አውሮፕላኖቹ ከተለያዩ ዓለማት የተውጣጡ ቡድኖቸ በ35 ቀናት ወስጥ 37 ጊዜ በማረፍ አስር አደሮችን ለማቋረጥ የሚያደርጉት እንደሆነ ቪኦኤ አመልክቷል። አሜሪካ ዜጎቿን አስመልክቶ ከባለስልጣናት ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ኤምባሲው አመልክቷል። ፋና እንዲህ ይላል

ከሁለት ቀን በፊት 20 ቀላል የሲቪል አውሮፕላኖች ከሱዳን ተነስተው የኢትዮጵያን ድንበር ያለፍቃድ አቋርጠው መግባታቻውን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታውቋል።

Related stories   ህወሃትና ኦነግ ሸኔ በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ቀረበ

አውሮፕላኖቹ በአሁኑ ጊዜም በጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲያርፉ መደረጋቸውን ነው ባለስልጣኑ የተገለፀው።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ በአሁኑ ወቅት እነዚህ ተልዕኳቸው ያልታወቀና ቀድመው ወደ ኢትዮጵያ የአየር ክልል ለመገባት ፍቃድ ያልጠየቁት ቀላል አውሮፕላኖች ማንነትና የኢቲዮጵያን አየር ክልል የመጣሳቸው ምክንያት እየተጣራ ነው ብለዋል።

እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ከባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ምርመራ እየተካሄደ ይገኛል ሲሉም ተናግረዋል።

Related stories   "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም አጠቃላይ የምርመራ ውጤቱ ከተጠናቀቀ በኋላ መንግሰት ጉዳዩን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ መግለፃቸውን ባለስልጣኑ ያደረሰን መግለጫ ያመለክታል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *