” የጉዞ ማስጠንቀቂያውን ደግመን አናይም፣ አናደርገውም” አሚሪካ

አሜሪካ ለዜጎቿ የሰጠችው የጉዞ ማስጠንቀቂያ በኢህአዴግ ዘንድ አልተወደደም። የኮሙኒኬሽን ጉዳይ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ውሳኔውን የተቃወሙት ባለተለመደ ሁኔታ ነው። ሚኒስትሩ ተቃውሟቸውን የገለጹት ” ወሳኔው የተሰጠው የኢትዮጵያን ሰላምና መረጋጋት ከማይፈለጉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰዎች ነው” በማለት ነበር። ይሁንና አሜሪካ ውሳኔው ጥንቃቄ የተሞላበትና እንደገና የሚፈተሽ ጉዳይ እንዳልሆነ ነው ያስታወቀችው።

የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ማክሰኞ በተለያዩ የዓለማችን ጉዳዮች ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ መሰጠቱን ፣ በመግለጫውም የኢትዮጵያ ጉዳይ ተነስቶ እንደነበር በማስታወስ የቪኦኤ የአማርኛ ክፍል እንዳለው ፣ ማብራሪያውን የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ ” የጉዞ ማስጠንቀቂያውን ዳግም መመልከት አያስፈልግም። አናደርገውም” በማለት ነበር በቀጥታ የመለሱት።

“በኢትዮጵያ ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ ሰዎች የሚከናወነው እስር። የኢንተርኒት መዘጋት፣ የህዝባዊ ስብሰባዎች መከልከል፣ የሰዓት እላፊ አዋጁና የመናገር ነጻነት ማዕቀብ የሚያስከትለው ውጤት እንደረበሸን አለ”ሲሉ አሜሪካን ኢትዮጵያ ውስጥ በሚሆነው ሁሉ ስጋት እንዳለባት የጠቆሙት ቃል አቀባዩ የጉዞ ማስጠንቀቂያው በቀላሉ እንዳልወጣ አመልክተዋል።

እንዲህ ያለው ማስጠንቀቂያ በመላው ዓለም ላሉ አገሮች ሁኔታዎች በጥንቃቄ እየታዩ የሚከናወን ጉዳይ መሆኑንን የጠቆሙት ቃል አቀባዩ፣ ” ኢትዮጵያ የተለየች አይደለችም” ብለዋል። አሜሪካኖች በየትኛውም ዓለም ሲንቀሳቀሱ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ምክርና ማስጠንቀቂያ መስጠት የተለመደ እንደሆነም ተናግረዋል።

አለመታደለ ሆኖ አሜሪካውያን ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን የጉዞ እቅድ እንዲሰርዙ የተወሰነው የአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት የማያስደስታቸው የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አንዳንድ ሰዎች ፍላጎት እንደሆነ አቶ ጌታቸው መናገራቸው ለፖለቲከኞች ለዩ ትርጉም እየሰጠ ነው። ለወትሮው ተመሳሳይ ቃል የሚናገሩት የሁለቱ አገራት ባለስልጣናት ወደ እንዲህ መሳዩ ፍረጃ መዞራቸው ” ቀጣዩ ምን ሊሆን ይችላል?” የሚል ብልጭታን ፈጥሯል።

የቀድሞው ስዓት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ሰሞኑን ቪዥን ኢትዮጵያ ባዘጋጀው መድረክ ላይ አሜሪካ ያወጣችው የጉዞ ማስጠንቀቂያ በቀላሉ የሚታይ እንዳልሆነ ተናገረዋል። ማስጠንቀቂያው አሜሪካን ለሚሰሙ አገሮች ሁሉ የሚያገለግል በመሆኑ ጫናው የከፋ እንደሆነም አክለው ገልጸዋል።

Related stories   በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ፍተሻ ተጀመረ

ጆን ከርቢ ” እንሱ ካወጡት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንጻር ሲታይ የእኛ ማስጠንቀቂያ የተሻለ ነው” በለዋል። አቶ ጌታቸው በበኩላቸው አዋጁ ውጤታማና በአገሪቱ ሰላም ማስፈን እንደቻለ አስረግጠው ነው የተናገሩት። የቪኦኤን ዚና ያድመጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *