በየዓመቱ አፕሪል 18 በባቡር ሽቡያ የባቡር መንገድ የትውስታ ስነ ስርዓት የከናወንለታል። በዕለቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ውሻ አፍቃሪዎች ተሰባስበው ያስቡታል። ይህ እድለኛ ውሻ ሃቺኮ ይባላል። በጃፓናዊያን ልብ ውስጥ ትልቅ ስፍራ ያለውና ፍጹም ታማኝ የሚባል ነው።
አሳዳሪው ፕሮፌሰር Ueno ጠዋት ወደ ስራ ሲወጡ ባቡር ጣቢው ዘንድ አድርሷቸው ይመለሳል። ከስራ በሚመለሱብት ሰዓትም ሄዶ ይቀበላቸውና ወደ ቤት አብረው ይመለሳሉ። ይህ የዘወትር ተግባራቸው ነበር እስከ 1925 ሜይ ድረስ።

Related stories   እኛ የምንመርጠው አባትና አያቶቻችን የመረጡትን ነው።

200px-hachikoበመጨረሻው ቀን ፕሮፌሰሩ ጠዋት እንደ ልማዳቸው በውሻቸው ታጅበው ባቡር ጣቢያ ይደርሳሉ። ሃቺኮ ወደ ቤቱ ተመልሶ ሊያመጣቸው እንደ ለማዱ ባቡር ጣቢያ ሲሄድ አሳዳሪው ይቀራሉ። ይጠብቃል፣ ይጠብቃል… ሰዓታት፣ ቀናት፣ ሳምንታት፣ ወራት፣ ዓመታት ጠበቀ። አሳዳሪው ግን ላይመለሱ ነበር የወጡት። ለወትሮው በአንጎል እጢ ይቸገሩ የነበሩት ፕሮፌሰር አልፈው ነበር።
ሃቺኮ እዛው ባቡር ጣቢያ ጌታውን ሲጠብቅ ዘጠኝ ዓመት ከዘጠኝ ወር ከአስራአምስት ቀን ጌታ220px-Hachiko's_grave_in_the_Aoyama_cemetery,_Minatoku,_Tokyo,_Japan.jpgውን ጠበቀ። ቀደም ሲል ከፕሮፌሰር ጋር የእለት ተግባሩን ሲያከናውን የሚያውቁት የባቡር ጣቢያው ሰራተኞችና ሌሎች ምግብ በማቅረብ ሃቺኮን ይንከበከቡት ጀመር። በማርች 8 ቀን 1935 በተወለደ በ11 ዓመቱ አሳዳሪውን በሚጠብቀበት ባቡር ጣቢያ አረፈ።

Related stories   የመረጃ መንታፊዎች ዋትሳፕን እንደ ጥቃት ማድረሻ መሳሪያ እየተጠቀሙ መሆኑ ተገለጸ

የጃፓናውያንን ቀልብና ልብ ያገኘው ሃቺኮ ካሳዳሪው ጎን ተቀብሮ ሃውልት ቆመለት። በየዓመቱም ይዘከር ጀመር። ኢግዚቢሽን ይዘጋጅለት ጀመር። ፊልምም ተሰራለት። በዙ በዙ ነገሮች ከሱ ጋር እየተዛመዱ ተከየኑ። አፕሪል ዘፉል ሃውልቱ ተሰረቀ በሚል ማስደንገጫ ሆነ። እኛ ታሪክ እናወድማለን፤ ፈጣሪ ልብ ይስጠን

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *