Hazard.jpg
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ገንዘብ ከሚከፈላቸው 20 ተጫዋቾች መካከል ስድስቱ የማንችስተር ተጫዋቾች ናቸው። ሌሎቹ ስድስት ተጫዋቾች ደግሞ ከሲቲ ሲሆኑ ቼልሲ አራት ተጫዋቾች አሉት። ኦዚል 140 ሳንቼዝ 130 ሺህ በሳምንት ያገኛሉ። አሁን ሳንቼዝ እና ኦዚል ያነሱት የመደራደሪያ ክፍያ ጥያቄም ከዚሁ መርጃ በመነሳት ሲታይ አግባብ ይሆናል። የኦዚልን ብንተወው እንኳን ሳንቼዝ ያነሳው ጥያቄ ፖግባ ያለ አንዳች አገልግሎት ከተቆለለበት ደሞዝ ጋር ሲነጻጸር ያስቃል። ለዚህም ይመስላል ዌንገር ተስፋ በቆረጠ ስሜት ” 18 ወር በኳስ ዓለም ብዙ ነው” ሲሉ የመለሱት።
አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ሳንቼዝ ወደ ቻይና ሊያመራ ይችላል። ሲቲዎችም አላስቀምጥ ብለውታል። አርሰናልም የተጠየቀውን ያህል የሚከፍል አልሆነም እናም ሳንቼዝና አርሰናል ይለያያሉ የሚለው ወሬ አየሩን ሞልቶታል። በመካከሉ የሚነሳው አንድ አማራጭ ግን ኦዚልን የመሸጥና ሳንቼዝን የሚደረገውን አድርጎ የማስቀረት ጉዳይ እንዳለ የሚጠቁሙ ዜናዎችም አሉ።
አብዛኞች እንደሚሉት ኦዚል ቢሄድ አርሰናል አይጎዳም። የመሃል ሜዳ ተጫዋች ችግር የለምና። እንደውም ሳንቼዝን ወደ ተደራቢ አጥቂነት በማሸጋሽግ አንድ ጠንካራ አጥቂ ከመጣ አርሰናል ውጤታማ እንደሚሆን የሚናገሩ አሉ። ለዚህም ይመስላል ዌንገር የሚላኑን አጥቂ በ20 ሚሊዮን ለማግዛት የከጀሉት። አሁን ባለው ወቅታዊ አቋም ሳንቼዝ ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን በማዘጋጀት፣ ቡድኑን መለስ እያለ በመምራት፣ በማግባት፣ መከላከልን ከባላጋራ በምጀምር፣ በፍላጎትና በእልህ ውጤታማ የሆነ ተጫዋች በመሆኑ ዌንገር እሱን ቢመርቱ አይገርምም። ለሁሉም ኢትዮ ስፖርት ሰለ ተጫዋቾች ደሞዝ ይህን በሏልsergio-aguero-manchester-city_3358974

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ተከፋይ ተጫዋቾች
POSTED ON DECEMBER 8, 2016
በቻይናው ሊግ አንደብራዚላዊው ሹልክ ያሉ ተጫዋቾች 320,000 ፓውንድ ሳምንታዊ ደመወዝ እየተከፈላቸው በመጫወት ላይ ቢገኙም በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ላይ እየተጫዋቱ የሚገኙ ተዋቾች ግን ከታክስ በፊት በሳምንት 290,000 ፓውንድ እያገኙ መሆናቸው የወቅቱ አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኗል ይለናል የእንግሊዙ ጋዜጣ ደይሊ ሜል።
ሜሌ ዛሬ ይዞት በወጣው ዘገባ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 20 ከፍተኛ ተከፋይ ተጫዋቾች ዝርዝርም ይህን ልዩነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። እንደጋዜጣው ዘገባ ከሆነም በተወዳጁ እና ብዙ ተመልካቾች ያሉት የእንግሊዝ ፕሩሚየር ሊግ ውስጥ በመጫወት ላይ ከሚገኙ ተጫዋቾች መካከል የረብጣ ፓውንዶች የደመወዝ ክፍያ በማግኘት በቁጥር አንድ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ያለው ኮንትራት እስከ2021 ድረስ የሚዘልቀው ፓል ፖግባ ነው። ፈረንሳዊው ተጫዋች በሳምንት 290,000 ፓውንድ ያገኛል።

Arsenal v Watford - Barclays Premier League

 

እንዲሁም እሱን ተከትለው እስከሶስተኛ ባለው ደረጃ የዩናይትድ ተጫዋቾች ይገኛሉ። የማንችስተር ሲቲዎቹ ተጫዋቾች ሰርጂዮ አጉዌሮ 240,000ና ያያ ቱሬ 220,000 ፓውንድ እንዲሁም የቼልሲው ኤዲን ሃዛርድ በተመሳሳዩ 220,000 ፓውንድ በየሳምንቱ ወደኪሳቸው ያስገባሉ።
ይሁን እንጂ ለአርሰናል ትልቅ ግልጋሎት እየሰጠ የሚገኘው እና ከወደሩቅ ምስራቋ ሃገር ቻይና በሳምንት 400,000 ፓውንድ ደመወዝ የዝውውር ጥያቄ እየቀረበለት የሚገኘውን አሌክሲ ሳንቼዝን በዚህ ዝርዝር ውስጥ በ15ኛ ደረጃ ላይ ለማግኘት 185,000 ፓውድን የሚያገኘውን ዴቪድ ደኽያን፣ 180,000 ፓውንድ የሚያገኘውን ራሂም ስተርሊንግን እንዲሁም 170,000 ፓውንድ የሚያገኘውን ሴስክ ፋብሪጋዝን በቅደም ተከተል ቆጥረው ማለፍ ይጠበቅብዎታል።

ደይሊ ሜሌ ይዞት የወጣው ሙሉ 20 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ተከፋይ ተጫዋቾች ዝርዝርም የሚከተለውን ይመስላል።
1: ፓል ፖግባ (ማን ዩናይትድ) 290,000 ፓውንድ በሳምንት
2: ዋይኒ ሩኒ (ማን ዩናይትድ) 260,000 ፓውንድ በሳምንት
3: ዝላታን ኢብራሂሞቪች (ማን ዩናይትድ) 250,000 ፓውንድ በሳምንት
4: ሰርጂዮ አጉዌሮ (ማን ሲቲ) 240,000 ፓውንድ በሳምንት
5: ያያ ቱሬ (ማን ሲቲ) 220,000 ፓውንድ በሳምንት
6: ኤዲን ሃዛርድ (ቼልሲ) 200,000 ፓውንድ በሳምንት
7: ዴቪድ ሲልቫ (ማን ሲቲ) 200,000 ፓውንድ በሳምንት
8: ዴቪድ ደ ኽያ (ማን ዩናይትድ) 185,000 ፓውንድ በሳምንት
9: ራሂም ስተርሊንግ (ማን ሲቲ) 180,000 ፓውንድ በሳምንት
10, ኬቨን ደ ብሩይኔ (ማን ሲቲ) 170,000 ፓውንድ በሳምንት
11, ሴስክ ፋብሪጋዝ (ቼልሲ) 170,000 ፓውንድ በሳምንት
11, መሱት ኦዚል (አርሰናል) 140,000 ፓውንድ በሳምንት
12, ሁዋን ማታ (ማን ዩናይትድ) 140,000 ፓውንድ በሳምንት
13, ባስቲያን ሽዊንስቴገር (ማን ዩናይትድ) 135,000 ፓውንድ በሳምንት
14,አሌክሲ ሳንቼዝ (አርሰናል) 130,000 ፓውንድ በሳምንት
15, ዲሚትሪ ፓየ (ዌስት ሃም) 125,000 ፓውንድ በሳምንት
16, ዊሊያን (ቼልሲ) 120,000 ፓውንድ በሳምንት
17, ቪንሰንት ኮምፓኒ (ማን ሲቲ) 120,000 ፓውንድ በሳምንት
18, ዳኒኤል ስተሪጅ (ሊቨርፑል) 120,000 ፓውንድ በሳምንት
19, ቲብዋ ኮርትዋ (ቼልሲ) 120,000 ፓውንድ በሳምንት

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *