍንፍን የለውም፡፡ እግዜአብሔር የመረጣቸው ከእስር ቤት አውጥቶ ከስደት መልሶ መርጦ “ልጄ አንተ ነህ፤ ወንበሬም ያንተ ነው” ብሎ ያስቀመጣቸው ብፁዕ ወ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጋር ነው የምገባው፡፡ የምገባው ከእርሳቸው ቡራኬና በረክት ለማግኘት ነው፡፡ እንደማንም ወሬ ላመላልስ አይደለም የምገባው፡፡ ይሄ የታወቀ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ ስለ እኔ በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ የተነሳ ነገር የለም፡፡

ጥያቄ፡- የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች በአባቶች መሀል አለመግባባት እንዲፈጠር የምታደርገው እሷ ነች ይላሉ፡፡

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- የምትለውን ማኅበር እኔ አላውቀውም፡፡ የጽዋ ማኅበር ይሁን ወይም ሌላ እኔ አላውቀውም፡፡ የማኅበረ ማርያም፣ ማኅበረ ግሸን የሚባል አውቃለሁ፡፡ ራሱን ቅዱስ ብሎ የሚጠራ ማኅበርን ግን አላውቅም፡፡ አሉባልታን የሚያናፍሰው የአጋንንት ማኅበር ካልሆነ ማን ሊሆን ይችላል? ሃይማኖት ያለው ሰው አሉባልታ ላይ ጊዜ አያጠፋም፡፡  እኔን እዚህ እንዳልገባ ሊከለክሉ የሚችሉት ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ብቻ ናቸው፡፡

ጥያቄ፡- በነገራችን ላይ ከብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ጋር ዝምድና አላችሁ እንዴ?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- የለንም፡፡ በመጀመርያ ደረጃ ዝምድና የሚባል ነገር ከእርሳቸው ጋር የለኝም፡፡ ዝምድናው ባይኖረኝም ግን የመንፈስ ቅዱስ አባቴ ናቸው፡፡ እንደማንኛውም ሰው ቀርቤ አይቻቸዋለሁ፡፡ የዋህ፣ ቅን፣ ሩህሩህ፣ ደግ፣ ይቅር ባይ፣ ሐሰት በአንደበታቸው የማይዞር አባት መሆናቸውን ነው የተረዳሁት፡፡ ካለቀሰው ጋር ሁሉ የሚያለቅሱ፣ ሩህሩህ አባት መሆናቸውን አውቃለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የእኚህ አይነት አባት ማግኘቷ ራሱ ትልቅ በረከት ነው፡፡

ጥያቄ፡- የእቅዴን ያህል ሰርቻለሁ ትያለሽ?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- እግዜአብሔር ይመስገን፡፡ እግዜአብሔር በረዳኝ መጠን የተቻለኝን ያህል ድጋፍ አደርጋለሁ፡፡ ሰዎችን እረዳለሁ፡፤ ከዚህ በፊት 64 ኪሎ ግራም እጢ ለ22 ዓመት ማህፀኗ ውስጥ ይዛ የኖረችን ሴት ከሰውነቷ ውስጥ እንዲወጣ አድርገናል፡፡ ያለ ፊንጢጣ የተወለደች ልጅንም ረድቻለሁ፡፡ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን በተቻለኝ አቅም ለመስራት እሞክራለሁ፡፡ በምድረ ከብድ አቡዬ ገ/መንፈስ ቅዱስ ገዳም ብትሄድ በግል ገንዘቤ ለጳጳሳት ማረፊያ 12 ክፍል ቤት ሰርቻለሁ፡፡ ትልቅ አዳራሽም አለው፡፡ ብፁዕ አባታችን ናቸው ባርከውና ቀድሰው ስራ ያስጀመሩት፡፡ ሰከላ አቡዬ ገ/መንፈስ ቅዱስ ገዳምም እንደዚሁ ቆርቆሮ አልብሻለሁ፡፡ ባህር ዳርም ቤዛዊት ማርያም የአቅሜን ሰርቻለሁ፡፡ ሰዎችን በማስታረቅም የማምን ሰው በመሆኔ የተቀያየሙትን ሁሉ ሰብስቤ አስታርቃለሁ፡፡ በብፁእ አባታችን ላይ መጥፎ ነገር ሲናገሩ የነበሩ ሰዎችን ሳይቀር አስታርቃለሁ፡፡ ተቧድነው የሚናከሱትን ሁሉ ይቅር እንዲባባሉ አድርጌያለሁ፡፡ እሳቸውም ይቅር እንዲሏቸው አድርጊያለሁ፡፡

ጥያቄ፡- ቢሮሽ የቤተ ክህነት ነው፡፡ ማን ነው የሰጠሸ? ፓትሪያርኩ ናቸው?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- ብፁእ አባታችን አስከዛሬ ድረስ ይሄ ይደረግልኝ ብያቸው አላውቅም፡፡ እሳቸውም ሰጥተውኝ አያውቁም፡፡ ወሬው ግን ቀድሞ ይወራል፡፡ አሁን ያለሁበት ቢሮ የቤተ ክህነት ቤት ነው፡፡ ጨረታ ሲወጣ ተጫርቼ ነው፡፡

ጥያቄ፡- መኖርያ ቤቱስ?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- ሥላሴ ጋር ያለው ቤት የእኔ አይደለም፤ የልጄ ቤት ነው፡፡ እሱንም የዛሬ ስንት ዓመት የወደቀ የፈራረሰ ቤት ስለነበረ 284 ሺህ ብር ወጪ አድርጌ ሰርቪስ ሰርቼ፣ አሳድሼ አጥር ሰርቼ ነው ልጄ እየኖረችበት ያለቸው፡፡

ጥያቄ፡- ማን ሰጠሸ፤ ፓትሪያርኩ አይደሉም?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- የዚያን ጊዜ እንዲያውም ከፓትሪያርኩ ጋር አንተዋወቅም፡፡ የሰጡኝ ብፁእ አቡነ ቄርሎስ ናቸው፡፡ ከዚህ ውጭ የተሰጠኝ ቤት የለም፡፡

ጥያቄ፡- በቤተክህነት ግቢ ውስጥ እጅሽ ረጅም እንደሆነ ይገለጻል፡፡ በእርግጥ የእጅሽ ርዝመት ምን ያህል ነው?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- በጣም ጥሩ፡፡ ይገርማል ይህ አባባል እኔን እራሴን አንዳንዴ ብቻዬን ቁጭ ብዬ ያስቀኛል፡፡

ጥያቄ፡- በቤተ ክህነት ሥልጣንሽ ምንድነው?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- ምንም ሥልጣን የለኝም፡፡

ጥያቄ፡- የቤተክህነቱ ሠራተኛ ነሽ?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- አይደለሁም፤ እኔ ቤተክህነት ምንም ነገር የለኝም፡፡ አባቴ ግን ትልቅ አባት መሆናቸውን አምናለሁ፡፡ አባቴ የክርስቶስ እንደራሴ ናቸው፡፡ መከበር አለባቸው፡፡ አትንኩዋቸው ነው የምል፡፡

ጥያቄ፡- ለመጀመርያ ጊዜ ቅዱስ አባታችንን ያወቅሻቸው መቼ ነበር?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- ቅዱስ አባታችንን ለመጀመርያ ጊዜ ያየኋቸው ፓትሪያርክ ሳይሆኑ በፊት ነው

ጥያቄ፡- የት?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- አሜሪካ ሎሳንጀለስ

ጥያቄ፡- እዚያ እያሉ ውዝግብ ገጥሟቸው ያውቃል?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- ያኔማ አባታችን አባታችን ነው የሚባሉት፡፡ የተከበሩ ልዩ አባት ናቸው፡፡ የሎስአንጀለሷን ማርያም ያቋቋሙት እሳቸው ናቸው፡፡ አሜሪካ ሰባት ቤተክርስቲያናት አቋቁመዋል፡፡

ጥያቄ፡- እዚህ ከ200 በላይ ቤተ ክርስቲያን ማሰራታቸው ይነገራል

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- የዚህማ ምኑ ተነግሮ፡፡ ምን ያልሰሩት አለ…ልማቱስ…ግንባታውስ…ት/ቤቱስ…ድሮ ቄስ የረባ ደሞዝ አልነበረውም፡፡ ዛሬ የምታየው ከሺህ ብር በላይ ደሞዝ የሚከፈለው ቄስ ሁሉ ድሮ ወይ በጤፍ ወይ በሰላሳ ብር ብቻ ነበር የሚያገለግለው፡፡

ጥያቄ፡- ብዙ የሠሩትን ያህል ብዙ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- ጻድቅ ሰው ይዋረዳል፡፡ ይሰደባል፣ ጌታ እየሱስ ክርስቶስም ያን ሁሉ መከራ የተቀበለው እያገለገለ ጥሩ ስራ እየሰራ ነው፡፡

ጥያቄ፡- ለአባታችን ሀውልት የማቆሙን ነገር ከጠነሰሱት ውስጥ አንዷ አንቺ…

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- ዛሬ ይህን ጥያቄ በመጠየቄ በጣም ደስ ይለኛል፡፡ ይህን ጥያቄ ነበር እኔ ያጣሁት፡፡ እውነቱ እንዲወጣ እፈልጋለሁ፡፡ በመጀመርያ ደረጃ ቅዱስ አባታችን ሀውልት ይሰራላቸው ብዬ ያመነጨሁት ሐሳብ የለኝም፡፡

ጥያቄ፡- የማን ሐሳብ ነው ታድያ?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- ቃሊቲ ያለችው ቁስቋም ማርያም ፅላቷ ለጥምቀት ከወጣ በኋላ አልገባም ብሎ አልመለስም አለ፡፡ ለብዙ ጊዜ ተቀምጦ ሕዝቡ በምህላ በለቅሶ በጭንቀት ላይ ነበር፡፡ በኋላ ቤ/ክ አሰራለሁ ብለው መሰለኝ አንድ ሰው ሰሩ፡፡ እሱ ከተሰራ በኋላ አሁንም ማስገባት አልተቻለም፡፡ ከብዙ ምህላ በኋላ ቅዱስ አባታችን ቦታው ድረስ ሄዱ፡፡ ያን ጊዜ “እስካሁን ያልተቻለውን አሁን እኚህ ሊያስገቡ ነው?” እያሉ የተቹ ነበሩ፡፡ በአንድ ቡራኬ ነው፡፡ ድፍት ብለው ወድቀው ጸሎታቸውን ካደረሱ በኋላ ብድግ አድርገው |ፅላቱን ያስገቡት፡፡

በዚህ ምክንያት እዚያ ያለው ሕዝብ በሙሉ “ሐውልት ሊሰራላቸው ይገባል፤ በሕይወት እያሉ ተቀርፆ ማየት አለባቸው” ብሎ ተነሳ እንጂ እኔ ያመጣሁት ሐሳብ አይደለም፡፡ እኔ ያመጣሁት ሳንቲም የለም፡፡

ጥያቄ፡- በማን ገንዘብ ተሠራ?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- ያው ሕዝብ ያዋጣላቸው ነው

ጥያቄ፡- ሕዝቡ ምን ያህል አዋጣ?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- ከአራት መቶ ሺ ብር በላይ

ጥያቄ፡- ስለዚህ ለሀውልቱ ግንባታ ውስጥ የለሽበትም ማለት ነው?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- ያን ነገር ስሰማው የሳቸውን ክብር ማየት ከማንም በላይ ምኞቴ ስለነበረ ተደስቼ በዓሉ በሚደምቅበት መንገድ ማገዝ ጀመርኩ፡፡

ጥያቄ፡- ለምሳሌ ምን በማድረግ?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- ቅዱስ አባታችን እንዳይሰሙ ሰርፕራይዝ አድርጓቸው ብዬ በአሉ ድምቀት እንዲኖረው ያማረ እንዲሆን አድርጌያለሁ

ጥያቄ፡- ቦሌ መድኃኔዓለምን ለምን ተመረጠ?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- በሳምንት ሦስቴ እየመጡ እዚያች ጭቃ ላይ ቁጭ እያሉ ከኪሳቸው ገንዘብ እያወጡ በሬ እያረዱ ያሰሩት ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ነው የመረጥነው።

ጥያቄ፡- ሀውልቱ ከምንድነው የተሰራው?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- አምስት መቶ ዓመት መቆየት በሚችል ፋይበር በሚባል ነገር ነው የተሰራው

ጥያቄ፡- ስለሀውልቱ መቆም አባታችን ምንም አያውቁም ያልሽ ኝ መሰለኝ

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- መድኃኔዓለም ምስክሬ ነው፡፡ እመቤቴን እልሀለሁ፡፡ ምንም ነገር አያውቁም

ጥያቄ፡- የመረቁት ግን እሳቸው ናቸው?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- ጉዳዩን ሳያውቁት ነዋ የተጠሩት

ጥያቄ፡- እንዴት?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- ሲጠሩ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀናቸው ተማሪዎች ስላሉ ይምጡና ይመርቁልን ብለዎታል ተብለው ነው የተጠሩት፡፡

ጥያቄ፡- አላወቁማ?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- ምንም የሚያውቁት ነገር የለም

ጥያቄ፡- ሲያዩት ምን አሉ

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- መጡ፤ የእውነት ለመናገር ከመጡ በኋላ ሪቫኑን በመቀስ ቆረጡ ከዚያ የተሸፈነውን ክፈቱት አልናቸው፡፡ ሲከፍቱት በጣም ደነገጡ፡፡ እንዲያውም ደንግጠው መስቀላቸውን እንዲህ አይናቸው ላይ አድርገው የተከዙበት ፎቶ ግራፍ አለ፡፡ ላሳይህ እችላለሁ፡፡ ለማስረጃ፡፡

ጥያቄ፡- ከዚያስ ምን አሉ?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- አይገባኝም ነው ያሉት፡፡ ይሄ ነገር ለኔ አይገባም ነው ያሉት፡፡ ምን ስላደረኩ፤ ማን ነኝና፤ ብለው ራሳቸውን ዝቅ ያደረጉ አባት ናቸው፡፡

ጥያቄ፡- አሁን የሀውልቱ መጨረሻ ምንድነው?

ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- ሐውልቱማ አሁንም አለ፡፡ ይኖራል፣ ይቀጥላል፡፡ የሚፈርስ ሀውልት የለም፡፡

 82 comments:
Anonymous said…
አፈር ያብላሽ መቼ?
Anonymous said…
እግዚኦ መሃረነ የውሸት ብዛት!!!!!!!!!!!!
ሰው ይህን ያህል ሲያወራ ሳት ብሎት እውነት እንኳ አይቀላቅልም?ስለሃውልቱ የማውቀው ነገር የለም አላሠራሁም ግን ደግሞ ከፋይበር ነው የተሠራው 500 ዓመት መቆየት ይችላል፣ ጳውሎስ የሃውልቱን መሠራት አያውቅም እናም የሚመርቀው ነገር ምን እንደሆነ ሳያውቅ ሪባን በጠሰ የተሸፈነውንም ገልጦ የራሱን ሃውልት አዬ – ለምን ቢባል ሰርፕራይዝ ለማድረግ፣ ከማስጠንቀቂያ ጋር ሃውልቱን ማንም አያፈርሰውም! ጳውሎስ በጸሎቱ የቃሊቲ ቁስቋምን አስገባ………. በጣም ይሰለቻል ያስባንናልም።ምን እስከሚሠሩን እንደምንጠብቅ ግን አልገባኝም።
ምነው አምላከ ቅዱሳን በቤትህ ላይ ቅንዓትህ ራቀች!

ቢንያም ዘባህርዳር

June 1, 2011 5:40 AM
samueldag said…
የሚፈርስ ሀውልት የለም፡፡ —————–አባ፡ሰረቀና፡ኤልዛቤል፡የመጨረሻ፡የጥፋት፡እጃቸውን፡እየዘረጉ፡ነውና፡አጽራረ፡፡ቤተ-ክርስቲያን፡አምላከ፡ቅዱሳን፡ያስታግስልን፡አሜን፡፡፡
June 1, 2011 6:06 AM
Anonymous said…
እውነቱ እንዲወጣ እፈልጋለሁ፡፡ በመጀመርያ ደረጃ ቅዱስ አባታችን ሀውልት ይሰራላቸው ብዬ ያመነጨሁት ሐሳብ የለኝም፡፡… እኔ ያመጣሁት ሐሳብ አይደለም፡፡ እኔ ያመጣሁት ሳንቲም የለም፡፡
.. ከኪሳቸው ገንዘብ እያወጡ በሬ እያረዱ ያሰሩት ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ነው የመረጥነው።.. … እኔ ያመጣሁት ሐሳብ አይደለም… ውይ ግኡድ

June 1, 2011 6:29 AM
Anonymous said…
ይገርማል
June 1, 2011 7:36 AM
Anonymous said…
ይገርማል
June 1, 2011 7:38 AM
Anonymous said…
qomech aligebam alech yetebalechiw tabot..ewun be abune pawlos amakagninet / biqat qidesina new yegebachiw ? deje selamawyan ebakachun mitawukutn nigerugn ……
June 1, 2011 8:12 AM
Anonymous said…
እጅግ አየሁ (እውነተኛዋ ኤልዛቤል) እባክሽን ቤ/ክህነትን ለቀቅ አድርጊልን በፈጠረሽ!!!
June 1, 2011 8:34 AM
Bewnet said…
ayachihu wushetun wushet siyagalitew yigermal ayin yawota wushet!!!!!
June 1, 2011 9:42 AM
Anonymous said…
ወይ እጅጋየሁ ሰው ሁሉ አእነንደነንቸቺወው ከእነፎርሜሽን የራቀ ይመስልሻል ወይስ እንደንቺ ማስተዋል የተሳነው፡፡
እጅግ በጣም ያሰዝናል
June 1, 2011 9:46 AM
Anonymous said…
እግዚኦ መሃረነ የውሸት ብዛት!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! ቆይ እሷ ካላሰራች (ሲሰራ ዋና ተዋናይ ካልሆነች)እነዚህን ነገግሮች እንዴት አወቀች ????
=> ስለሃውልቱ የማውቀው ነገር የለም አላሠራሁም ግን ደግሞ ከፋይበር ነው የተሠራው 500 ዓመት መቆየት ይችላል፣
=> … እኔ ያመጣሁት ሐሳብ አይደለም፡፡ እኔ ያመጣሁት ሳንቲም የለም፡፡.. ከኪሳቸው ገንዘብ እያወጡ በሬ እያረዱ ያሰሩት ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ነው የመረጥነው።የቤተክህነቱ ሠራተኛ ነሽ?…አይደለሁም፤ እኔ ቤተክህነት ምንም ነገር የለኝም፡፡
+ ሐውልቱማ አሁንም አለ፡፡ ይኖራል፣ ይቀጥላል፡፡ የሚፈርስ ሀውልት የለም፡፡
ከቤተ ከህነት መዋቅር (ከሲኖዶስ )በላይ ስልጣን አላትን ? ይህን ያህል ምነው የአባቶቻችንን ውሳኔ ሴትየዋ አቃለለችው ????ተስፋሁን (OUTE)

June 1, 2011 10:28 AM
Anonymous said…
Dejeselamawian, if ur blog allows to view personalities plz write more about who is Elizabel.
June 1, 2011 10:33 AM
Anonymous said…
“ይህንን ለማድረግ እድሜዬ፣አስተዳደጌ፣ ሃይማኖቴ አይፈቅድም… እኔ የምገባበት ቦታ የታወቀ ነው፡፡ ሽፍንፍን የለውም፡፡ እግዜአብሔር የመረጣቸው … ብፁዕ ወ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጋር ነው የምገባው፡፡ የምገባው ከእርሳቸው ቡራኬና በረክት ለማግኘት ነው፡ ይሄ የታወቀ ነገር ነው፡፡””እግዚአብሔር ኃጢአተኛን እንኳ ፊቱን ጸፍቶ፣ አፉን ከፍቶ ያናግራል” የሚባለው ነገር ዘንድሮ እየተፈጸመ ነው። ባልደረባሽ ሠረቀ ትናንት የራሱን ጉድ በራሱ ጊዜ ሲዘከዝክ ውሎ ዛሬ ደግሞ አንች በተራሽ ትቀባጥሪ ገባሽ። በጋዜጣኛ መጠይቅ እንዲህ መላቅጡ ከጠፋሽ ጥቂት ጠበል ቢረጩሽ ምን ትሆኝ ኖሯል ጃል?

በመሠረቱ አንች “ቅዱስ” የምትይው ጳውሎስ ቅድስናውን የገለጠው ላንች መሆን አለበት እንጅ የኢትዮጵያ ምዕመን እንኳን ግቢውን ሊረግጥና ሊባረክ(ነው ወይስ ሊረገም?) ድምጹንም በቴሌቪዥን ያውም ለፖለቲካ ሥራ ካልሆነ በቀር ሰምተን አናውቅም። ባፍ ጢም የሚደፋ ወታደሩና ጋሻጃግሬው የት ሄዱ እርሱ ዘንድ ልንቀርብ ይቻለናል። በዓለም ላይ ካሉ የሃይማኖት መሪዎች በህዝቡ ዘንድ የሚጠላና ከህዝቡ ጋር የማይቀላቀል ብቸኛው ሰው እነደሆነ ማን በነገረሽ። አንቺ እንዳልሽው እውነተኛ መሪ፣ ምዕመናንን የሚወድና በእኩል ዓይን የሚያይ፣ ርህሩህ… ቢሆንማ ኖሮ እሱ ዘንድ የምትገቢና የምትወጭ አንቺ ብቻ ሳትሆኝ ሁላችንም ነበርን። ይህ ደግሞ ያገኘሽው እሱም ያገኘው ጥቅም ስለመኖሩ ምን ጥያቄ ያሻዋል?

ልበ ካለሽ የቃዥሽውን መጠይቅ ዞረሽ አንብቢና ራስሽን መርምሪ። እንዳልሽው የተከበርሽ የሃይማኖት ሰው ብትሆኝስ በዚህ ዕድሜሽ ባሳፋሪ ምግባርሽ ህዝብን ባላሰናከልሽም ነበር?

ልብ ይስጥሽ።

June 1, 2011 11:03 AM
Anonymous said…
‘‘ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- ሐውልቱማ አሁንም አለ፡፡ ይኖራል፣ ይቀጥላል፡፡ የሚፈርስ ሀውልት የለም፡፡ ‘‘
ምን አይነት የትዕቢት አነጋገር ነው? ይህ የእምነቱን ተከታይ ምዕመኑን ከመናቅ የመነጨ ነው። በውኑ የቤተክርስቲያን መመሪያ የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስ አንብበው ያውቃሉ? በትዕቢት የተነፉት መጨረሻቸው ምን እንደሚሆን ማወቅ ከፈለጉ ያንብቡት። እሱን ማንበብ ካልቻሉ ደግሞ ስለ ቤተክርስቲያንን ታሪክ የሚዘክሩ መጽሐፍትን ያገላብጡ ወይም እውነተኛ አባቶችን ጠይቀው ይረዱ። ይህ እኮ የእምነት ቤት ነው። የሆነ የውስጥ አላማን ለማራመድ ሲባል ውሸት እንደ ልብ የሚዘከዘክበት ቦታ አይደለም። እንደዚህ አይነት ነገር የሚገኘው አስመሳይ ነጋዴዎች ጋር ነው። ደምበኛቸውን ለመያዝ የማይፈነቅሉት ድንጋይና የማይቀባጥሩት ነገር የለም። ቃለ ምልልሱ እንደዚያ ነው የሆነብኝ። ‘‘የማኅበረ ማርያም፣ ማኅበረ ግሸን የሚባል አውቃለሁ፡፡ ራሱን ቅዱስ ብሎ የሚጠራ ማኅበርን ግን አላውቅም፡፡‘‘ እውነት ማህበረ ቅዱሳን ራሱን ቅዱስ ብሎ የጠራ ማህበር ነው? ያልተጻፈ ማንበቡ ለምን አስፈለገዎት? ለመሆኑ አማካሪ የለዎትም? ለምሳሌ እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመረቅሁ ነኝ። በምማርበት ወቅት ይህ ማህበር መንፈሳዊ ትምህርት አስተምሮኛል። ስለማመልከው አምላክ አፌን ሞልቼ ዛሬ በምሰራበት ቦታ ሁሉ መናገር እንድችል ያደረገኝ ማህበር ነው። ባይገርምዎ ማህበሩ ባሁኑ ስዓት የት እንዳለሁ ምን እንደምሰራ እንኳ አያውቅም። እምነቱን ማወቅ የፈለገን ሰው አስተምሮ መልቀቅ። ከጓደኞቼ መካከል አባል ሆነው ቤተ ክርስቲያንን እያገለገሉ እንደሆነ አውቃለሁ። እኔ ግን ለዚያ አልታደልሁም። እናም እግዚዘብሔርን እያመለክሁ በተመረቅሁበት ሙያዩ አገሬን እያገለገልሁ እገኛለሁ። ይህም ቢሆን የህትመት ውጤታቸውን አነባለሁ። እንድም ቦታ ላይ እርስዎ እንሚሉት ይህ ማህበር እራሱን ቅዱስ ብሎ አያውቅም። ለመሆኑ እንዲህ ባደባባይ ደረቅ ውሸት ይዘው ብቅ ሲሉ ቀናኢ የሆኑ የሐይማኖቲቱ ተከታዮች ዝም ብለው የሚያልፍዎት ይመስለዎታል? ለነገሩ ቃለ ምልልስ ማድረግዎ ለእኛ እጅግ በጣም ጥሩ አጋጣሚ ነው። ‘አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል‘ እንዲል። ወ/ሮ እጅጋየሁ ማን ናቸው ለሚል ማንኛውም ጠያቂ ቁምነገር መጽሔት የዚህን እትም ወይም ኮፒውን ከዚህ ዌብሳይት እንብብ ማለት ብቻ ነው። ጊዜው ሲደርስ ሁሉም እንዲህ እንደሚቀባጥር ተስፋ አለኝ። አልጠራጠርም የማመልከው አምላክ‘‘ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ‘‘ ብሎ ገርፎ እርስዎንና መሰሎቹን የሚያስወጣበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። እስከዚያው ግን የቀረዎት ነገር ካለ አሁንም ነገር በማመላላስ አባቶችን ማበላላት ይቀጥላሉ። ሲፈልጉ ደግሞ እንዲህ ወጣ እያሉ መግለጫውን ያወጣሉ። አደራ ይህን ቃለ ምልልስዎን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እንዲደግም ያድርጉት። ምክንያቱም ቁም ነገር መጽሔት የማትደርስበት ብዙ ምዕመናን ስላለ። ከጀመሩት ላይቀር በደንብ አድርገው ያራግቡት። ለሌሎች ጥሩ መማሪያ ይሆናሉና።
አምላከ ቅዱሳን ኢትዩጵያን ይባርክ።
June 1, 2011 11:10 AM
Anonymous said…
oh!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
አይፈረድብሺም ዉሸት የባህሪሽ ስለሆነ ምንም ማድረግ አትቺይም። በነገራቺን ላይ ቤተክርስቲአን የቦዘኔወች መድረክ አይደለቺም(ባለ ፈቶች ለማለት ነው)።
ሰዉን አስታርቃለሁ ብለሽ ከመዋሸትሺ በፊት ራስሽ ከባለበትሽ ጋር ታረቂ።
June 1, 2011 11:13 AM
Anonymous said…
አይፈረድብሺም ዉሸት የባህሪሽ ስለሆነ ምንም ማድረግ አትቺይም። በነገራቺን ላይ ቤተክርስቲአን የቦዘኔወች መድረክ አይደለቺም(ባለ ፈቶች ለማለት ነው)።
ሰዉን አስታርቃለሁ ብለሽ ከመዋሸትሺ በፊት ራስሽ ከባለበትሽ ጋር ታረቂ።
June 1, 2011 11:13 AM
Anonymous said…
አይፈረድብሺም ዉሸት የባህሪሽ ስለሆነ ምንም ማድረግ አትቺይም። በነገራቺን ላይ ቤተክርስቲአን የቦዘኔወች መድረክ አይደለቺም(ባለ ፈቶች ለማለት ነው)።
ሰዉን አስታርቃለሁ ብለሽ ከመዋሸትሺ በፊት ራስሽ ከባለበትሽ ጋር ታረቂ።
June 1, 2011 11:15 AM
Anonymous said…
የተወደድክ ሙሀሙድ ምኑን ቺለሀው ኖርክ? ይሄንን ሁሉ ዉሸት መቻልህ በእዉነት ታላቅ ሰው መሆንክን ያሳያል።
June 1, 2011 11:18 AM
samueldag said…
አባ፡ሰረቀና፡ኤልዛቤል፡የመጨረሻ፡የጥፋት፡እጃቸውን፡እየዘረጉ፡ነውና፡አጽራረ፡፡ቤተ-ክርስቲያን፡አምላከ፡ቅዱሳን፡ያስታግስልን፡አሜን፡፡፡
June 1, 2011 11:20 AM
Anonymous said…
በጣም ይገርማል
“በእርግጠኝነት ሐሳዊ መሰሕ ከዚህች አሮጊት ይወለዳል ለማዬት ያብቃችሁ”
አባ ተስፈ ማርያም ከ ጎንደር
June 1, 2011 12:12 PM
Anonymous said…
‘‘ራሱን ቅዱስ ብሎ የሚጠራ ማኅበርን ግን አላውቅም፡፡‘‘ማኅበረ ቅዱሳን እንዲህ አይነቱን ሰው በቸልታ ማለፍ ያለበት አይመስለኝም። ይህ ሆን ተብሎ በምዕመናን መካከል ውዥንብር ለመፍጠር የተጠነሰሰ ሴራ ነው። የስሙ ትርጓሜ ምን እንደ ሆነ ሁሉግዜም በሚወጡት ሕትመቶች ሳያሰፍር ቀርቶ አያውቅም። ሴትዮዋም ይህን በደምብ ጠንቅቀው ያውቃሉ። የማኅበሩን ስም በማጉደፍ ምዕመናንን ለማደናገር የሚለኩሱትን ሴራ አግባብ ባለው ሊጠይቃቸው ይገባል።
እውነት እውነት ናት!
June 1, 2011 12:27 PM
Anonymous said…
አቡነ ጳውሎስን ምን ነካቸው?
አሁንስ በዙሪያቸው የሚከናወነውን ነገር የሚያውቁ አልመስልህ አለኝ። እንኳን ከአንድ የቤተክርስቲያን መሪ ከቀበሌ መሪም እንዲህ አይነት ነገር አይጠበቅም። ለመሆኑ እንዲህ አይነት ቃለ ምልልስ ማድረጓን ያውቃሉ? ለመሆኑ ምዕመኑ ምን ያህል እንዳዘነ ያውቃሉ? አይመስለኝም።፡ቢያውቁ ኖሮ እዚህ ስሕት ውስጥ ዘው ብለው አይገቡም ነበር። ጠጋ ብሎ እውነትን ፍርጥ አርጎ የሚነግር እውነተኛ ሰው የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ሰውዬው አሁን እንደ ሙባረክ ሌላ አለም ውስጥ ጭልጥ ብለው እንቅልፋቸውን የሚለጥጡ ይመስለኛል። ይህ ከባድ የእንቅልፍ ድባብ ብዙ ነገር እያበላሸ ነው። እኔ የምፈራው የዚህ የሐውልታቸው ነገር ሃገራዊ መዘዝ እንዳያመጣ ነው። የሴትዮዋ አይነት ፉከራ ምዕመኑን ሌላ ውስጥ እየከተተው ነው። መንግስትስ ቢሆን እንዲህ አይነት ቀስቃሽ የሆነ ቃለ ምልልስ እንዴት በቸልታ ያልፈዋል? እኛ እኮ ወጦ ማፈራረስ ከብዶን አይደለም። ብዙ ነገሮችን አሰላስለን፤ጥቅምና ጉዳቱን አይተን በእነርሱ ያምራል ብለን ነው የተውነው። የይፍረስ አይፍረስ ውሳኔ የቤተ ክርስቲያኗ አባቶች እንጂ አንድ ተራ ምዕምን እየወጣ የሚፎክርበት መሆን የለበትም። አናም በቁስላችን ላይ እንጨት አይሰደድብን!!!!!!!!!! ዉጤቱ የከፋ ይሆናል! መንግስትም ሁኔታውን በአንክሮ ቢከታተለው መልካም ነው።
June 1, 2011 12:40 PM
ayyaanaa said…
sew be and kalemeteyik yihen hullu yiwashal!!! mot yishalal!!! yemayaneb, mereja yemagignet filagotim mebtim yelelew, yewah, yaltemare chewa… hizb agignta min tadirg tikelidibin inji!!!lebetekiristian idme lik yedekemu abatochina inatochachin be godana lay tetilew, lersua lij ke betekiristian bet tesetuat…awult mesrat kerto be fotoachew bitamelk bersua innifired???? …hullum yalfal.
June 1, 2011 1:02 PM
YibasAtamta said…
Banchi yetenesa banchi yetenesa
Yegebanewu eda yayenewu abesa
Yiqr Ayinesa Yiqr Ayinesa!Ejigayehu Ejigayehu
Elzabelua Ejigayehu
Banchi kifat sintun ayehu!Ewuyyyyyyyyyyiiiiiiii!!!!!!!!
Angefegefshign!

June 1, 2011 1:05 PM
Anonymous said…
“የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች በአባቶች መሀል አለመግባባት እንዲፈጠር የምታደርገው እሷ ነች ይላሉ፡፡”
kum neger yihen ket agegnech??? yet semach ?? yet anebebech
June 1, 2011 1:07 PM
ዘዮ said…
“ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።”
ዕብራውያን 5:12የዘመናችን ዮዲት ጉዲት!
እርስዎ ብል ደስ ይለኝ ነበር ። ነገር ግን አንቺ መባልን ስለሚመርጡ እንግዲህ አንቺ ለማለት ልገደድ ነው። እድሜ የማያስተምርሽ እምነት የሌለሽ የተሃድሶ አራማጆች ተላላኪ ለመሆኑ በዘረፍሽው የቤተክርስቲያን ገንዘብ ሀውልት አሰርተሽ ስታበቂ ገንዘቡን ያዋጣው ህዝብ ነው ትያለሽ ? ይህ ማጭበርበር አይደል? በርግጥ ለተለያየ ተልዕኮ ገንዘቡን በማታለል የሰበሰብሽው ከሚስኪኑ ምእመን እንደሆነ ይታወቃል። ይሁንና ያንቺ አጋፋሪዎች ካልሆኑ በስተቀር ለሃውልት ማሰሪያ ያዋጣ አንድም የተዋህዶ ልጅ አይኖርም። ያውም ቤተክርስቲያንን ለሚያምሱ “አባት”…ቀልደኛ!ይልቅ ከተናገርሽው ውስጥ አንድ እውነት አገኘሁብሽ እርሱም “ማህበረ ቅዱሳንን አላውቀውም”ማለትሽ። በእርግጥ አታውቂውም፣የሌላ የእምነት ድርጅት ተከታይ ሆነሽ እንዴት ማህበሩን ልታውቂው ትችያለሽ?ብታውቂውማ የሚያፀድቅ መንፈሳዊ ስራን ከመሃበሩና ከሌሎች እውነተኛ የቤተክርስቲያን አባቶችና ልጆች ጋር ትሰሪ በነበር።

ደግሞም ለቤተክርስቲያን ህንፃ ማሰሪያ እና ትምህርት ቤት ግንባታ በሚል ሰበብ ከየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በየጊዜው ከዘረፍሽው ገንዘብ ውስጥ በጣም ጥቂቱን ሰራሁት ብለሽ ለተመፃደቅሽበት ተግባር አውለሽው ሊሆን ይችላል ያውም እውነት ከሆነ።

ከሰሪው ጋር መታገል እንደማያዋጣ ተረድተሽ መጀመሪያ ቢቻልሽ እራስሽን በንስሃ እጠቢ። ያን ጊዜ መልካም ነገር ልትሰሪ ትችያለሽ። ሌላው በቤተክርስቲያን እና ዘመንሽን ሙሉ ባደግሽበት የጭፈራና የጥንቆላ ቦታ መካከል እጅግ ፍፁም ልዩነት እንዳለ ተረድተሽ ከብጥበጣና ካለሽበት የጥንቆላና የሴሰኝነት ህይወት እግዚአብሄር አላቆ ለንስሃ እንዲያበቃሽ ፀልዪ!

ወገኖቼ ሊመጣ ያለው እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ይመጣልና በፆም፣ በፀሎት፣በንስሃና በመልካም አገልግሎት ቤተክርስቲያናችንን እንጠብቅ!

“ገና በጣም ጥቂት ጊዜ ነው፥ ሊመጣ ያለውም ይመጣል አይዘገይምም፤”
ዕብራውያን 10:37

ስለ እናቱ ድንግል ማርያም እና ስለ ቅዱሳኑ ቃል ኪዳን ብሎ ቁጣውን በምህረቱ ያሳልፍልን!አሜን።

June 1, 2011 1:25 PM
Anonymous said…
Wey zendro! Egzio meharene-Kristos! Sint gud yasayenal! Patriarku gin min nekachew??? Lekas ende-Ejigayehu yalut hodamoch nachew “erso Kidus newot” eyaluachew …
June 1, 2011 2:03 PM
Anonymous said…
anchi gin minew ende edmesh bitnori,gizash eko yenisha new,anchim yegiber abatochishem WESHETAMOCH,ZERAFIWOCH,wey ahunis selechachihugne minew betachinen lekachihu bitwetulin??? gizash kireb new satshomi mertesh atikeri midre…………………….
June 1, 2011 2:26 PM
Anonymous said…
ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ብዙ የተምታታባት ነገር ያለ ይመስላል። ለምሳሌ:-
፩ “ማኅበረ ቅዱሳን የሚባል ማኅበር አላውቅም ፤ ራሱን ቅዱስ ብሎ የሚጠራ ማኅበርን አላውቅም ፤ ማኅበረ ማርያም፣ ማኅበረ ግሸን የሚባል አውቃለሁ፡፡” ብለሻል። ማኅበረ ቅዱሳን ማለት ራሱን ቅዱስ ብሎ የሚጠራ ማለት ነው ካልሽ አንቺ የምታዉቂዉ ማኅበረ ማርያም ራሱን ማርያም ብሎ የሚጠራ ነው ማለት ነው? መጀመሪያ ስለምታወሪዉ ነገር ጠንቅቀሽ እወቂ። እኔ እስከማውቀው ድረስ ማኅበረ ማርያም ማለት ሰዎች በእመቤታችን ስም ተሰባስበው ወይ ፅዋ ሲጠጡ ወይም መልካም ሥራ ሲሰሩ ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ማለትም በቅዱሳን ስም ተባስበው ለቤተክርስቲያን መልካም ሥራ አየሰሩ ያሉ ፤ የቤተክርስቲያንንም ልጆች ከእንዳንቺ አይነቱ አሳሳቾች ለመጠበቅ ደፋ ቀና የሚሉ ክርስቲያኖች ማህበር ነው እንጂ አንቺ እንደምትይው ራሱን ቅዱስ ብሎ የሚጠራ ማኅበር አይደለም።
፪ ስለ መኖርያ ቤቱ ስትጠየቂ “የዚያን ጊዜ እንዲያውም ከፓትሪያርኩ ጋር አንተዋወቅም ፤ የሰጡኝ ብፁእ አቡነ ቄርሎስ ናቸው፡፡” አልሽ። ትንሽ ዝቅ ብለሽ ደግሞ “ቅዱስ አባታችንን ለመጀመርያ ጊዜ ያየኋቸው ፓትሪያርክ ሳይሆኑ በፊት ነው ፤ አሜሪካ ሎሳንጀለስ” ብለሻል። ምን ማለት ነው? የምታወሪው እርስ በራሱ ይጣረዛል። ደግሞስ አንቺ ማን እና ምን ስለሆንሽ ነው አቡነ ቄርሎስ ቤት የሚሰጡሽ?
፫ ስለ ሐውልቱ ስትጠየቂ ደግሞ “እኔ ያመጣሁት ሳንቲም የለም ፤ በዓሉ በሚደምቅበት መንገድ ማገዝ ጀመርኩ ፤ ቅዱስ አባታችን እንዳይሰሙ ሰርፕራይዝ አድርጓቸው ብዬ በዓሉ ድምቀት እንዲኖረው ያማረ እንዲሆን አድርጌያለሁ” ብለሻል። ይሄ ማለት የአንቺ ሚና ሐውልቱ ሲመረቅ በዓሉን በማሳመር ብቻ ይመስላል። ግን ደግሞ ዝቅ ብለሽ የሚሰራበትን ቦታ እና እቃ በመምረጥ መሳተፍሽን ገልፀሻል። ሌላው ደግሞ ሐውልቱ የተመረቀ ወቅት የአንቺ እና የእነ በጋሻዉ ማህበር ለሐውልቱ መገንባት በገንዘብም በጉልበትም ትልቅ አስተዋፅዎ እንዳበረከተ ተገልፆ ተሸልማችሁበታል።የበተናችሁት የመጥሪያ ወረቀት ላይም የእናንተ ስም እንጂ የአ/አ ወይም የቃሊቲ ህዝበ ክርስቲያን ያሰራው አይልም። እና የኢትዮጵያ ሕዝብ አያዉቅም ፤ አይሰማም መስሎሽ ነው እንደዚህ አደባባይ የወጣ ውሸት የምትዋሽው?
እነዚህ ለምሳሌ የተጠቀሱ ናቸው እንጂ የአንቺ እና የግብረ አበሮችሽ ውሸት በዚህ አያበቃም።
ደግሞስ “እርሳቸው ጋ የምገባው ቡራኬና በረከት ለማግኘት ነው” ያልሽው አንች ከኢትዮጵያ ህዝበ ክርስቲያን በምን ተለይተሽ ነው ቤታቸው ሄደሽ ቡራኬና በረከት የምትቀበይው?
ብቻ እግዚአብሔር ለአንቺ እና ለመሰሎችሽ ልቦና ይስጥልን።
June 1, 2011 2:58 PM
Anonymous said…
ይቺ ሴትዮ አሁንስ ለየላት። እንዲህ የሀሰት መአት የሚያስደረድራት መቼም የተጠናወታት መንፈስ ነዉ እንጂ… ፀበል የሚያስጠምቅ ዘመድ የላትም እንዴ?
June 1, 2011 3:21 PM
Anonymous said…
ere ebakachehu wegen yebtekereseteyan sew setesadebu hateyat testaweru sew kedemoachehu telo yet deresewal ahun min agegnachehu yesew hateyat awertachehu? yiker yibelachehu egziooooo maherene kersetos yeabune pawlos Amelak Dink new derom melkam ena kidus abat yisedebal bebalege minew rasachehun meremeru tsadekan atehunu yemetsafelachehun asteyayeten teruwen becha atetsafu tekawemowenem awetu tedebeko torenet yelem ethio.vio amerka megelechawen semachehu? teru neger new astewelu
June 1, 2011 4:33 PM
man yaziwal said…
ልክ ብለሻል ኤልዛቤት የቅዱሳኑን ማሕበር አታውቂውም። ብታውቂውማ በቤተ ክርስቲያን ጣኦት ባላቆምሽ ነበረ። ዕርጉም የተረገምሽ ነሽ። የእሥራኤል አምላክ መጨረሻሽን ያሳየኝ።
June 1, 2011 5:59 PM
Melikamekene said…
ዛሬ የምታየው ከሺህ ብር በላይ ደሞዝ የሚከፈለው ቄስ ሁሉ ድሮ ወይ በጤፍ ወይ በሰላሳ ብር ብቻ ነበር የሚያገለግለው፡፡
O! we know our house and loyal priests of EOTC till this moment without payment and 10 EBirr/yr.
ስለሃውልቱ የማውቀው ነገር የለም!!
is she considers us kid? Foolish, we know all! you will get your wage form God. He know all!!
GETAHOYE YENISEHA MOTE SITACHEWE LEHULETUME
June 1, 2011 6:12 PM
T/selase ከስዊድን said…
ምንድን ነች ሴትየዋ፣ በዚህ በ66 (አንድ 10 ቀንሳለች) ዕድሜዋ ትዋሻለች
June 1, 2011 6:41 PM
Anonymous said…
ተማረኩ (ስነ ግጥም)
አለም ያከበረኝ ጎበዝ ነገር ሠሪ
ለቃሉ ያልተገዛሁ በጣሙን መሠሪ
ትዕዛዝን የማልወድ ትዕግስት የማያውቀኝ
ና በዚህ ከተባልኩ ወደዛ የሚታየኝ
መልካም በታየበት ክፉ የሚወጣኝ
ደግ ነገር ሣይሆን ተንኮል የሚቀድመኝ
የጠራኝን ገፊ የሣመኝን ነካሽ
ያየሁትን ሁሉ ያለምክንያት ተንኳሽ
ቅንነት ያላየኝ ቸር ወሬ የማልወድ
ከመልካሙ ይልቅ ለክፋት የምሰግድ
ፀጥታን የማልወድ ሠላም የሚያውከኝ
መልካምን ለማጥፋት ዕንቅልፍ የሚነሣኝ
ለመከረኝ ጠላት ለወደደኝ አጥፊ
ላጎረሰኝ ነካሽ ያቀፈኝን ገፊ
አንገተ ደንዳና ልበ ድንጋይ ክፉ
ነበርኩኝ ጠማማ እጅግ ልበ ጥፉ፡፡
መልካሙ ሲወራ ውስጤ ይረበሻል
ፀጥታ ካለበት ሠላሜ ይናጋል
ቃሉ ከተወራ ያንቀጠቅጠኛል
ለባልቴቱ ወሬ ጆሮዬ ይተጋል
ጌታ ከተጠራ ውስጤ ይታወካል
ኢየሱስ ባለበት መቆም ያቅተኛል
ልጆቹን ሳያቸው ያበሰጫጨኛል
የእነርሱ እርጋታ ልቤን ይረብሻል
የእነርሱ መፅናናት ሠላም ይነሳኛል
ውድቀታቸው ጽድቄ ክብሬ ይመስለኛል
እነርሱን ለማጥፋት እንቅልፍን አጣለሁ
ከእውነቱ ይልቅ በሀሰት እፅናናለሁ
ለእውነት እንደሮጥኩኝ ለራሴ ነግሬ
በክፋት ውስጥ ነበርኩ ከብዶብኝ ቀንበሬ፡፡
ዛሬ ግን
ለክፋት መትጋቴ እልህ ሣያሲዘው
እርሡን ማሣደዴ እኔን ሣያስገፋው
በገፋሁት ቁጥር በፍቅር እያየኝ
ተግቼ ሳሳድድ ፍቅር እየለገሰኝ
በትር ሣነሳበት ዘንባባ እየሰጠ
የዘላለም አምላክ ህይወቴን ለወጠ
እንደተናገረ በፍቅሩ ስቦኛል
ታሪኬን ለውጦ ልጁ አድርጎኛል
ፍቅሩን ሣጣጥመው ልዩነቱ ገብቶኝ
ለርሡ የመገዛት እርካታው ተሰምቶኝ
ተማረኩኝ ብዬ እጄን አንስቼአለሁ
ለማረከኝ ጌታ ራሴን ሰጥቻለሁ
ተማረኩኝ ጌታ በዘላለም ፍቅርህ
ተገዛሁ ለክብርህ ለሚያድነው ኃይልህ
ተንበረከኩልህ ሰገድኩልህ ዛሬ
ላንተ ሳጎነብስ ወደቀ ቀንበሬ
የገዛኝን ክፉ ባሪያው ያረገኝን
በስምህ ኃይል ጣልኩት ዛሬ ቀን ወጥቶልኝ
ወደቀ ጠላቴ ተመታ በስምህ
እኔም ተማረኩኝ ሰገድኩኝ ለክብርህ
ተማረኩ ብያለሁ ተማረኩ ተገዛሁ
በፍቅሩ ለረታኝ ማንነቴን ሰጠሁ
ጥቅሜ ብዙ ሆኖ ሠላሜ ታድሷል
ከጌታ ጋር ከሆንኩ ማንስ ይችለኛል
በብርቱ ክንዱ ሥር ተሸሽጌ አለሁ
እረፍትን አግኝቼ ይኸው እታያለሁ
እኔም ወግ ደረሰኝ ጠላት ተቆጣብኝ
የኢየሱስ ነው ብሎ ጥርሱን ነከሰብኝ
እኔም ተቆጣሁኝ ጥርሴን ነከስኩበት
መንግስቱን ለማፍረስ በግልጽ ተቋቋምኩት
ዛሬ ወግ ደረሰኝ መማረክ ጠቅሞኛል
ከጌታ ጋር ከሆንኩ ማን ይቃወመኛል?
ማን ይታገለኛል? ማን ይቋቋመኛል?
ኢየሱስ ብርቱ ነው ሁሉን ያሸንፋል
ተማረኩኝ በእርሱ ሠላሜ በዛልኝ
ከሁሉ ለሚበልጥ ለርሡ ተገዛሁኝ
ተማረኩኝ በርሡ መልካም ሰው ሆኛለሁ
ጌታ ስለነካኝ ተለዋውጫለሁ
ለሚያውቁኝ ሌላ እንግዳ ሰው ሆንኩኝ
በበታደገኝ ጌታ ፍፁም ተለወጥኩኝ
ተበሳጨ ሲሉኝ በትዕግስት አልፋለሁ
ተሣደበ ሲሉኝ መርቄ እገባለሁ
ረበሸ ሲሉ ሠላም አሰፍናለሁ
ተቃወመ ሲሉ ስሙን እሰብካለሁ
በርግጥም
ኢየሱስ ነውና ተለውጫለሁ
ገና ብዙ ብዙ ሌላ ብዙ ነገር ጌታ በኔ ይሠራል
ትውልድም ታሪክም ይህን ይታዘባል፡፡
June 1, 2011 6:52 PM
stop said…
Why not use your time for developing the church than playing with ignorant widow?
June 1, 2011 7:09 PM
Anonymous said…
ለወሮ እጅግአየሁና እርሷን ለመሰሉ ዛሬም እየተፈለፈከሉ ላሉት የሐሰት ጫጩቶች እግዚአብሔር ከተቀሰፈ ሕሊናቸው እንዲፈውሳቸው እጅግ ካልፀለይንላቸው እጅግ ይጎዱናል፡፡ በሥጋ፡፡ እነርሱ ግን በነፍስ ይጎዳሉ፡፡ እጅግ አየሁ ሆይ እጅግ ተግተሽ ራስን እይ! እግዚአብሔር ይርዳሽ፡፡ አንቺን ከረዳ እኛም እንደራዳለንና፡፡
June 1, 2011 7:18 PM
Anonymous said…
ይህንን ወሬ በዛ አካባቢ ቃሊቲ ያላችሁ ብታረጋግጡልን
አልፎ አልፎ የሀሰት ተዐምር ተደረገ እያሉ የሚቀጥፉ የሚያወናብዱ አሉ
ነገ ደግሞ የሞተ ሰው አስነሳን ይሉናል
” ወ/ሮ እጅጋየሁ፡- ቃሊቲ ያለችው ቁስቋም ማርያም ፅላቷ ለጥምቀት ከወጣ በኋላ አልገባም ብሎ አልመለስም አለ፡፡ ለብዙ ጊዜ ተቀምጦ ሕዝቡ በምህላ በለቅሶ በጭንቀት ላይ ነበር፡፡ በኋላ ቤ/ክ አሰራለሁ ብለው መሰለኝ አንድ ሰው ሰሩ፡፡ እሱ ከተሰራ በኋላ አሁንም ማስገባት አልተቻለም፡፡ ከብዙ ምህላ በኋላ ቅዱስ አባታችን ቦታው ድረስ ሄዱ፡፡ ያን ጊዜ “እስካሁን ያልተቻለውን አሁን እኚህ ሊያስገቡ ነው?” እያሉ የተቹ ነበሩ፡፡ በአንድ ቡራኬ ነው፡፡ ድፍት ብለው ወድቀው ጸሎታቸውን ካደረሱ በኋላ ብድግ አድርገው |ፅላቱን ያስገቡት፡፡
June 1, 2011 7:26 PM
Anonymous said…
ባለረዥም ግጥምበአንተ/አንቺ የኑፋቄ ትምህርት ማ ይቀናል? ከቀደመች ርትእት ሃይማኖት መውጣት እንደ ጽድቅ መቆጠሩ ነው ይህን ያህል መቀባጠሩ?

ለማንኛውም የእጅጋየሁ ገሃድ የወጣ ሀሰት በሀሜት ሳይሆን በተግባር በታየበትና በሚተችበት በዚህ ሰዓት እርሷን የመንቀፍን ኢተገቢነት ለማውገዝ በሞከሩበት በዚህ ረብ የለሽ ግጥምጥምዎ እርስዎን ጨምሮ የቡድናችሁን የተሐድሷዊ ኑፋቄ በመናዘዝዎ ሳላመሰግንዎ አላልፍም።

ኢየሱስን አሁንም ስለማግኜትዎ ግን ርግጠኛ ይሁኑ። ሕዝብ የሚያውቀውን እውነት ዓይኔን ግንባር ያድርገው ብሎ መዋሸት ኢየሱስን ማግኜት ተደርጎ ከተወሰደ እኛ የምናውቀው ሳይሆን እውነተኛውን ስም የወሰደ ሌላ “ውሸታም ኢየሱስ” (ሎቱ ስብሐት) መሆን አለበት።

ለማንኛውም እናንተ አዲስ አምላክ በማግኘታችሁ አንቀናም አንቃወምም። ጥያቄያችን ቤታችን ውስጥ እየታመሳችሁ ሰላም አትንሱን ነው። ወይ ሙጨጭ ብለን የእናንተን ጥንታዊት የተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የእኛ ነች ብለን ከሆነ ህግ ይዳኘን። ነገር ግን ትናንት የመጣችሁት እናንተው ስለመሆናችሁ በቅርቡ ኢየሱስንና ሰላምን ማግኘትዎን ባተቱበት ግጥምዎ አምነውልናልና ፍርድ ቤት ድረስ ምን አስጓዘን? ምን አለበት ረፍት ባትነሱን?

ለማን አቤት ይባላል? ለፈጣሪ ብቻ። እግዚአብሔር ያስታግሳችሁ!!!!!!

ቢንያም ዘባህርዳር

June 1, 2011 8:02 PM
yohannes said…
ሰይጣን(የወ/ሮ እጅጋየሁ )በሰዎች ልቡና ያድርና ራሱን ደብቆ ክፉ ሥራ ሲያሠራቸው ይኖራል፡፡ በወንጌል እንደተነገረው በጾም፣ በጸሎትና በመንፈሳዊ ሥራ እንዲሁም በተቀደሰ ውሃና አፈር (በጸበል) ኃይሉ ሲደክምበት ‹‹ተቃጠልኩ›› እያለ ይለፈልፋል፡፡ በዚህ ጊዜ ሰይጣን መሆኑ ታውቆ አስፈላጊውን መንፈሳዊ ሥርዓት በማከናወን ያንን ሰው ለቆ እንዲወጣ ይገሠጻል፤ ይረገማል፤ ይገዘታል፡፡ ወዲያውም ለቆ ይሄዳል፡፡የተወደድክ ሙሀሙድ ምኑን ቺለሀው ኖርክ? ይሄንን ሁሉ ዉሸት መቻልህ በእዉነት ታላቅ ሰው መሆንክን ያሳያል።
June 1, 2011 8:45 PM
Zehawassa said…
Ejegayehu, i have no dout your destiny will like Ariyos,unless you correct your way.
June 1, 2011 8:53 PM
yohannes said…
ሰይጣን(ወ/ሮ እጅጋየሁ)በሰዎች ልቡና ያድርና ራሱን ደብቆ ክፉ ሥራ ሲያሠራቸው ይኖራል፡፡ በወንጌል እንደተነገረው በጾም፣ በጸሎትና በመንፈሳዊ ሥራ እንዲሁም በተቀደሰ ውሃና አፈር (በጸበል) ኃይሉ ሲደክምበት ‹‹ተቃጠልኩ›› እያለ ይለፈልፋል፡፡ በዚህ ጊዜ ሰይጣን መሆኑ ታውቆ አስፈላጊውን መንፈሳዊ ሥርዓት በማከናወን ያንን ሰው ለቆ እንዲወጣ ይገሠጻል፤ ይረገማል፤ ይገዘታል፡፡ ወዲያውም ለቆ ይሄዳል፡፡የተወደድክ ሙሀሙድ ምኑን ቺለሀው ኖርክ? ይሄንን ሁሉ ዉሸት መቻልህ በእዉነት ታላቅ ሰው መሆንክን ያሳያል።

June 1, 2011 8:57 PM
Anonymous said…
“የዚያን ጊዜ እንዲያውም ከፓትሪያርኩ ጋር አንተዋወቅም” …. “ቅዱስ አባታችንን ለመጀመርያ ጊዜ ያየኋቸው ፓትሪያርክ ሳይሆኑ በፊት ነው…አሜሪካ ሎሳንጀለስ” …
ስንዋሽ ትንሽ ብንጠነቀቅ ጥሩ አይመስልሽም እጅግየ!?
June 2, 2011 3:49 AM
Anonymous said…
Thank you w/o Ejegayew! Aba Paulos is a great father. please let us stop disrespecting him.
June 2, 2011 7:22 AM
Anonymous said…
እጅጋየሁ
ቅዱስ እባታችንን በደግ ማንሳትሽ መልካም ነበር:ያልተገባ ሙገሳ እየደረደርሽ በከንቱ ውደሴ ፀጋቸውን አሳጣሻቸው እንጂ ዛሬ ሙገሳ ና ውደሳ በዝቶባቸው ወደጎ ን ዘንበል አሉ:ለእርሳቸው ጠብ እርግፍ የሚል እውነተኛ የቤ/ክርስትያን ልጅ ነው::ማህበረ ቅዱሳን ብሎ ራሱን ቅዱስ አድርጎ የሚጠራ ማህበር አላውቅም አልሽ ሰይጣን እኮ የምትሉትን አላውቅም አስብሎ ያስክዳል ቅዱስ ጴጥሮስን አሰኝቶት ነበር::
ማህበረ ቅዱሳን የቅዱሳን ስብስብ ማለት ነው ካልሽ
ማህበረ ማርያም የማርያሞች ስብስብ
ማህበረ አማኑኤል የአማኑኤሎች ስብስብ መሆኑ ነው ማለት ይሆን?እኔን እንዳልገባ የሚከለክሉኝ አቡነ ጰውሎስ ናቸው አልሽ የቤ/ክርስትያን ስርአት ና ደንብ ለማታውቂ ላንቺ የቤተክህነቱ ፈላጭ ቆራጭ አዎ እሳቸው ናቸው ብታውቂው ግን ሲኖዶስ የመጨረሻው የቤ/ክርስትያን የስልጣንባለቤት ነው/የብዙ ብፁዓን አባቶች ጸሎት ና ቃል ይሰማል::

ሀውልቱን ሲያዩ
እኔ ማነኝ ይሄ ነገር ለኔ አይገባም ምን ስላደረግሁ ብለው ራሳቸውን ዝቅ አደረጉ: ዛሬ ደግሞ ማን ወንድ ያፈርሰዋል ብለው ራሳቸውንቀና አደረጉ:: አይገርምም እጅጋየሁ?

ሀውልቱማ አሁንም አለ ወደፊትም ይኖራል አልሽ አዎ የሲኖዶሱ ስልጣን ስልጣን ባንቺ የተወረሰ ይመስለኛል::

June 2, 2011 9:26 AM
Anonymous said…
እጅጋየሁ እና ግብራበሮቿ ቤተክርስቲያንን እንዲህ ለማደፍረስ የሚያደርጉትን ሩጫ እግዚአብሔር እንደሚያጠራው አትጠራጠሩ፣ እኔ ግን አንድ ነገር አስተዋልኩኝ ድምጻዊ መሐሙድ አሕመድ ምንኛ ተገላግሏል፣ ከዚህች ሴት በመለያየቱ አርፏል፡፡ ምንም እንኳን እኛን በተራዋ እያቆሰለችን ብትገኝም፡፡
June 2, 2011 10:44 AM
Yebirzaf said…
ምትለውን ማኅበር እኔ አላውቀውም፡፡ የጽዋ ማኅበር ይሁን ወይም ሌላ እኔ አላውቀውም፡፡ የማኅበረ ማርያም፣ ማኅበረ ግሸን የሚባል አውቃለሁ፡፡ ራሱን ቅዱስ ብሎ የሚጠራ ማኅበርን ግን አላውቅም፡፡ አሉባልታን የሚያናፍሰው የአጋንንት ማኅበር ካልሆነ ማን ሊሆን ይችላል? ሃይማኖት ያለው ሰው አሉባልታ ላይ ጊዜ አያጠፋም፡፡ እኔን እዚህ እንዳልገባ ሊከለክሉ የሚችሉት ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ብቻ ናቸው፡፡
Yeminagerutin Ayukumna Yiker belachew
June 2, 2011 11:48 AM
Anonymous said…
እንዲህ አይነት ሴቶች በየጊዜው ይነሳሉ ዮዲትም ተነስታለች እኔ ግን በእሳ አፍ በእሳ አለባበስ በእሳ ህይወት
ለአቡነ ፓውሎስ ሲመሰከርላቸው ስለቤተክርስቲያን ክብር ስል አፈርኩ ኦ አባት ሆይ ይህን ቀን አሳጥርልን በደምህ ስለ መሰረትካት ስለቤተክርስቲያን ስትል
June 2, 2011 3:07 PM
Anonymous said…
እድሜዋ 66 ያውአንድ6 ትጨምርና 666 ትባል
June 3, 2011 7:01 AM
Merkeb said…
እኚህን አዛውንት የእድሜ ባለፀጋ ሴት እኔ በፍፁም አላውቃቸውም። ሆኖም ንግግራቸው ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነና አናዳጅ የመሸታ ቤት ሴት ንግግር ይመስላል። በዚህ ስብዕናቸው ነው ሰው የሚያስታርቁትና በጎ ሥራ እየሰራሁ ነው የሚሉት?ወላዲተ አምላክ ትሁናቸው!!

የኖህ መርከብ ከአ.አ.

June 3, 2011 8:44 AM
Anonymous said…
ውድ የደጀ ሰላም ታዳሚዎች!
መናፍቀኑን ቅሰጣ ለመመከት እያደረግነው ያለው ተጋድሎ በጣም የሚያስደንቅ ነው። ይሁንና ከማዕበሉ (ከሱናሚው)ሀያልነት አኳያ ሲታይ እጅግ የሚመጣጠን አይደለም። ጀልባዋ እጅግ እየተናጠች እኛ ግን ጥሩ እንቅልፍ ላይ ነን። እባካችሁ ነገሩ ሁሉ “ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው” እንደሚባለው ዓይነት ሆኖ ስለተሰማኝ የመጨረሻውን የመከላከል አቅማችን ተጠቅምን ወደ መልሶ ማጥቃት እንሸጋገር። ብዙ ሺህ ዘመን ተሻግራ የመጣችውን ቤተክርስቲያናችንን በጥቂት ዓመታት አጥተን ምድረበዳ ላይ እንዳንቀር። አደራ! የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ነገር አደራ!
June 3, 2011 9:25 AM
Anonymous said…
ወንድሞቼ እህቶቺይህችን ሴትዮ እንደ አንድ ጋለሞታ ንቆ ማለፍ ስህተትን ነው። ይህን የተማርነው ከስህተታችን ነው።
እዝህ ሲያትል ዋሽንግተን በምትገኝ አንዲት ደብር ካህኑና በተሰቦቻቸው ቤተክርስቲያንቱን የግል ብዝነስ አካውንት ለማድረግ ባነሱት ሴራ፤ በምህመናን እና በካህኑ ቤተሰብ በተነሳ ውዝግብ፤ ሰበካ ጉባአኤውና ምእምናን የፈጸሙት ስህተን ይህን ነበር። ካህኑ እጅጋዪሁ አለችልኝ አሉ። ሰበካ ጉባኤውና ምህመና፤ በፍጹም ቅዱሳ ፓትርያርኩና ሃገረ ስብከቱ፤ በአንዲት ሴት አይመሩም፤ የሚወስኑት ውሳኔ የቤ/ክርስቲያንቱን ህግና ቀኖና የጠበቀ ነው የሚሆን እንጂ ፤ የአንዲት ሴት አይደለም በማለት ተደላደሉ። ይገምቱ፤ እጅጋዬሁን የተማመኑ ረቱ፤ ቃል በቃል የእጅጋዬሁ ውሳኔ በደብዳቤ ተጽፎ ለደብሩ ደረሰ። ስኖዶስ፤ ፓትሪያርክ፤ ሃገረ ስብከት እጅጋዬሁ ናት። እንማር። ብዙ ብዙ ታሪክ አለ። ሴትዮዋ የፓትሪያርኩን የግል ምስጥራቸውን ሳይቀር አውቃ፤ በጥቅም ተሳስራ፤ ከስኖዶስና መስፈስቅዱስ በላይ ሆና፤ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን እያሰገረች ናት። ደጀ ሰላም ነቅታለች፤ ሁላችን እንንቃ። የርሷ ኔትዎችኮችን በያሉበት እንንቀላቸው። እርሱ ጌታ ይታደገን። አሜን።
June 3, 2011 10:41 AM
Anonymous said…
ለደጀ ሰላሞች፡-
በዚች ጉደኛ ሴትዮ ላይ ካንባቢዎቻችሁ የተሰጡ አስተያየቶች ማለፊያ ናቸው። ምን ያህል ደካማ ቃለ ምልልስ እንደሆነ ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ስለዚህ ቃለምልልሱንና የንባቢዎችን አስተያዮት በፒዲኤፍ አድርጋችሁ ብታስቀምጡልን እያተምን ጉዷን ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማድረስ ዝግጁን። ስለዚህ እባካችሁ ይህን አድርጉልን።
June 3, 2011 11:24 AM
Anonymous said…
የቅዱሳን አባቶች ምስክራቸው ስራቸው እንጅ በእንዲህ አይነት ቅጡ የጠፋት ሰው አይደለም። እንዃን ለምስክርነት ልትበቂ ይቅርና የቆምሽበትን ቦታ በቅጡ ያወቅሽ አይመስለኝም። ቦታው እኮ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የተመሰረተ ቦታ ነው።
June 3, 2011 2:52 PM
Anonymous said…
እጅጋየሁ፡
እውነቱን ደብቃ ስትለበልፍ ያያት፣
ጅብ በማያቁት አገር ተብሎ እንደሚተረት፣
ጋጠወጥ መሆኗን ከቁምነገር እዩአት።
የሁሉ ፈጣሪ የስራሽን ይስጥሽ፤
ሁነሽ እንዳትቀሪ ቤተክርስቲያን አፍራሽ።
ግንቦት 26/2003.
ጀርመን
June 3, 2011 3:04 PM
Anonymous said…
THE PERSON WHO GAVE COOMENT FOR EJEGAYEHU. DONOT USE BAD WORDS, OK YOU ARE OUT OF GOSPEL. IF YOU WANT GIVE COMMENT USE GOOD WORDS.THINK BEFORE YOU WRITE . I AM NOT A SIDE OF THE LADY , I AM TAKING SIDE FOR MY CHURCH.
June 3, 2011 3:34 PM
Anonymous said…
ባያድለን፣ ብንረገም፣ በክፉ ሥራችን ክፉ የሃይማኖት መሪ ለቅጣት ቢጥልብን እንጂ ቤተክርስቲያናችን በመሃል ሠፋሪዎች ማዕበል በምትናጥበት በዚህ ሰዓት የአንዲት አሮጊት ጋለሞታ ጉዳይ አጀንዳችን ሆኖ እንወዛገብ ነበር።ኣይ አባ ጳውሎስ እግዚአብሔር ይይልዎ። የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በራሷ ታሪክ ይቅርና በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ሁኔታ የአንዲት ተራ ሴት ታሪክ የቤተክርስቲያን የየዕለት መነጋገሪያ ሆነ። የአንድ አገር ፓትርያርክ ለዚያውም ደግሞ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዝዳንት ይቅርና አንድ አባወራ ቢፈጽመው እጅግ የሚያሳፍር ተግባር።

እባክዎን ሴትዮዋ በየዕለቱ ከእርስዎ ዘንድ እየቀረበች የመባረክ ግዴታ ከጣሉባት ቢያንስ ቢያንስ ሕዝብን በማያሰናክልና በማይታይ መንገድ ይሁን። ከተቻለም ከእርስዎ እጅግ ቀለል ያለውን አባ ሰረረረረረረረረረረረቀን ይመድቡላት።

እግዚአብሔር ያያል!

ቢንያም ዘባህርዳር

June 3, 2011 4:33 PM
Anonymous said…
Hizbechrstian bemulu, yichi setio yenorechew alem lay sitizefin, sitchefere new. Silzih tiru negere metebeke kenetu new. Erso ena godegnocho ande nache yegeremegne gin papasatu beso hasabe simeru new. Egiziabehere becherenetu yitbiken enji geziew asferi new. Bezih seat new malkese, mazene yalbin gobeze. Egiziabehere lepapasatum lebona yistachew elalehu.
June 3, 2011 5:05 PM
Emuye said…
YEZIAN GIZE ENDIAWUM KE PATRIAKU GAR ANTEWAWOKEM……….. YE MAWUKACHEWU LOSANGELES AMERICA EYALU NEWU. WEEEEEEEY WUSHET!!!!!!!!!!!!!!!!
June 3, 2011 5:32 PM
Anonymous said…
To all orthodox
And ewnet lingerachu,enezih sewoch(yemibetebitun -ene ejigayehu,ene getachewdoni,ene sereke ,lelochim Egziabher yemiawkachew)mejemeriam kebetechiristian aymeslugnim.Wede nisiha endigebu enitseliyilachew,enastemirachew. wede nisiha eskimetu gin yemaigebachewin siltan yizew endaybetebitun yetechalenin hulu enadrig.Yebetechristian astedader zimbilo bezefekede endaihon lemiketilewyesinodos sibseba agenda biazilin.Hizbu lesinodos sibseba tiyakewin endiasema bideregilin.
bet sikoshish yiteregal,sikatelim zim
ayibalim.Esti hulachin betechristianin endebetachin enkuterat.Egna eko tegnitenal. hulachin betsegachin ,begenzeb, begulbet,beewket belelam yemagelgel halafinet alebin-yene bilen eniyazew.le 3000 amet yeabatoch,yeenatoch,yekidusan tegadlo
ebet kuch bilo betedeledele nuro yemifers endaihon.Bezih agatamai estisilekidusan tegadlo enenibib endiet yeseytanin fetena endalefu.tselot enadirg betechemariyikoyen

June 3, 2011 8:01 PM
tekelusisaye said…
Enateye w/ro Ejigayehu Ebakeweten befeterewet B 3tu selasochi Sekesike bilewu Alekesew Fetarin Yikereta weyem neseha yigebu! Kesewe befite egizabiheren yiferu!Yihene yemelewot kesewu hulu betam tinshi tebiya yehonkute sehoneEbakewote Enate hulun yitewut ena Lefetari bicha yikorekoru! Egizabihere Yimarewot , Abero yimaren!
June 4, 2011 1:11 AM
ለውጥአየሁ said…
የተሐድሶ ሴራ በሐዋሳ ከተማ ይመልከቱ
እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን፡፡http://www.youtube.com/watch?v=ldoU-V-2GtM&feature=related
June 4, 2011 9:15 AM
Anonymous said…
WOW DEJE SELAMOCI AHUNIM YEZEGUBACIHU MESILOGN BETHAM AZIGNE NEBER. MENORACIHUN SAY DESSSSS ALEGN. TSIHUFUN BEHUWALA ANEBALEHU AHUN GHIN MENORACIHUN BE MAYETE DESTAYEN LIGILETS INA … LEMIN GHIN INDEBEFITU BE MAIL AYIDERSEGNIM NEWS???
June 4, 2011 9:21 AM
Anonymous said…
ሀውልቱ አይፈርስም? ትእቢተኞችን የሚያፈራርስ ጌታችን አንቺን ያፈረስሻል!!!!!!! ማፈሪያ
June 4, 2011 1:36 PM
yemelaku bariya said…
ይቺ ጋለሞታ አወቀችው አላወቀችው ምን ታመጣለች:: ለነገሩ በሷ ቤት Smart መሆኗ ነው ማ/ቅ ምንድነው? የጽዋ ማህበር ይሁን አይሁን አላውቅም አለች:: እንደት ትወቀው:: የሚመነተፍ የለው የድሆች ማህበር:: ያለውን ያለአግባብ የማያወጣ የቅንጦት ወጭ የሌለው ለቅዱስነታቸው የተለያዩ ዓለማዊና ብዙም ኃይማኖታዊ ላልሆኑ ነገር ግን ስማቸው ኃይማኖታዊ በሃሎች ገንዘብ ያማያዋጣ ለሳቸው ስጦታ የወርቅ መስቀል የመሳሰለውን መስቀል የማይሰጥ ጋለሞታይቱ ጥሩ አድርጋ የቸበቸበችውን የሳቸውን ፎቶ በገንዘብ ያልገዛ እና ሌላውንም የዚህ ሁሉ መዝገብ ያለው እኮ እሷ ጋ ሳይሆን አይቀርም:: በዛ ዝርዝር ውስጥ የሌለውን አታውቀውም:: በዛ ያለዉን ግን መልኩን ባታውቅ ስሙን ታውቃለች:: እሷ አወቀች አላወቀች ደግሞ ምንታመጣለች:: ፓትርያርክ ተብየውን ምን እንዳስነካቻቸው አይታወቅም:: ደግሞ እሳቸው ጻድቅ ናቸው አለች ይገርማል የጽድቅ ዝርዝርም ከሷ ጋ አለ ማለት ነው:: ብታውቀውስ የአዘቅት መንገድ ናት:: እሳቸውን የምትወጃቸው ከሆነ እባክሽ ለንስሃ የሚሆን ትንሽ እንኳን ጊዜ ቢያገኙ ለቀቅ አድርጊያቸው:: አንቺም ትንሽ ስምሽ ይረፍ:: ደሞኮ የጽድቃቸው ሚስጥር ሲነገረን ከሚ/ር ዶኒ ጋ መክራችሁ ያደረጋችሁት እንደሆነ እንድንጠረጥር እያደረጋችሁን ነው:: እናንተ እንደሆነ እግዚአብሔርን ህልውናውን እንኳ የማታምኑ ምናምንቴዎች ስለሆናችሁ በታቦቱ አትሳለቁን ማለት አይቻልም:: እኛን አሁንያሳሰበን የጳጳሳቱ አሟሟት መመሳሰል ነው:: መንግሥት ስለሌለን አጠራጣሪ የሆኑ አሟሟቶችን እንኳ አይመረምርም እንጅ ቢመረምር የሆነ ነገር አይጠፋውም ደግሞ የሞቱት የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች ነበሩ:: አየጉድ እግዚአብሔር ብትሩን ያነሳ ጊዜ እነዛ የምታዣቸው የደህንነት ሠዎች እንኳን አያስጥሉሽም:: ለመሆኑ ልጅ አለሽ ካለሽ ለጆችሽን የምለምነው እባካችሁ እናታችሁን ከቤተ ክርስቲያናችን ላይ ገላግሉን ስለ ገብርኤል ብላችሁ:: እባካችሁ!!!!!!
June 4, 2011 2:12 PM
Surprise!!!! said…
“የተወደድክ ሙሀሙድ ምኑን ቺለሀው ኖርክ? ይሄንን ሁሉ ዉሸት መቻልህ በእዉነት ታላቅ ሰው መሆንክን ያሳያል።”
to the above comment giver,
+ You see, what a single man-Mahmud carried the garbage of one evil widow, for Ethiopians become difficult though we are millions.Surprise!!!!
June 4, 2011 2:24 PM
Anonymous said…
ahun min yihun ye weyezero Ejegayewen foto ezhi lay mawetat min asfelge?Yihe tsedk new?Egziabeher enkuan Ylejochun Bedel yishefenal ayee enanete lib yisetachehu Weyezero Ejegayehu Be Egziabeher Be Abatewa Medehaniyalem fit Tekbralech Enante Gin waaaa azenkulachehu
June 4, 2011 6:13 PM
Wolde Tensae (Hawassa) said…
Dear Dejeselam, Enante bezemenu yalewun yebetechristianin chigir silawoyayachihu egziabher yibarkachihu. Gin yihe tumera fitsum hayimanotawi silehone besimet sidib yemitsifutin batakerbu des yilegnal. Hulum asteyayet mekirebu tiru new (tekewumom bihon) kesidib besteker. Ene endemayewu, bebetechristian wust yalew fetena kemechewum gizie yekebede new. Silezih min enadirg bemilew guday lay sewu hasab endiset forum bitifetru tiru new. Mechem yemengist balesiltanatim gudayun eyayut endehone asibalehu. mahibere kidusanim bihon gudayun le mengistim biasawuk tiru yimeslignal. Mengist behaimanot wust talka ayigebam yemil neger binorim, tikit sewoch behageritu tilikun yehaimanot tekuam siamisu zim bilo mayet yalebet ayimeslegnim. Yalewun impact maseb tiru new. Mengist kewust gebto tirit adirigo negerun matinat yitebekibetal. Mechem sew hagerun bitela tilo lihed yichilal egziabherin gin tito mehed ayichalim. Silezih dejeselamoch, mintenigiber (min enadirig), bemilew lay hasab bitansherashiru tiru new. Egziabher amlak betechristianin yitebikilin. Wolde tinsae (Z hawassa)
June 4, 2011 9:08 PM
Anonymous said…
ውድ ደጀሠላማውያን
ይህን ካለመጠይቅ ያደረገው ጋዜጠኛ ማን እንደሆነ ብናውቀው ጥሩ ነበር
June 5, 2011 1:35 AM
ETHIOPIA said…
እባካችሁን ወገኖቼ የምንጠላዉን ክፉ ሰው ደግ ሆኖ በንስሃ እንዲመለስ እንጸልይለት ሁላችን በኃጢዓት ረክሰናልና እርስ በእርሳችን ብንተማማ መልካም ነገር አይመጣልንም በቤተክርስቲያናችን አባቶቻችን መካከል ያለዉ አለመግባባት፣ እጅግ ልዩ የሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ለተዋህዶ እምነታችን የወርቅ ዓምድ በሆኑት ማህበረ ቅዱሳን ላይ እየደረሰ ያለው የማጥፋት ዘመቻ፣ በእመቤታችን ቅድስት ንጽህት ድንግል ማርያም ፣ በቅዱሳን መላእክት እና ጻድቃን ሰማዕታት ንጽህናና ቅድስና የቀደሙት ቅዱሳን አባቶቻችን ለቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችንና ቤተክርስቲያናችን ይበጃል ይጠቅማል ብለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሰሩልንን ፍጽምት ሥርዓት ዛሬ ሳይበቁ በቅተናል ብለው አንዳንድ አባቶችና ወንድሞች ቤተክርስቲያንን እናድሳታለን በሚል ክፉ መንፈስ ልዩ እንግዳ ትምህርት ከሚያስተምሩት ከክህደት ትምህርታቸው በንስሃ እንዲመለሱ ዘወትር በጾም በጸሎት ከንጹሕ እንባ ጋር ወደ አግዚአብሔር ልናቀርብ ያስፈልጋል ፡፡yared seyoum

June 5, 2011 4:54 AM
ETHIOPIA said…
እባካችሁን ወገኖቼ የምንጠላዉን ክፉ ሰው ደግ ሆኖ በንስሃ እንዲመለስ እንጸልይለት ሁላችን በኃጢዓት ረክሰናልና እርስ በእርሳችን ብንተማማ መልካም ነገር አይመጣልንም በቤተክርስቲያናችን አባቶቻችን መካከል ያለዉ አለመግባባት፣ እጅግ ልዩ የሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ለተዋህዶ እምነታችን የወርቅ ዓምድ በሆኑት ማህበረ ቅዱሳን ላይ እየደረሰ ያለው የማጥፋት ዘመቻ፣ በእመቤታችን ቅድስት ንጽህት ድንግል ማርያም ፣ በቅዱሳን መላእክት እና ጻድቃን ሰማዕታት ንጽህናና ቅድስና የቀደሙት ቅዱሳን አባቶቻችን ለቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችንና ቤተክርስቲያናችን ይበጃል ይጠቅማል ብለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሰሩልንን ፍጽምት ሥርዓት ዛሬ ሳይበቁ በቅተናል ብለው አንዳንድ አባቶችና ወንድሞች ቤተክርስቲያንን እናድሳታለን በሚል ክፉ መንፈስ ልዩ እንግዳ ትምህርት ከሚያስተምሩት ከክህደት ትምህርታቸው በንስሃ እንዲመለሱ ዘወትር በጾም በጸሎት ከንጹሕ እንባ ጋር ወደ አግዚአብሔር ልናቀርብ ያስፈልጋል ፡፡
yared seyoum
June 5, 2011 4:55 AM
ETHIOPIA said…
እባካችሁን ወገኖቼ የምንጠላዉን ክፉ ሰው ደግ ሆኖ በንስሃ እንዲመለስ እንጸልይለት ሁላችን በኃጢዓት ረክሰናልና እርስ በእርሳችን ብንተማማ መልካም ነገር አይመጣልንም በቤተክርስቲያናችን አባቶቻችን መካከል ያለዉ አለመግባባት፣ እጅግ ልዩ የሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ለተዋህዶ እምነታችን የወርቅ ዓምድ በሆኑት ማህበረ ቅዱሳን ላይ እየደረሰ ያለው የማጥፋት ዘመቻ፣ በእመቤታችን ቅድስት ንጽህት ድንግል ማርያም ፣ በቅዱሳን መላእክት እና ጻድቃን ሰማዕታት ንጽህናና ቅድስና የቀደሙት ቅዱሳን አባቶቻችን ለቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችንና ቤተክርስቲያናችን ይበጃል ይጠቅማል ብለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሰሩልንን ፍጽምት ሥርዓት ዛሬ ሳይበቁ በቅተናል ብለው አንዳንድ አባቶችና ወንድሞች ቤተክርስቲያንን እናድሳታለን በሚል ክፉ መንፈስ ልዩ እንግዳ ትምህርት ከሚያስተምሩት ከክህደት ትምህርታቸው በንስሃ እንዲመለሱ ዘወትር በጾም በጸሎት ከንጹሕ እንባ ጋር ወደ አግዚአብሔር ልናቀርብ ያስፈልጋል ፡፡yared seyoum

June 5, 2011 5:11 AM
Anonymous said…
ባለጌን ካሳደገ የገደለ ይጸድቃል፡፤ ሌላ ምንም አልልሽም ለንስሃ ሞት ያብቃሽ፤።አንችም ሰው መናቅ ይቅርብሽ ካላወቅሽ መጠየቅ አለብሽ።ማ ቅ የሚለውን ስም ራሳቸው ያወጡት አይደለም ብጹኣን ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው ።መዝገብ ቤቱ በጅሽ ስለሆነ ግቢና ተመልከች።
June 5, 2011 7:43 AM
Anonymous said…
ማነሸ ወ|ሮ እንዳልልሸ ቸገረኝ ጋለሞታም እንዳልልሸ
ስድብ ጥሩ እንዳልሆነ አዉቃለሁ ስመ አጠራርሸ
ቸገረኝ who are you?
እኔን እንዳቃጠልሽኝ ያቃጥልሽ ባልልሽም የሚቀዘቅዝ ነገር እንዲሰጥሸ የዘወትር ፀሎቴ ነዉ ቆይ ግን አንች ማነሽ እና ነዉ ጳጳስ ቤት እየገባሽ የምትባረኪዉ? ምን እሚሉት አይን አዉጣነት ነዉ? ሁሉን ሰጡሽ እንግዲህ የቀረሽ ስልጣኑ ነዉ በዉጭ እንደምየዉ ክነቱም ይስጡሽ ያልተሰራ ታሪክ የለም እኮ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሲጠፋ ሃይ የሚል ሰዉ ጠፋ ምን ያድርጉ በታሪኮ በገንዘቦ ይጫዉቱ እንጅ ምን አለ ስለ ካህናት ደመወዝ ተንታኝ ያደረገሽ ማን ነዉ
የድሮ አባቶች እኮ ለደምመወዝ ሳይሆን ለእግዚአብሄር ነበር
የሚገለግሉ ግን ሰዉየዉ ምን ነካቸዉ? ? ? እኛም ባያድለን ተጎዳን በትችት በሀሜት አለቅን በበረከት ፈንታ…
እሱም ዝም ብሎ ያየናል ጥሩዎችም እየሄዱ ነዉ ምን ይሻለናል?
June 5, 2011 9:51 PM
Anonymous said…
አወይ አለመታደል !!!!!!!! የዘመኗ ጉዲት!!! ትዝ ይልሻል ያኔ ገና ለውጥ ሳይመጣ? ግዮን ሆቴል
ማህሙድን እንዴት እንዳጠመድሽው?
ትዝ ይለኛል እኔም ሁለት ታናናሽ እህቶቼን ከት/ቤት
መልስ ግዮን ለዋና እወስዳቸው ነበር:: አርቲስት ማህሙድም ልጆቹን ያስዋኛቸው ነበር:: አጅሪትም
የማትቆፍሪው ነገር አልነበረም ከጥቂት ጊዜ በሁዋላ
አሜሪካ ኬንታኪ የማህሙድን ልጆች ላክሽ::
ይህንን ምስኪን በምን አጠመድሽው??
ማህሙድም ሚስቴ ወለደች ብሎ ደስታውን ሲነግርሽ አንችም ያደረግሽውን ታውቂዋለሽ
ያ አራስ ጥሪ ብለሽ የሰጠሽው አንሶላ!!!!!!!!!!!!!
ውስጡ ያስመተትሽበት የሰይጣን ስራ ለትዳሩ መበተን ምክንያት ነሽ:: በሰአቱ ማህሙድ የሚያውቀው ነገር የለም የአብርሃም በግ!!!!!!!!!!
አሁን ደግሞ ወደ ቤተ ክህነት ገብተሽ ማመስ ጀመርሽ:: ድሮም ቢሆን አምልኮትሽ የጣኦት ስለሆነ አሁንም ጣኦት አቆምሽ:: ቢያድልሽ ኖሮ ያለፈው በደልሽ በበቃ ነበር:: ማህበረ
ቅዱሳንን አላውቅም ብትይ አያስገርምም ለምን ብትይ በየ ጠንቋይ ቤት የሚያፈነድድ ሊያቀው አይችልም!!!!!!!!!!
June 5, 2011 11:46 PM
Anonymous said…
አወይ አለመታደል !!!!!!!! የዘመኗ ጉዲት!!! ትዝ ይልሻል ያኔ ገና ለውጥ ሳይመጣ? ግዮን ሆቴል
ማህሙድን እንዴት እንዳጠመድሽው?
ትዝ ይለኛል እኔም ሁለት ታናናሽ እህቶቼን ከት/ቤት
መልስ ግዮን ለዋና እወስዳቸው ነበር:: አርቲስት ማህሙድም ልጆቹን ያስዋኛቸው ነበር:: አጅሪትም
የማትቆፍሪው ነገር አልነበረም ከጥቂት ጊዜ በሁዋላ
አሜሪካ ኬንታኪ የማህሙድን ልጆች ላክሽ::
ይህንን ምስኪን በምን አጠመድሽው??
ማህሙድም ሚስቴ ወለደች ብሎ ደስታውን ሲነግርሽ አንችም ያደረግሽውን ታውቂዋለሽ
ያ አራስ ጥሪ ብለሽ የሰጠሽው አንሶላ!!!!!!!!!!!!!
ውስጡ ያስመተትሽበት የሰይጣን ስራ ለትዳሩ መበተን ምክንያት ነሽ:: በሰአቱ ማህሙድ የሚያውቀው ነገር የለም የአብርሃም በግ!!!!!!!!!!
አሁን ደግሞ ወደ ቤተ ክህነት ገብተሽ ማመስ ጀመርሽ:: ድሮም ቢሆን አምልኮትሽ የጣኦት ስለሆነ አሁንም ጣኦት አቆምሽ:: ቢያድልሽ ኖሮ ያለፈው በደልሽ በበቃ ነበር:: ማህበረ
ቅዱሳንን አላውቅም ብትይ አያስገርምም ለምን ብትይ በየ ጠንቋይ ቤት የሚያፈነድድ ሊያቀው አይችልም!!!!!!!!!!
June 5, 2011 11:47 PM
Anonymous said…
ለዚህ ደፋርነትሽ…ምናለበት አንቺንም ዘማሪ ፍቃዱ ሠርጉ ላይ ጠርቶሽ ቢሆን…የደብረ አሚን ተክለሃይማኖት የሃይማኖት ሰልፈኛ ወታደሮች ቢያገኙሽ!
June 6, 2011 12:52 PM
Anonymous said…
የዚያን ጊዜ እንዲያውም ከፓትሪያርኩ ጋር አንተዋወቅም፡፡ የሰጡኝ ብፁእ አቡነ ቄርሎስ ናቸው፡፡ ከዚህ ውጭ የተሰጠኝ ቤት የለም፡፡lemehonu anchi maneshena new betu yetesetesh.Abune kerlos degmo endeanchi ayenetuan ye betekirsitiyan telat yemewagu enji anchin yemedegifu aydelum.mahibere kidusanenma endet tawekewalesh? haweltun man yaseraleshal.you are so buzzy.anyways today is the time to say good bye for you and for your groups.you bettter to stop this kind of corruption.alebeleziya anchim bezih edmesh endene dagmawi derebe dula yeketeleshal.
June 6, 2011 9:20 PM
Anonymous said…
how old u said 66 but u are 666
June 8, 2011 3:45 AM
Anonymous said…
አፈር ድ’..ሜ ብይ!
ከሐረርr
June 8, 2011 11:08 AM
Anonymous said…
Dear dejeselam
I came to know this lady 5 years ago in San Jose California in st Mariam church USA.She was telling people that the Ethiopian Orthodox followers should nominate Abune Poulos as saint and sculpture TABOT in his name.SO do not be surprised by what she is doing now.By that time she was telling people that she is a close relative to Abune Poulos
June 17, 2011 3:56 PM
እዉነት said…
እዉነቶን ሊሆን ይችላል ነገር ግን ህዝብን እየፈተነ ያለዉ ሰይጣን እርሶን በመሳሪያ ነት እንዳይጠቀምባት ደግሞም ፈተናዉ እስከሚያልፍላት ራቅ ብላ ከቤተ ክህነቱ አካባቢ ባትታይ እመክራታለሁ በእርግጠኛነት ምንም ስለ ሐይማኖት ቅዉቀት ስለሌላት ሊፈረድባት አይገባም እና እባክሽ ራቅ በዬ ! ! !
Related stories   የበልግ ዝናብ በአንዳንድ አካባቢዎች ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ