ዛጎል ዜና፡- ዛሬ የኦሮሚያ ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ በማካሄድ ላይ ነው። በጉባኤው የአዲሶቹ ሁለት ፐሬዚዳንቶች ሹመት የሚጸድቅ ሲሆን ፋና እንዳለው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ የክልሉ ሚና ምን ሊሆን እንደሚገባ ይመክራል። እንደ ዘገባው አፈ ጉዳኤ አባዱላ ገመዳ ማብራሪያ አቅርበዋል። በማብራሪያቸው አሁን በአገሪቱ አንጻራዊ ሰላም መኖሩን አስታውቀዋል።

በክልሉ የተጀመረውን “ተሃድሶ” የሚያጠናክር ሹም ሽር የሚካሄድበት ይህ ጉባኤ ከወዲሁ እነ ማንን ከሃላፊነት እንደሚያሰናብትና እነ ማንን እንደሚሾም ፍንጭ አልተሰጠም። ይሁን እንጂ የድርጅቱ የስራ አስፈጻሚና የኢህአዴግ ምክር ቤት አባል የሚሆኑት ቁልፍ ሰዎች በአዲስ ይተካሉ የሚለው ግምት ሚዛን የሚደፋ እንደሆነ ይታመናል።

Related stories   ትህነግ ከትግራይ አስተዳደር ጋር መሳሪያ አስረክቦና ጦሩን በትኖ እንዲደራደር ታስቧል፤ መንግስ የተረፈውን ሃይል ሊያጸዳ ነው

ኦህዴድ የዞንን የወረዳ በተለይም የበታች መዋቅሩ እንዳፋነገጠ የሚያውቁ ሹም ሽሩ አስቸኳይ ለውጥ ሊያመጣ እንደማይችል እየገለጹ ነው። በክልሉ የተነሱት ጥያቄዎች በጥገናዊ ለውጥ የሚመለሱ ሳይሆኑ የፖሊሲና የአገዛዘ ለውጥ ስለሚሹ አሁን የሚደረገው እንቅስቃሴ ዋጋ ቢስ እንደሆነ የተቃውሞው አስተባባሪዎች በስፋት እየወተወቱ ነው። እነሱ ይህን ይበሉ እንጂ ኢህአዴግ አስቸኳይ አዋጁ ውጤት አስመዝግቧል ባይ ነው።

በክልሉ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎች ብዛት ቢያከራክርም ቀላል ቁጥር የሌላቸው ዜጎች ስለመገደላቸው ስምምነት አለ። በተለይም በኢሬቻ ክብረ በአል ላይ የተፈጸመው ግድፈትና ያስክተለው ዘግናኝ አደጋ በኦሮሚያ ውስጥ ኢህአዴግ እንዳከተመለት አመላካች እንደሆነ የሚጠቁሙ ወገኖች ” አሁን ኢህአሃግ እስከ ቀጣዩ ምርጫ ቢደርስ እንኳን ማን ይመርጠዋል” ሲሉ በሁሉም አግባብ የኢህአዴግንና የኦሮሞ ህዝብን ፍቺ ያረጋግጣሉ።

Related stories   የኢዜማ 23 የፓርላማ እጩዎች እነማን ናቸው?

የሞት ሙሾ እየተደረደረለት ያለው ኢህአዴግ በበኩሉ ለተፈጠረው ቀውስ ” ተጠያቂ እኔ አይደለሁም” በሚል የተፈጠረውን አለመግባባት ለማሻር ” በጥልቅ ታድሼ አገልጋያችሁ እሆናለሁ” ሲል ቃል ገብቶ ያዋጣኛል ያለውን እያከናወነ ነው። ከመታደሱ ጋር ይገናኝ አይገናኝ በውል ባይታወቅም አስቸኳይ ጊዜ መቋቋሙ ግን በሁሉም ዜጎች፣ ብሎም በለጋሽ አገራት አልተወደደም። የተባበሩት መንግስታትም ቢሆን ቅሬታውን በማስጠንቀቂያ መልኩ ይፋ አድርጓል።
ፋና የሚከተለውን አጭር ዜና አትሟል።
ጨፌ ኦሮሚያ 5ኛ የስራ ዘመን ሁለተኛ አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ ጀምሯል። በአዳማ ጨፌ አዳራሽ ለሁለት ቀናት የሚቆየው አስቸኳይ ስብሰባ በአገራዊ እና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማካሄድ ጀምሯል። በወቅታዊ ጉዳዮች ላይም የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

Related stories   በኢትዮጵያ የትግራይ ጉዳይ ላይ የጸጥታው ምክር ቤት ሳይስማማ ተበተነ፤ አማራ ትህነግን በህግ ሊጠይቅ ነው

በዚህም ወቅት እንዳሉት በአገሪቱ ህገ መንግስት መሰረት በመላው አገሪቱ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በክልሉ ብሎም በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋትን አምጥቷል። ጨፌው በአሁኑ ወቅት ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈፃፀምና የጨፌ አባላት ሚና ዙሪያ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል። በአስቸኳይ ስብሰባው ጨፌው የተለያዩ ሹመቶችን ያጸድቃል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *