የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ጸሐፊ ሰለባ ሆኑ! ም/ፕሬዚዳንቱ እንዲነሱ የቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሆነ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ላጠፋው ጥፋት ጸሐፊውን አቶ አሸናፊ እጅጉን ከስራ በማባረር ፣ምክትል ፕሬዚዳንቱና የቡድን መሪ የነበሩትን አቶ ብርሃኑ እንዲነሱ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አደረገ። አስቸኳይ ስብሰባ የተጠራው የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው እለት ያሳለፈው ውሳኔ ስብሰባ የማያስፈልገው እንደሆነ ተጠቁሟል። ተመጣጣኝ ቅጣት ይጥላል ተብሎ የተጠበቀው የካድሬዎች ስብሰባ ተቀጣሪውን ጸሐፊ በማሰናበትና አቶ ሰውነት ቢሻው ” ህዝባዊ አደራቸውን እንዲወጡ በማሳሰብ ተጠናቋል። በሰዓታት ልዩነት ኢሬቲድ የዘገበው ዘገባ እንዲህ ይነበባል። ፌዴሬሽኑ በነሃሴ ወር አጠቃላይ ጉባኤውን ያካሂዳል ተብሏል። 

images (3)

 

 

 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ሰኔ 17/2005 ዓ/ም በጠራው አስቸኳይ ጉባኤ የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃኑ ከበደ ከሀላፊነታቸው እንዲነሱ ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስቸካይ አጠቃላይ ጉባኤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ብድን ያለአግባብ ተጫዋች ማሰለፍ ተከትሎ ያጋጠመው ችግር ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡ጉባኤው ችግሩ መፈጠር ያልነበረበትና አሳዛኝ ድርጊት መሆኑን በመግለፅ ለዚህም ሀላፊነቱ  ፌደሬሽኑ መውሰድ ይኖርበታል ብሏል፡፡

አሁን ብሄራዊ ቡድኑ አስፈላገው ዝግጅት በማድረግ ያለው ሙቹ አጋጣሚ በመጠቀም ሴንትራል ሪፐብሊክ አፍሪካ በማሸነፍ ለጥሎማለፍ ጨዋታ ማለፍ ይኖርበታል፡፡ለዚህም ቡድኑ አስፈላጊውን ዝግጅት ከወዲሁ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የጠራው አስቸኳይ ጉባኤ ሲጠናቀቅ የፌደሬሽኑ ፕሬዝደንት ሳህሉ ገብረወልድ እንዳሉት በፌደሬሽኑ የሚታዩት በግልፅነት አሰራር፣ አደረጃጀት ፣ ከሚዲያ ጋር ያለው ግንኙነት በማጠናከርና በቂ መረጃ በግዜው ለሚመለከተው አካል በማድረስ ላይ  የሚታዩት ችግሮች ለመቅረፍ በትኩረት ይሰራል፡፡

ከደቡብ አፍሪካ የሚነሳው የ 3 ነጥብ ይገባኛል ጥያቄ አንድ ተጫዋች ሁሌቴ ስለማይቀጣ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ስጋት  በፊፋ እልባት እንደተሰጠበት አቶ ሳህሉ አረጋግጠዋል፡፡

በነሃሴ ወር መጨረሻ 2005 ዓ/ም የሚካሄደው የፌደሬሽኑ አጠቃላይ ጉባኤ ለማሳካትም አስፈላጊው ዝግጅት እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

የኢትየጵያ ብሄራዊ ቡድን በቀሪው ጊዜ አስፈላገውን ዝግጅት በማድረግ ለቀጣይ ውድድር ለማለፍ ፌደሬሽኑ አስፈላገው ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግም አቶ ሳህሉ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ብድን አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው  በድኑ የሚጠበቀው ጥረት በማድረግ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገውን ነጥብ ለማምጣት አስፈላጊውን ርብርብ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡

የፌደራል ስፖርት ኮሚሽነር አብዲሳ ያዴታ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በዘርፉ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ለስፖርቱ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው መገናኛ ቡዙሃን የተቀናጀ ግንኙነት በመፍጠር በጋራ ለዘርፉ እድገት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል ኮሚሽነር አብዲሳ  ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሀፊ ከስልጣናቸው ተነሱ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ የፌዴሬሽኑን ዋና ጸሀፊ አቶ አሸናፊ እጅጉ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ወስኗል፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን በብራዚሉ የ2014ቱ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ላይ ከቦትስዋና ባደረገው ጨዋታ ላይ ሁለት ቢጫ እያለው በስህተት የተሰለፈውን ተጫዋች ምክንያት በማድረግ ሶስት ነጥብና ሶስት ጎል ተቀንሶበታል፡፡

ይህንንም ምክንያት በማድርግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቅርቡ በሰጠው መግለጫ ችግሩን ለማጣራት እንደሚሰራ መግለጹን ተከትሎ በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሀፊ አቶ አሸናፊ እጅጉን ከስልጣናቸው አንስቷል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ብርሃኑ ከበደ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ያቀረቡት ጥያቄ ስራ አስፈጻሚው አጽድቆታል፡፡ጠቅላላ ጉባዔው እንደቀጠለ ነው፡፡/ ኢሬቴድ/

ሰይፉ አለምሰገድ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *