“Our true nationality is mankind.”H.G.

ኦሮምያ – ከውስጥ በተሃድሶ፣ ከውጭ ለለውጥ!!

ኦሮምያ – ከውስጥ በተሃድሶ፣ ከውጭ ለለውጥ

በኦሮሚያ አገር ቤት በ” ጥልቅ ተሃድሶ” ፣ ከውጪ ደግሞ “በቃን” በሚሉ ዜጎች የሽግግር ጊዜ ዝግጅት ድግስ ላይ ያለች ትመስላለች። ዓመት ግድም የቆየውንና በቀላሉ ሊገለጽ የማይችል ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ የነበረችው ኦሮሚያ ዛሬ አዲስ መሪና አዳዲስ ካቢኔዎች ተሰይሞላታል። በተመሳሳይ ሎንዶን ላይ ደግሞ ስለ መጪው እድልዋ እየተመከረላት ነው።

የፖለቲካ ክፍተትና የርስ በርስ አለመስማማት ሲያይልበት ሁሌም ተሃድሶ የሚያካሂደው ኢህአዴግ፣ ከዓመት በላይ ለቆየው የከፋ ቀውስ መድሃኒት አድርጎ የወሰደው ሹም ሽርን ነው። ለዚህም ይመስላል ኦሮሚያ አዲስ መሪዎችና አዳዲስ ካቢኔ እንድትሰይም ሆናለች።

የክልሉ መሪ የሆኑት አቶ ለማ መገርሳ የኦህዴድ ነባር ሰው እንደመሆናቸውና በተለያዩ መዋቅሮች እንደማገልገላቸው ሃላፊነቱ እንደማይበዛባቸው የሚያውቋቸው ይናገራሉ። ሆኖም ግን ሹመቱን ያገኙት ታማኝ በመሆናቸው ነው ሲሉ መልሰው ያሙዋቸዋል።  አቶ ኡምር ሁሴን ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ደመላሽ ገብረሚካኤል የክልሉ የአስተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ጨምሮ 18 የካቢኔ አባላት የተሰየመላት ኦሮሚያ በቀጥይ ከጠባሳዋ አሽራና እንዴት ተረጋግታ ተቀጥላለች የሚለው በሂደት የሚታይ ይሆናል።

Related stories   የኢትዮዽያ የቁርጥ ቀን ልጅ "ስለአባይ እውነቱን እንካችሁ" – መካ አደም አሊ

አቶ ለማ የመልካም አስተዳደርን ለማስፈንና በክልሉ ያለውን ስራ አጥነት ለመቅረፍ እንደሚተጉ መግለጻቸውን ፋና አመልከቷል። እሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ የድርጅቱን የበታች መዋቀር አሰባስቦ ወደ ቀድሞው ቦታ መመለስ እጅግ አስቸጋሪ እንደሚሆን፣ የፈሰሰው ደም፣ በኢሬቻ ክብረ በአል ወቀት የሆነው አንድ ላይ ተዳምሮ የፈጠረውን የጎሸ ስሜት መፈወስ፣ ከሁሉም በላይ የተነሳውን የለውጥ ፍላጎት ማክሰም ቀላል እንደማይሆን ከወዲሁ አውሮፓና አሜሪካ የሚቀመጡ የክልሉ ተወላጆች እየተናገሩ ነው።chefe_3

ኦህዴድን አብዝተው የሚቃውሙትና በከሃጂነት የሚፈረጁት ክፍሎች ” ኦሮሚያ ለውጥ ስለመፈጠሩ ሳይጠራጠሩ የናገራሉ” መናገር ብቻ ሳይሆን የራሳቸውን መተዳደሪያና አገር መመስረቻ ሰንድም እያዘጋጁ መሆናቸውን ያወሳሉ።

ኦህዴድ እንዳበቃለትና ወደ መቃብር እየወረደ እንደሆነ እምነት ተይዞ ባለበት በዚህ ወቅት ትሃድሶውን ከአናቱ የጀመረው ኦህዴድ በክልሉ የተፈጠረውን ችግር ፈቶ ” ልማታዊነቱን” እንደሚያሳይ በሙላት በአገር ቤት መገናኛዎች እየተነገረ ነው። በኦህዴድ ብቻ ሳይሆን ድፍን ኢህአዴግ ” ጥልቅ ተሃድሶ”አካሂዶ የወየበውን ገጹን እንደሚያበራ እየመሰከረ ነው።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

ለሁሉም ግን ከተሃደሶና ከለውጥ ለኦሮሚያ ቀድሞ የሚደርስላት የቱ ይሆን?

የካቢኔ አባላት እና የተለያዩ የክልሉ መንግስት መስሪያ ቤት ሃላፊዎች ዝርዝርም ለጨፌው በማቅረብ አስፀድቀዋል። በዚህም መሰረት
1 አቶ ኡመር ሁሴን ፦ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር
2 አቶ አብይ አህመድ፦ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት እና ቤቶች ቢሮ ሃላፊ
3 አቶ ስለሺ ጌታሁን፦ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የእርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሃላፊ
4 አቶ ቶሎሳ ገደፋ፦ የክልሉ የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሀላፊ
5 አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ፦ የክልሉ የፍትህ ቢሮ ሃላፊ
6 ዶክተር ደረጄ ጉደታ፦ የክልሉ የጤና ጥበቃ ቢሮ ሃላፊ
7 ዶክተር ሀሰን የሱፍ፦ የክልሉ የደን እና አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ቢሮ ሃላፊ
8 አቶ ሀብታሙ ሀይለሚካኤል፦ የክልሉ የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ
9 አቶ ደመላሽ ገብረሚካኤል፦ የክልሉ የአስተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ
10 ወይዘሮ ሎሚ በዶ፦ የክልሉ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ
11 አቶ አሰፋ ኩምሳ፦ የክልሉ የውሃ፣ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ
12 ወይዘሮ አዚዛ አብዲ፦ የክልሉ የሴቶች እና የህፃናት ቢሮ ሃላፊ
13 አቶ ወንድማገኝ ነገራ፦ የክልሉ ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ሃላፊ
14 አቶ ካሳዬ አብዲሳ፦ የክልሉ የቴክኒክና ሙያ ቢሮ ሀላፊ
15 አቶ ብርሃኑ ፈይሳ፦ የርዕሰ መስተዳድሪ ጽህፈት ቤት ቢሮ ሃላፊ
16 አቶ ኤልማ ቃጴ፦ የክልሉ ዋና ኦዲተር
17 ወይዘሮ ሂሩት ቢራሳ፦ የክልሉ የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር
18 አቶ ጌቱ ወዬሳ፦ የኦሮሚያ ራዲዮ እና ቴሌቭዥን ድርጅት ዋና ዳይሬክተር
ሆነው እንዲሾሙ የቀረቡ ሲሆን፥ ተሿሚዎቹ የዳበረ የሥራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት ያላቸው መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ለማ መገርሳ ለጨፌው አቅርበዋል። የጨፌው አባላት ሹመቱን በሙሉ ድምጽ አጽድቀውታል።

Related stories   እስራኤል አልጃዚራ ቴሊቪዥን፣ አሶሲየትድ ፕሬስና ሌሎች ሚዲያዎች የሚጠቀሙበትን ህንጻ አወደመች

የተሷሚዎች ዝርዝርና ምስል ከፋና በሮድካስቲንግ የተገለበጠ

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0