“Our true nationality is mankind.”H.G.

መራራ – ጣፋጩና ታማኙ ኢትዮጵያዊ ፖለቲከኛ!! ቤቱን ሸጦ ችግርተኛ ተማሪዎችን የረዳና ኪራይ ቤት የወደቀ ለጋስ!! መጨራሻው ማዕከላዊ!!

ጥላቻን የሚጠየፉ፣ ታማኝ ፣ ቀጥተኛ፣ የሚመስላቸውን የሚናገሩ፣ የማይፈሩ፣ ከጀርባ መናገር የማይወዱ፣ በርካታ የዴሞክራሲ ተሟጋቾችን ያፈሩ፣ ለጋስ፣ ስብዕናቸውን የጠበቁ፣ በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚከበሩ፣ ላለፉት 25 ዓመታት የታገሉ፣ ሰላማዊ ትግልን የሚደገፉ፣ የኦሮሞ ጥያቄ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚፈጠር ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ ይመለሳል ብልው የሚያምኑ፣ ማክረርን የማይወዱ፣ በመንገዳቸው የቆሙ፣ የማይልከሰከሱ፣…. ለመረራ ጉዲና በተለያዩ ጊዚያት የተሰጡ ምስክርነቶች ናቸው።
የኦሮሞ ፌደራሊስት ምክትል ሊቀመንበር አቶ መላኩ ገመቹ ለቪኦኤ ያረጋገጡት ይህንኑ ነው። እሳቸው እንደሚሉት እንዲህ ያሉትን ፖለቲከኛ ማሰር ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። የሂይውማን ራይትስ ዎችዋ ሚሸል ካጋሪ ደግሞ ድርጊቱን ” በመናገር ነጻነት ላይ የተወሰደ ቅጥ ያጣ ርምጃ” ሲሉ ድርጊቱን ኮንነዋል። ሲቀጥሉም ” ለወራት የበርካታ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈውን ተቃውሞ መልሶ የመቆስቆስ ያህል ነው” ሲሉ የተናግገሩትን ስጋት ያዘለ ቃላቸውን ቪኦኤ አሰምቷል።merera-1
ቀደም ሲል ዜናውን ” ታማኞቻችን ነገሩን” ሲሉ እዳሰራጩት ሳይሆን፣ መረራን “የጸጥታ ሃይል” የተባሉት ክፍሎች የወሰዱዋቸው ከመኖሪያ ቤታቸው ከለሊቱ ስምንት ሰዓት አካባቢ ነው። ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ ቤታቸው ሲበረበር ነበር። ሶስት ላብቶፖች፣ የሞባይል ስልካቸው፣ ሰነዶች፣ ለጊዜው መጠኑ ያልተገለጸ ገንዘብ፣ እንደተወሰደባቸው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ጥሩንህ ገንታ አረጋግጠዋል። የአሜሪካ ሬዲዮ አዲስ አበባ ዘጋቢ እንዳለው መረራ ከአውሮፓ እንደተመለሱ ቤታቸው ሲገቡ ጤንነት ይሰማቸው ስላልነበር ወደ ሃኪም ቤት የመሄድ እቅድ ነበራቸው።
መረራ ወደ ማዕከላዊ ሲወሰዱ አብረዋቸው ይኖሩ የነበሩ ታዬ ነገራና ኩመራ ደበላ የሚባሉ ሁለት ወጣቶች አብረዋቸው የታሰሩ ሲሆን የነሱ እስርና የታሰሩበት ምክንያት ይፋ አልሆነም። በማግስቱ ምግብ እንደተቀበሉዋቸው፣ ይሁንና በአካል እንዳልተያዩ አቶ ጥሩንሀ በቦታው መገኘታቸውን ጠቅሰው ተናገረዋል።
በብራስልሱ የአውሮፓ ፓርላማ የምስክር ሸንጎ የሚያውቁትን እንዲመሰከሩ በደረሳቸው ጥሪ መነሾ ወደ ስፍራው አምርተው በሌሉበት ሞት ከተፈረደባቸው አርበኛ ብርሃኑ ነጋና የሪዮ ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ ባለቤት ፈይሳ ሌሊሳ ጋር አበረው የተቀመጡት ድ/ር መረራ፣ መታሰር ” ቢያስደነግጠኝም አልገረመኝም” ሲሉ የገለጹት ወ/ሮ አና ጎሜዝ ናቸው።
ወ/ሮዋ ስብሰባውን እዲጋበዙ ጥሪ ያስተላለፉ ራሳቸው መሆኑንን ጠቅሰው ለሚመለክታቸው ሃላፊዎች ድብዳቤ መጻፋቸውን አመልክተዋል። የማያወላዳ፣ የማያወላውል፣ ጠንካራ ተጽዕኖ እንዲደረግ ማሳሰባቸውን ያመለከቱት ወ/ሮ አና ጎሜዝ ጉዳዩን አክብዶ ለመያዝ በዙ መንገዶች እንዳሉ አመላክተዋል። በሌላም በኩል የአውሮፓ ህብረት በኢህአዴግ ላይ የተለሳለሰ አቋም እንደሚያራምድ ተናገረው ይህ ግን ሊቀጥል እንደማይችል አሳስበዋል። በቃላቸውም ለቪኦኤ ተናገረዋል።
የኦፌኮ ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ጥሩነህ ” መረራ” አሉ ” መረራ አስተማሪያችን፣ መሪያችን፣አስተባባሪያችን ነው መታሰሩ ይጎዳናል፣ ትግሉን ግን ያጠናክረዋል “፤ ልክ እንደ አቶ ጥሩነህ ሁሉ በርካታ አስተየየት ሰጪዎች የመራራ መታሰር ” ኢህአዴግ አምባገነንነቱን ለዓለም በይፋ እወቁልኝ የማለት ያህል ነው” ሲሉ ነወ የሚደመጠው። በኦሮሚያ አሁን ጋብ ያለ የሚመስለውን አምጽ መልሶ የመቆስቆስ ተግባር እንደተፈጸመ የሰበአዊ መብት ተሟጋቹ ሂይውማን ራይትስ ዎች ይፋ አድርጓል።
የ60 ዓመቱ መረራ በተለይም በዕራብ ሸዋ አመያ፣ ጉደር፣ አምቦ፣ ጊንጪ፣ ግንደበረት፣ ባቢች፣ ጥቁር ኢንጪኒ፣ ባቢች፣ጌዶ፣ ባኮ፣ ፍንጭ ውሃ.. እና በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች ያላቸው ተቀባይነት የአምልኮ ያህል በመሆኑ የግብረሰናይ ድርጅቶቹ ስጋት እንዲሁ በቀላሉ የሚታይ እንዳልሆነ ነው የሚገመተው። ፋና ብሮድ ካስቲንግ የመከላከያ ሚኒስትሩን አቶ ሲራጅ ፈርጌሳን ጠቅሶ የአስቸኳይ አዋጁን መተላለፍና አሸባሪ ተብለው ከተፈረጁት አርበኛ ብርሃኑ ነጋ ጋር በመገኘታቸው እንደታሰሩ መግለጹን መዘገባቸን ይታወሳል። ዶ/ር መረራን አስመልክቶ መድረክ እስካሁን ያለው ነገር የለም።
ጣፋጩ ፖለቲከኛ መረራ ማእከላዊ መግባታቸውን ተከትሎ ለዛጎል አስተያየት ከሰጡ መካከል ” የግል ቤቱን ሽጦ በዩኒቨርስቲ ውስጥ ችግር ላጋጠማቸው ወገኖቹ የደረሰና ህይወቱን በኪራይ ቤት የሚገፋ የታላቅ ስበእና ባለቤት ነውና በልባችን ውስጥ ታትሟል” የሚል ይገኝበታል። መረራ በደርግ አገዛዝ ለስምንት ዓመታት እስር ላይ የቆዩ መሆናቸው አይዘነጋም።

Related stories   ቻይና በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት የሚካሄደውን የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር እንደምትደግፍ ገለጸች

መረራ ፋና ባዘጋጀው ውይይት ላይ የሁሉም ዜጎች ክብራቸውና መብታቸው የተጠበቀባት ኢትዮጵያን መስርተን፣  ከኢህአዴግ ጋር ያለንን ንትርክ አቁመን አገሪቱን ወደ ዘላቂ ልማት ማሸጋገሩ ላይ ቢተኮር የተሻለ እንደሚሆንና ኢህአዴግም ይህንን በማድረግ ታሪክ ቢሰራ ሲሉ ለመጨረሻ ጊዜ ንግግር አድርገው ነበር። መሰረታዊ ለውጥ የህዝብ ጥያቄ እንደሆነም ደጋገመው ተናገረው ነበር። ለዚህም ተገባራዊነት ኢህአዴግ የያዛቸውን ሁለት ምርኩዞች፤ ማለትም ጠብመንጃና ምርጫ ቦርድን ወደ ጎን በማድረግ ህዝብ ያሻውን እንዲመርጥ መንገዱን እንዲያመቻቸ አሳስበውም ነበር።

Related stories   የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ለአሶሼትድ ኘሬስ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

ፎቶ ማዕከላዊ – ሂውማን ራይትስ ዎች

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0