የኢትዮጵያውያን የጡት ካንሰር ፋውንዴሽን በአትላንታ ተቋቋመ፣ ዓለምፀሐይ የጡት ካንሰር ፋውንዴሽን ምስረታ
ቅዳሜ፣ ሰኔ 15፣ ቀን 2013 ዓም በአትላንታ ከተማ “የዓለምፀሐይ የጡት ካንሰር ፋውንዴሽን” (Alemtsehay Breast Cancer Foundation) መመሥረቱን ወ/ሮ ፊፊ ደርሶ ለኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አስተዋውቀዋል። የፋውንዴሽኑም የመጀመርያ ስብስባ የተደረገው በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማዕከል ነበር። በስብሰባው የተገኙት ተሳታፊዎች በአትላንታና በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፣ ስለፋውንዴሽኑ መመስረት እጅግ መደሰታቸውንና ሙሉ በሙሉም ድጋፋቸውን የሚለግሱ መሆናቸውን ገልጸዋል። ከተሰበሰቡት መካከል 3ቱ ከካንሰር ህመም የዳኑ (survivors) መሆናቸውን ሲናገሩ፣ “ድርጅቱ አስፈላጊና ወቅታዊ መሆኑን አስረድተዋል። በዋና ተናጋሪነት የተጋበዙት ወ/ሮ ለምለም ጸጋው ከዋሽንግተን ዲሲ ነበሩ።