“Our true nationality is mankind.”H.G.

ዶ/ር መረራ የት መቀመጥ ነበረባቸው?ኢህአዴግ በመረራ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መመሪያ አንቀጽ 2 ተጠቀሰባቸው

ዶ/ር መረራ ለጋበዛቸው አካል ምስክርነታቸውን ከመስጠታቸው ሌላ በግል ክፕሮፌሰር ነጋ ጋር ስለመወያየታቸው መረጃ የለም”

ዶክተር መረራ ጉዲና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መመሪያ ተላልፈው በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያረጋገጠው ፋና የተላለፉትም አንቀጽ 2 ላይ የተመለከተው እንደሆነ አመልክቷል። “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት” የጠቀሰው ዜና ዶክተር መረራ ተላለፉ የተባለው መመሪያ በሽብር ከተሰየሙ ድርጅቶችና ከፀረ ሰላም ቡድኖች ጋር ማንኛውንም ግንኙነት ማድረግ የሚከለክለውን ነው። በዚህም የተነሳ ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው።

“ዶክተር መረራ በቤልጅየም ብራሰልስ በአሸባሪነት ከተፈረጀው ግንቦት ሰባት ቡድን መሪ ብርሃኑ ነጋ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውና መግለጫ መስጠታቸው የሚታወስ ነው” ያለው የፋና ዘገባ የትና በምን ጉዳይ እንደተወያዩ አልጠቀሰም። በወቅቱ የተላለፉ ዜናዎች እንዳሉት ዶክተር መረራ ከአርበኞች ግንቦት 7 መሪ ጋር በብራስልስ የትገናኙት እሳቸው ፈገው ስለመሆኑ አያረጋገጡም።

Related stories   የተላላኪው ጠበቃዎች

ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ድጎማ የሚለግሰው የአውሮፓ ህብረት ባደረገላቸው ጥሪ መሰረት ምስክርነታቸውን ለመስጠት ብራስልስ እንደተገኙ ነው የሚታወቀው። መረራ አክራሪነትንና ተራ የጎሰኝነትን አስተሳሰብ የሚጥሉ ሰላማዊ ፖለቲከኛ ስለመሆናቸው የሚያውቁ በሰሙት ዜና ማዘናቸውን እየገለጽ ነው።

” ጉዳዩ የአውሮፓ ህብረት ነው” የሚሉ ተከራካሪዎች እነሱ ስብሰባ ጠርተው፣ ስብሰባ የተጠሩ ሰዎች ሲታሰሩ ዝም ብለው የሚመለከቱ ከሆነ ጉዳዩ የሌላ እንደሚመስል ዛጎል ያናገራቸው ገልጸዋል። ፓርቲያቸው ሆነ መደረክ በዶ/ር መረራ መታሰር ጉዳይ እስካሁን ያሉት ነገር የለም። የአውሮፓ ህብረትም መግለጫና አቋም የሚጠበቅ ሆኗል።

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ

ከአስቸኳይ ጊዚ አዋጁ ጋር በተያያዘ የጀርመን ድምጽ ለውይይት የጋበዛቸው ዲያቆን ዘላለም ክብረትና መቶ አለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ በውይይት ለመሳተፍ ፈቃደኞች ከሆኑ በሁዋላ ሳይካፈሉ ቀርተዋል። በዚሁ በአስቸኳይ አዋጁ የተነሳ የፖለቲካ ስራ ለመስራት መሸማቀቃቸውን የጠቆሙ የፖለቲካ ድርጅቶች ፓርቲያቸው ፈቃዱን ለመመልስ የሚገደድበት ደረጃ ላይ መድረሱን ከዚህ ዜና አንድ ቀን ቀደም በለው በይፋ ማስታወቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

አቶ በቀለ ገርባን ያጣው የኦሮሞ ትግል አሁን ደግሞ ዋናውን ሰው ሊያጣ ነው። ይህንን አስመለክቶ አምቦ ዩኒቨርስቲ እንደሚማር የገለጸ ተማሪ ” ይህ መደናበር ነው። ተወደደም ተጠላም በቅርቡ ለውጥ ይኖራል። ህዝብም ኢህአዴግም ተጨንቀው በዚህ መልኩ አይቀጥሉም” ሲል ለዛጎል ተናግሯል። ዶ/ር መረራ መቼ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ አልታወቀም። ዶ/ር መረራ በውጪ አገር የተለያዩ ሚዲያዎች ሲጠየቁ ዘወትር ስለ ሰላማዊ ትግል የሚናገሩ መሂናቸው ይታወቃል። በቀርቡ ምናላቸው ስማቸው አንኳር በሚባል የኢትዮ ቲዩብ ገጽ ” … እርስዎ ለምን አይታሰሩም?” ሲል ጠይቋቸው፣ ” እሱን ኢህአዴግን ጠይቅ” በማለት መመለሳቸው ይታወሳል።

Related stories   “የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው››

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የጉደር አካባቢ ነዋሪ “የመድረክና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ከፕሮፌሰር ብረሃኑ ጋር በግል ቀጠሮ ይዘው ወደ ብርራስልስ አለመሄዳቸው የሚታወቀ ነው። ባካባቢው ባለኝ መረጃ ጉዳዩ ብዙ ችግር ያስከትላል”

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0