“ኢህአዴግን የገጠመው የፖለቲካ ክህደት ነው፣ ክህደት በሹም ሽር አይድንም”
“…ዋናው ችግር ስልጣንን የራስ ጥቅም ማስፈፀሚያ ያደረጉ ግለሰቦችን ከስራ አስፈፃሚ እስከ ተቋማት አቅፈን መያዛችን ነው “
ኢህአዴግ ለ”ጥልቅ ተሃድሶ” ደፋ ቀና በሚልበት በአሁኑ ወቀት የተቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶች ውህደትና የሽግግር ቻርተር በማዘጋጀት ተጠምደዋል። ሁሉም በየፊናቸው የተሃድሶና የቻርተር ቀረጻ ስራ ላይ ቢጠመዱም ሁለቱም ወገኖች ላይ አስተያየት እየተሰጠ ነው። ኢህአዴግ ያጋጠመው የፖለቲካ ክህደትና መንሸራተት በመሆኑ በሹም ሽር መታደስ እንደማይችል እየተጠቆመ ነው። ኢህአዴግ ስለ ” ጥልቅ” ተሃድሶ ማውራት ከጀመረበት ቀን አንስቶ ተቃውሞ ቢሰነዘርበትም ቤቱን ባስቸኳይ አዋጅ ዘግቶ ነገ የካቢኔ ሹም ሽር ለማድረግ መዘጋጀቱ ይፍ ሆኗል።

እነማ ተነስተው እነማ ወደ መድረክ ይመጣሉ የሚለው በግልጽ ባይለይም ፋና እንደዘገበው ከሆነ የሚሰየመው አዲስ ካቢኔ ነው። አዲስ ካቢኔ ይሰየማል ከተባለ የቀድሞዎቹ ይነሳሉ ማለት ነው። በዚህ መነሻ እነማን ካቢኔ ሆነው ይመጣሉ የሚለው ለራሱ ለኢህአዴግ ሰዎች ነገን የሚጠበቅ ቀን አድርጎታል።
በሌላ በኩል ኢህአዴግ በአባል ድርጅቶቹ የፖለቲካ ክህደት እንደተፈጸመበት የሚገልጹ ” አሁን ጉዳዩ ሁሉ ወደ ዘር ዘሟል። ከኢህአዴግነት ይልቅ ሁሉም ወደ ዘር ቋት መሳቡ የቀድሞው የኢህአዴግ ቅርጽ አለ ማለት አይቻልም” ሲሉ ይደመጣል። በተለያዩ ሚዲያዎችና ውይይቶች እንደሚነሳው ተሃድሶ ኢህአዴግን አያጠራውም።

ኢህአዴግ በበኩሉ ባካሄዳቸው መድረኮችና በራሱ ሚዲያዎች የምርጫ ስርዓቱን ከመለወጥ ጀምሮ ሹመት በሜሪት ለማድረግና ከተቀናቃኝ ድርጅቶችም ብቁ የሆኑ ሰዎችን ወደ መንበር እንደሚያመጣ፣ በዚህ አካሄድና ድርጅቱ በግል ውስጡን በማጥራት በአውራ ፓረቲነቱ እንደሚቀጥል አለሞ የጀመረውን ጉዞ በኮማንድ ፓስት አጃቢነት ገፍቶበታል።
በተመሳሳይ አራት ፓርቲዎች ስምምነት ላይ መድረሳቸው ደጋፊዎችን አስጨብጭቧል። ውህደቱ ቀጥይነት እንደሚኖረው የተገለጽ ሲሆን ስምምነት የፈጠሩት ድርጅቶች የፊርማ ስነስርዓት ሲያካሂዱ ታይቷል። ኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር፣ አርበኞች ግንቦት ስባት፣ የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር፣ የሲዳማ ሃርነት ንቅናቄ መሪዎች ስለውሃደቱ የበኩላቸውን ብለዋል። አንዳንድ እንደ ኦጋዲን ነጻ አውጪ ግንባር አይነት ድርጅቶች ኢትዮጵያ የሚለው ጉዳይ ላይ ተአቅቦ ማድረጋቸው ተጠቁሟል።
በተመሳሳይ የኦሮሚያን የሽግግር ሰነድ ለማዘጋጀት ደፋ ቀና የሚሉት በበኩላቸው በሎንደኑ ጉባኤ በጭብጨባ ሲያስተናገዱት ከነበረው የ”ኢትዮጰያ ትበታተን” ዲስኩር ስለመላቀቃቸው በይፍ ባይቃውሙም ጉዳዩ ውስጣቸው መካከል፣ በተለይም የሸዋ ኦሮሞዎችን ክፉኛ ቅር አሰኝቷል። ዛጎል እዚህ ጉዳይ ላይ ዝርዝር ዜና ታቀርባለች።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ፋና በሮድካስት አዲስ ካቢኔ ነገ ቀርቦ እንደሚጸድቅ ያስነበው ዜና ሙሉ በሙሉ እንደሚከተለው ይነበባል።

አዲስ የሚዋቀረው ካቢኔ ጥገናዊ ሳይሆን ስር ነቀል ለውጥን የሚያመጣ መሆን እንዳለበት ምሁራኑ ተናገሩ
አዲሱ የፌደራል መንግስት ካቢኔ ነገ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብ ይጠበቃል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው ምሁራን መንግስት የተሃድሶ አንድ አካል ነው ያለው፥ አስፈፃሚውን አካል የማዋቀር ውሳኔ ጥገናዊ ሳይሆን ስር ነቀል ለውጥን የሚያመጣ መሆን አለበት ብለዋል።
ምሁራኑ እንደሚሉት መንግስት ስር ነቀል ለውጥ በማምጣትና አጠቃላይ ችግሮቹን ነቅሶ በማውጣት አዲስ ነገር መፍጠር መቻል አለበት። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፥ ከወራት በፊት የፌደራል መንግስቱን ካቢኔ እንደ አዲስ ማዋቀር የተሃድሶ እንቅስቃሴው አንድ አካል ይሆናል ብለው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በገቡት ቃል መሰረት አዲሱ ካቢኔያቸውን ነገ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ካሁን ቀደም ባደረጉት ንግግር የመንግስት ዋናው ችግር ስልጣንን የራስ ጥቅም ማስፈፀሚያ ያደረጉ ከስራ አስፈፃሚው እስከ ተቋማት አመራር ያሉ ግለሰቦችን አቅፎ መያዙ ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት እና ስትራቴጂ ጥናት ኢኒስቲቲዩት የከባቢያዊ ፖለቲካ ጉዳዮች ምርምር ክፍል ሃላፊ አቶ አበበ አይነቴ እንደሚሉት፥ መንግስት በፖለቲካ አባልነት እና በብሄር ተዋጽኦ ሽፋን የሚደረገውን ስልጣንን ያለ አግባብ የመጠቀም ችግር ተገንዝቦ ችግሩን እፈታዋለሁ ማለቱ የችግሩ መፍትሄ መጀመሪያ ነው።
የሶስተኛ ዲግሪ እጩ የሆኑት አቶ ሙሉቀን ሀብቱ በበኩላቸው፥ እውነተኛ ለውጥን ያለመ መንግስት ጥገናዊ ለውጥን ሳይሆን ስር ነቀል የሚያመጣ መታደስን ያድርግ የሚል ሃሳብ አላቸው። ቃል በመግባት አደርገዋለሁ ማለት ብቻ ሳይሆን፥ ትክክለኛ ምላሽ መስጠት እንዳለበት በመጥቀስ።
የመታደስ ጅማሮው ስልጣንን የግል ጥቅም ማስፈፀሚያ ያደረጉ ሹመኞችን በማንሳት የሚቆም ሳይሆን፥ ህዝቡ ያነሳቸውን ጥያቄዎች የሚመልስ መሆን አለበት የሚለውም የምሁራኑ ሃሳብ ነው። አቶ ሙሉቀን መንግስት የህዝብ ጥያቄ የሆኑትን የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር እጦት ጥያቄዎችን ለመመለስ እና ለማረጋገጥ መስራት እንዳለበት ይገልጻሉ።
መንግስት አደርገዋለሁ የሚለው ለውጥ መሰረታዊ ግቡ የህዝብን ፍላጎት የሚያሟላ አመራርን ማምጣት መሆን አለበት የሚሉት አቶ አበበ ደግሞ፥ አሁን ቃል መግቢያ ሳይሆን የተግባር ወቅት በመሆኑ መሬት የወረደ የተግባር ለውጥ ያሻል ነው ያሉት።
ተግባራዊ እርምጃው አመራሩን ከአንዱ ወደ ሌላ ቦታ ማዛወር ሳይሆን፥ ህዝቡን አዳምጦ ምላሽ የሚሰጥ አመራር በክህሎት እና እውቀት መዝኖ የሚገባውን ስፍራ ማስቀመጥ መሆን አለበት የሚል ሃሳብም በምሁራኑ ተነስቷል።
አዲስ ካቢኔ ማዋቀርን የችግሮች ሁሉ መፍቻ አድርጎ ማሰብ ተገቢ አይደለም የሚሉት አቶ ሙሉ ቀን፥ መንግስት የካቢኔ ሹም ሽር ማድረግን ለጥያቄ ምላሽ መስጫ መንገድ አድርጎ መመልከት እንደሌለበትም ተናግረዋል።
ከዚያ ይልቅ ዘላቂ ተቋማዊ የአሰራር ስርዓትን መዘርጋት እና የማያሰሩ ስልቶችን መለወጥ ለዘላቂ መፍትሄው አስፈላጊ መሆኑን ያስረዳሉ። ምሁራኑ ተቋማትን በተዘረጋ ስርዓት በመምራት መንግስት ቀጣይነት ያለው ሂደት ማድረግ መቻል እንዳለበትም አንስተዋል.

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

………………………………………………………………………………………………………..

ከሚነሱት የካቢኔ አባላት ቁርጠኛነታቸው እየተታየ አዲስ ምደባ ይሰጣቸዋል ይላሉ አቶ ጌታቸው። አያየዘውም በከፍተኛ ሃላፊነት የማይታወቁ ሰዎች ወደ ካቢኔነት እነደሚመጡም አመልክተዋል። የኢዜአ  እንዲህ ይነበባል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መንግስት ለያዛቸው እቅዶች ስኬት የሚጥር ለህዝብ ጥያቄዎች ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራና ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ አዲስ ካቢኔ እንደሚያዋቅሩ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ገለፀ። የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ እንዳሉት፥ ከነገ ጀምሮ በሚካሄደው የፓርላማ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ የካቢኔ አባላትን መርጠው ለምክር ቤቱ ያቀርባሉ።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ቀደም ሲል በምክር ቤቱ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ላይ ተመስርቶም፥ ከአባላቱ ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ የህዝብን ጥቅም ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደርጋል ነው ያሉት አቶ ጌታቸው።

የመልካም አስተዳደርና የልማት ተደራሽነት ችግሮችን ለመፍታት በተያዘው ዓመት የሚሰሩ ስራዎችም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝርዝር ማብራሪያ ይሰጥባቸዋል። የካቢኔ አባላት ምርጫ አቅምን፣ ቁርጠኝነትንና ውጤታማነትን መሰረት ያደረገ እንደሚሆን የጠቀሱት አቶ ጌታቸው፥ የካቢኔ አባላቱ የሃገሪቷን ህግና ህገ መንግስቱን መሰረት አድርገው ሃላፊነታቸውን በአግባቡ የሚወጡና በትጋት የሚሰሩ መሆናቸውን አንስተዋል።

በገዥው ፓርቲ ትልቅ ሃላፊነት ላይ ያልነበሩ ግለሰቦችም አዲስ በሚዋቀረው ካቢኔ ውስጥ ሊካተቱ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተዋል። እንደ አቶ ጌታቸው ገለጻ፥ የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ላይ ሙሉ ትኩረት ሰጥተው የሚንቀሳቀሱ፣ በህገ መንግስታዊ ስርዓቱ፣ በህዝብ ተጠቃሚነትና ይህንን ለማረጋገጥ በተቀረፁ ፖሊሲዎች አፈፃፀም ላይ ሙሉ እምነት ያላቸው አባላትን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያካትታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አዲስ በሚዋቀረው ካቢኔ ከነበሩበት ሃላፊነት ተነስተው ያላቸውን አቅምና ቁርጠኝነት መሰረት አድርጎ የተሻለ ሊፈፅሙ ወደ ሚችሉበት የሃላፊነት ቦታ ሊዛወሩ የሚችሉ ይኖራሉም ብለዋል። በክልሎች ደረጃ በኦሮሚያ የተደረገው አይነት ለውጥ በሌሎች ክልሎችም ተግባራዊ እንደሚሆን አረጋግጠዋል። መንግስት የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስና የሃገሪቷን ፈጣን እድገት ለማስቀጠል እንዲሁም ሰላምና ደህንነትን ለማስጠበቅ በሚያደርገው ጥረት የህዝቡ ተሳትፎ ቀጣይነት እንዲኖረውም አቶ ጌታቸው አሳስበዋል።

ምንጭ፥ ኢዜአ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *