“ ፍጹም አሉባልታ ነው፤ የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል አይደለሁም” ጁነዲን ሳዶ

ኢህአዴግን ከድተው አሜሪካ የገቡት የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጁነዲን ሳዶ በጄነራል ከማል ገልቹ የሚመራውን ኦነግ በምክትል ሊቀመንበርነት ሲያገለግሉ እንደነበር ተሰማ። እሳቸው “ ፍጹም አሉባልታ ነው” ሲሉ ያስተባብላሉ።

ጀነራል ከማል ገልቹ ኦነግን ከተቀራመቱት የስደት “ታጋዮች” መካከል አንዱ ናቸው። ኦነግ በውል የሚታወቀው በአራት ማንነት ሲሆን፣ ለአራቱም ማንነቱ መሪና ተጠሪ አለው። ከአራቱ መካከል ጀነራል ከማል ገልቹ የሚመሩት ኦነግ እንደ ሌሎቹ ሁሉ ኤርትራ ይገኝ ነበር። ዛሬ ግን ጀነራል ከማል የሚመሩት ኦነግ ሰራዊቱ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ በግልጽ ባይነገርም እሳቸው ከኤርትራ ነቅለው መውጣታቸው ታውቋል። ጀነራሉ ለምን ወደ ካምፓላ እንደገቡ በግልጽ ባይናገሩም አስመራን ለቀው መውጣታቸውን አላስተባበሉም። ቀደም ሲል አስመራ በቁም እስር ላይ መሆናቸው ሲዘገብ ለማስተባበል ጊዜ አልወሰዱም ነብር።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

አቶ ጁነዲን አገር ከለቀቁ በሁዋላ የከማል ገልቹን ኦነግ መቼና የት እያሉ እንደተቀላቀሉ መረጃ የሰጡት ክፍሎች አላረጋገጡም። ይሁንና አቶ ጁነዲን እንደ አንድ በሳል ፖለቲከኛ የተበታተኑትን የኦሮሞ ድርጀቶች የማሰባሰብና የማቀናጀት ሃሳብ ነበራቸው። ለዚህም ተግባራዊነት ሲሉ በቅርብ የሚያውቋቸውን ከማል ገልቹን እንደቀረቡና ለውስን ጊዜ ምክትል ሊቀ መንበር በመሆን ሰርተዋል።

በባህሪያቸው ችኩል እንደሆኑ የሚነገርላቸው ከማል ገልቹ አቶ ጁነዲን ባሰቡትና በፈለጉት መንገድ የሚሄዱ ሆነው ባለመገኘታቸው ተለያይተዋል። እንደ ዜናው ሰዎች ገለጻ አቶ ጁነዲን ከማል ገልቹ ከሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶች ጋር ተባብረውና ተዋህደው እንዲሰሩ ለማስቻል በዙ ጥረዋል።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ዜናውን “ ፍጹም አሉባልታ” ሲሉ ያስተባበሉት አቶ ጁነዲን ካገር ከወጡ በሁዋላ የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል እንዳልሆኑ አስረገጠው ነው የተናገሩት። ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ለጊዜው እንደማይችሉ በማስታወቅ ዜናውን በጽሁፍ መልዕክት  ያስተባበሉት አቶ ጁነዲን አትላንታ በተደረገው በውጪ አገር የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች የሽግግር ሰነድ ቀርጻ ስብሰባ ላይ ተገኝተው  ነበር። አቶ ጁነዲን ድምጻቸው ጠፍቶ ከቆዩ በሁዋላ በተለያዩ መገናኛዎች ቃለ ምልልስ የሰጡ መሆናቸው ይታወሳል።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው የኦነግ ቡድን “የመገንጠል አጀንዳን ትተናል” በማለት ጥር 3 ቀን 2012 በቪኦኤ ካስታወቀ በሁዋላ የበርካቶችን ቀልብ ለመሳብ ችሎ እንደነበር ብዙዎች ይመሰክራሉ። ሆኖም ግን አሁን ካምፓላ አዲስ ከመሰረቱት ቤተሰባቸው ጋር ኑሮ መጀመራቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

በአቶ ዳኡድ ኢብሣ የምመራዉ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ”አናሳ ተገንጣይ”  ሲል የሚጠራው የከማል ገልቹ ቡድን አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ መርጃ የለም። ዳውድ ኢብሳም ቢሆኑ  ለኦሮሞ ትግል የአንበሳውን ድርሻ እንደሚይዙ ከመናገር በዘለለ በተጨባጭ የድርጅታቸውን ህልውናና አቅም የሚያሳይ ተግባር ባለማስመዝገባቸው ተቃውሞ እየተሰነዘረባቸው ይገኛል።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *