ዜናውን ለሰሙ የሃይሌ የቴሌቪዥን ጣቢያ መክፈት ሳይሆን ስራውን ለመስራት የመረጣቸው አጋሮቹ ስብጥር ነው። አቶ አማር አረጋዊ ያለ ምንም ጥርጥር በቁ ናቸው። ኢቲቭን ሲመሩት ነብስ ዘርተውበት እንደነበርና ዛሬ ድረስ 120 በሚል  ስያሜ የሚታወቀውን የመዝናኛ ፕሮግራም እንደተከሉ ምስክር አላቸው። ይህ በቸኛ መዝናኛ ክፍለ ጊዜ ብዙዎችን እሁድ በቤታቸው ያሳረፈ ነው። የወርልድ ስፔስ ራዲዮ መስራች ኖህ ሳማራ ቅንና ለስራም ሆነ ለሃይሌ እቅድ ውድ ሰው ናቸው። ገብረ እግዚአብሄር ገብረማርያም አስተዋይና ብሩህ የንግድ እሳቤ ያለው አትሌት እንደሆነ የዚህ ገጽ አዘጋጅ ምስክሩ ነው።

Related stories   የአሜሪካ ሴናተሮች የኢትዮጵያ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረቡት ጥሪ ብልህነት የጎደለው እጅግ አደገኛ ነው - ሎረንስ ፍሪማን

ዚናውን ያተመው ኢትዮ ስፖርት መቼና ምን ስም ይዞ ስርጭቱ እንደሚጀመር ባያሳውቅም ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች ከሃይሌ ጋር ሽርክና መስርተው ለመስራት መስማማታቸውን ይፋ አድርጓል። የዝግጅት ክፍላችን ቀደም ሲል  እንደሚያውቀው አቶ አማረ እና ኖህ ሳማራ ዘርፉ ላይ በሙያው የበቃ የተባለ የሚዲያ ተቋም የማቋቋም ህልም ነበራቸው። የኢትዮ ስፖርትን  ዘገባ ከታች ይመልከቱhailegebresialse

በቅርቡ የኢትዮጵያ አትሌትቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆኖ የተመረጠው አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ከሸሪኮቹ ጋር በመሆን የቴሌቭዥን ጣቢያ ባለቤት ሊሆን መሆኑ ተሰማ::

Related stories   "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ

የኃይሌ ሸሪክ በመሆን የሚሠሩት የሪፖርተር ጋዜጣ መስራችና አዘጋጅ አማረ አረጋዊ፣ አትሌት ገብረእግዚአብሔር ገ/ማርያምና የወርልድ ስፔስ ራድዮ መስራች አቶ ኖህ ሳማራ ቴሌቭዥን ጣቢያ በመዝናኛና መረጃ (ኢንፎቴይመንት) ላይ እንደሚያተኩር ምንጮች አስታውቀዋል:: ለዚህ አዲስ የቴሌቭዥን ጣቢያም በሰሜን አሜሪካ ካሉት ትልልቅ ከተሞች ውስጥ አንዷ በሆነችው ችካጎ ከተማ ውስጥ ስቱዲዮ የተከፈተ ሲሆን በአዲስ አበባ አትሌት ገብረ እግዚአብሄር ገብረማርያም ሕንጻ ላይም ስቱዲዮው ተሰርቶ መጠናቀቁ ታውቋል:: የቴሌቭዥን ስርጭቱ በአማርኛ እና በ እንግሊዘኛ ቋንቋ ይሰራጫልም ተብሏል::

Related stories   "ኢትዮጵያን የውስጥና የውጭ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው ሊያጠፏት የተነሱበት ወቅት ላይ እንገኛለን፤ ሁሉም አንድ መሆን ይገባዋል – የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *