በዓመት 300 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ገቢ እንደሚያስገኝና፣ ለ3,000 ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል ተበሎ የታመነበት ፕሮጅርክት መንግስት እንዲረከበው መጠየቁ ይፋ ሆኗል። አይሲኤል የተሰኘው የእስራኤል ኩባንያ በኢትዮጵያ የጀመረውን ኢንቨስትመንት በማቋረጡ ምክንያት፣ በአፋር ክልል የሚገኘውን የፖታሽ ማዕድን ልማት ፕሮጀክት ለደረሰበት ጉዳት ምላሽ ካላገኝ ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ሊወስድ እንደሚችል ተሰማ።allana_potash_1

Dallol potash project

ዜናውን በመከታተል የሚዘግበው ሪፖርተር ጋዜጣ ለድርጅቱቅርብ ናቸው ያላቸውን ምንጮች ጠቀሶ መስከረም 29 ቀን 2009 ዓ.ም ” አይሲኤል የገዛው መሬቱን ሳይሆን በቶሮንቶ ስቶክ ገበያ ላይ የተመዘገበውን የአላና አክሲዮኖችን ስለሆነ፣ የካፒታል ዕድገት ግብር ሊጠየቅ አይገባም” በማለት ዘግቦ ነበር። አያይዞም አይሲኤል በኢትዮጵያ የሚገኘውን ፕሮጀክቱን እንደሚዘጋ በአዲስ አበባ ጽሕፈት ቤቱ ላሉ ሠራተኞቹ ይፋ ማድረጉን አመልክቶ ነበር።
በገቢዎችና ጉምሩክ 55 ሚሊዮን ዶላር ታክስ የተጠየቀው ኩባንያ በተደጋጋሚ ላቀረበው የደብዳቤ ጥያቄ በቂ መላሽ ባለማግኘቱ በአንድ ቢሊኦን ዶላር ሊገነባው ያቀዳቸውን ሶስት የማዳበሪያ ፋብሪካዎች እውን ሳያደርግ ፕሮጀክቱን መንግስት እንዲረከበው ጠይቋል። ውዝግቡ በድርድር የማይፈታ ከሆነ ጉዳዩን ወደ ዓለም ዓቀፍ ፍርድ ቤት እንደሚወስደው ተሰምቷል። ከታቸ ሙሉ የሪፖርተር ዘገባ ያንብቡ።
የእስራኤሉ ኩባንያ መንግሥት የፖታሽ ፕሮጀክቱን እንዲረከበው ጠየቀ
– ለጠፉ ንብረቶች መንግሥትን ተጠያቂ አደረገ
አይሲኤል የተሰኘው የእስራኤል ኩባንያ በኢትዮጵያ የጀመረውን ኢንቨስትመንት በማቋረጡ ምክንያት፣ በአፋር ክልል የሚገኘውን የፖታሽ ማዕድን ልማት ፕሮጀክት መንግሥት እንዲረከበው ጠየቀ፡፡
አይሲኤል ከታክስ ክፍያ ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ጋር እሰጥ እገባ ውስጥ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ኩባንያው አላና ፖታሽ የተሰኘውን የካናዳ ኩባንያን የገዛበት የካፒታል ዕድገት ግብር፣ የአላና ፖታሽ መክፈል የነበረበት ዊዝሆልዲንግና ቫት በአጠቃላይ 55 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ያላግባብ ተጠይቄያለሁ በማለት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በአፋር ክልል ዳሎል አካባቢ የጀመረውን የአንድ ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ማቋረጡን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ኩባንያው ኢንቨስትመንቱን ማቋረጡን ካስታወቀ በኋላ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የኩባንያውን የባንክ ሒሳቦችና ንብረቶቹን አግዷል፡፡ ይሁን እንጂ የኩባንያው የባንክ ሒሳቦች መታገዳቸው በሥራ ሒደቱ ላይና በንብረቶቹ ላይ የፈጠረውን አደጋ በማስረዳት የባንክ ሒሳቡ ዕግድ ተነስቶለታል፡፡
አይሲኤል ኅዳር 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ለማዕድን፣ ፔትሮሊየምና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ የፖታሽ ፕሮጀክቱን ሚኒስቴሩ እንዲረከበው አመልክቷል፡፡ ኩባንያው ለሚኒስቴሩ በጻፈው ደብዳቤ ዝርዝር የማስረከቢያ ሒደቱን የሚገልጽ ዕቅድ ያሰፈረ ሲሆን፣ ሚኒስቴሩ ፕሮጀክቱን ከተረከበ በኋላ የፕሮጀክት መዝጊያ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡
አይሲኤል የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የባንክ ሒሳቡን ባገደበት ወቅት ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበት ገልጿል፡፡ የባንክ ሒሳቡ በተዘጋበት ወቅት ሠራተኞቹን መስክ ለማስወጣትና የሥራ እንቅስቃሴውን ሙሉ በሙሉ ለማቋረጥ ተገዶ እንደነበር ጠቅሶ፣ ይህም በኩባንያው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳስከተለበት አትቷል፡፡
በመስክ የሚገኙ ማሽኖች፣ መሣሪያዎችና ሌሎች የተለያዩ የኩባንያው ንብረቶች ለዝርፊያና ለስርቆት መዳረጋቸውን የገለጸው ኩባንያው የደረሰበትን የንብረት ውድመት መጠን በማጣራት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የባንክ ሒሳቦቹ በታገዱበት ወቅት ለሠራተኞችና ለኮንትራክተሮች ክፍያ መፈጸም ተስኖት እንደነበር ጠቁሞ፣ በዚህም ምክንያት የካሳ ጥያቄ ሊመጣበት እንደሚችልና ለዚህና ለጠፉ ንብረቶቹ ሙሉ በሙሉ መንግሥትን ተጠያቂ አድርጓል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ አይሲኤል በኢትዮጵያ ቢሮ የሚሠሩ 145 ቋሚ ሠራተኞቹን ኅዳር 1 ቀን 2009 ዓ.ም. በደብዳቤ ሸኝቷል፡፡ ኩባንያው ሠራተኞቹን ያሰናበተው አስፈላጊውን የአገልግሎትና የሥራ መፈለጊያ ክፍያ ሳይፈጽም መሆኑ፣ በሠራተኞቹ ዘንድ ግራ መጋባትን መፍጠሩን ምንጮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
አይሲኤል በዳሎል የፖታሽ ማዕድን ማውጫ፣ ሦስት የማዳሪያ ፋብሪካዎች ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ለመገንባት አቅዶ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡ ፕሮጀክቱ ለአገሪቱ በዓመት 300 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪና ለ3,000 ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ተገምቶ ነበር፡፡
በአይሲኤል ደብዳቤ መሠረት ኩባንያው ወደ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለመሄድ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ፡፡ መንግሥት ከወዲሁ ችግሮቹን በድርድር መፍታት ወይም የሚመጣውን ክስ ለመመከት ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ እንዳለበት ያሳስባሉ፡፡
ዜና – ቃለየሱስ በቀለ እና በዳዊት ታዬ’s blog 1028 reads Reporter Amharic

Related stories   Ethiopia: Lies, Damn Lies, Axum and the West – by Jeff Pearce

pic, Typical landscape of the Danakil depression, close to where Allana’s potash project is located.

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *