” ሞት በእኔ አልተጀመረም”ምሩጽ ይፍጠር

miruts-from-great-distance-runners

ምሩጽ ይፍጠር በህይወት መኖሩን ለቪኦኤ ተናገረ። አጭር መልእት ያስተላለፈው ምሩጽ በህዝብ ጸሎትና ርዳታ አለሁ ሲለ የሚወራው ሁሉ ወሸት መሆኑንን አመልክቷል።ዛጎል ፋናን ጠቅሶ ስለዘገበው ይቅርታ ይጠይቃል። ምሩጽ ህክምና ላይ ሆኖ በስልክ ለወዳጆቹ፣ ለአገሩ ህዝብ፣ ለቤተሰቦቹና ሞተ መባሉን ለሰሙ ሁሉ በህይወት መኖሩን አብስሯል።

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አትሌት ምሩፅ ይፍጠር ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

አትሌት ምሩፅ ይፍጠር ታሪክ ከሰሩ ብርቅዬ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አንዱ ሲሆን በ1972 ዓ.ም ሞስኮ ላይ በተካሄደው ኦሎምፒክ በ10,000 እና 5000 ሜትር ተወዳድሮ ሁለት የወርቅ ሜዳልያ ማስመዝገጉ ይታወሳል። አትሌቱ በአጨራረስ ብቃቱ የተነሳ “ማርሽ ቀያሪው” የሚል ቅፅል ስምም ተሰጥቶታል። ምሩፅ በ1964 ዓ.ም በተካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ በ10,000 ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ አግኝቷል።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

አትሌቱ በ1965ቱ የመላ አፍሪካ ጨዋታ በ10,000 የወርቅ ፤ በ5000 ሜትር ደግሞ የነሃስ ሜዳልያ ለሀገሩ ማስገኘቱም የሚታወስ ነው። በ1969 ዓ.ም በተካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታም በ5000 እና በ10,000 ሜትር ሁለት ወርቅ ማስመዝገቡ አይዘነጋም። አትሌት ምሩፅ በአትሌቲክስ በአጠቃላይ ከ410 በላይ ውድድሮች የተሳተፈ ሲሆን፥ በ210 ውድድሮች በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያዎችን አግኝቷል። ይህን ሁሉ አስደናቂ ድል ያስመዘገበው አትሌት ምሩፅ ይፍጠር ጤናው በመታወኩ በውጭ ሀገር ህክምናውን ሲከታተል ቆይቷል።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

አትሌቱ በ72 ዓመቱ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *