ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

ኢትዮጵያና ግብፅ ድርድሩን ለመቀጠል ተስማሙ

4ff28a9823b64d31d17bd0411c6126bd_XL

 

 

ከትናንት ሰኔ 10/2005 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ አበባ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስተሮች ደረጃ ሲወያዩ የነበሩት ኢትዮጵያና ግብፅ ግድቡ በግብፅና በሱዳን ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተፅእኖ እንዲገመግም የተቋቋመው ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ያስቀመጣቸውን የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ ለመደራደር ተስማሙ፡፡

ከውይይታቸው በኋላ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴውድሮስ አድሓኖምና የግብፅ አቻቸው መሀመድ ካመል አሚር በጋራ በሰጡት መግለጫ የባለሙያዎቹ ቡድን ባቀረበው የመፍትሄ ሀሳብ መሰረት የግድቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተፅእኖዎች ለማወቅ ተጨማሪ ጥናት ለማካሄድ አገራቱ ተስማምተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ መቀላጠፍ የወንዙን ተፈጥሯዊ አቅጣጫ ካስቀየረች በኋላ በአንዳንድ የግብፅ ፖለቲከኞችና ባለስልጣናት አፍራሽ የሆኑና የሁለቱን አገራት ግንኙነት የሚጎዱ አስተያየቶች ሲሰጡ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

በምንም መልኩ የግድቡ ግንባታዋን ለሰከንድ እንኳን እንደማታቆም የገለፀችው ኢትዮጵያ በፖለቲከኞቹ ባለስልጣናቱ አስተያየት ላይ ግብፅ ማብራሪያ እንድትሰጣት በይፋ ጠይቃም ነበር፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲም እንደገለፁት ግብፅ ማብራሪያውን ለመስጠት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ወደ አዲስ አበባ ኢንዲመጡ በጠየቀችው መሰረት ነው ሞሀመድ ካመል አሚር ወደ መዲናችን የመጡት፡፡

 

ምንጭ-ኤፍ.ቢ.ሲ

Share and Enjoy !

0Shares
0
0Shares
0
Read previous post:
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ JUNE 17, 2013  "የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን...

Close