በአብዛኞች ዘንድ መልካም ስብዕና እንዳላቸው የሚነገርላቸው ዶ/ር መረራ ጉዲናን ለመፍታት እቅድ እንዳለ መስማታቸውን አንድ የህግ ባለሙያ ለዛጎል ጠቆሙ። ዛጎል ከዶ/ር መረራ እስር ጋር በተያያዘ ማብራሪያ ለመጠየቅ በስልክ ያገኛቸው ታዋቂ የህግ ባለሙያ ” ለጊዜው ምንም አስተያየት መስጠት አልፈልግም፤ ግን መረራን የመፍታት እቅድ ስለመኖሩ አውቃለሁ” ሲሉ ተናገረዋል።

ዝርዝር ውስጥ ለመግባት የማይፈልጉት ክፍርሃቻ ሳይሆን ” አላስፈላጊ አስተያየት መሰንዘር ዶ/ር መረራንም ሆነ ሌሎች እስረኞችን አይጠቅምም። አጉል እልህ ማጋባት ነው” ሲሉ ምክንያታቸውን ተናግረዋል። የመፈታታቸው ፍንጭ መኖሩ የሰሙት ጉዳዩን ከያዙት የውጪ ዲፕሎማቶች ዘንድ እንደሆነም ጠቁመዋል። ዶ/ር መረራ ከአውሮፓ በተመለሱበት እለት ሌሊት መያዛቸው የሚታወስ ሲሆን፣ የሳቸውን መታሰር ተከትሎ ለምስክርነት የጠራቸው  የአውሮፓ ፓርላማ፣ አሜሪካን፣ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ ድርጊቱን መቃወማቸውና በአስቸኳይ እንዲፈቱ መጠየቃቸው የሚታወቅ ነው።

Related stories   “ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

በዲሰምበር 7 ቀን 2016 ስርጭቱ ቪኦኤ ዶ/ር መረራ ሲያዙ አብረዋቸው የታሰሩት ታየ ነገራና ኮመራ ደለሳ መፈታታቸውን ዘግቧል። እስረኞቹ የታሰሩበትን ምክንያት እንዳላወቁ በዘገባው ተመልከቷል። የዶ/ር መረራን እስር አስመልክቶ ኮማንድ ፓስቱ ህግ መተላለፋቸውን ከመግለጹ ውጪ ሌላ የተባለ ነገር የለም።

ዛጎል ዜና ዲሰምበር 12 – 2016

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *