“…ሻዕቢያን አመንክ በላህ፣ ወያኔን አመንክ በላህ፣ ፈረንጅ አምንክ በላህ፤ አሁን ደግሞ  ፕሮፌሰር ብርሃኑን አመንክ ይበላሃል ይሉኛል” አሉ አቶ ሌንጮ፣ አብረው ለመግባባትና ለመስራት ሲስማሙ ልዩነታቸውን በገሃድ አስቀምጠው እንደሆነ አስታውቀው አጠገባቸው የተቀመጡትን አርበኛ ብርሃኑንን እያመላከቱ ” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ግን አይበላኝም ብዬ አስባለሁ” ሲሉ ቤቱ በሳቅ አወካ።

ሌንጮ እጅግ የሚያዝናና ንግግር ነው ያደረጉት። ለቀረቡላቸው ወሳኝ ጥያቄዎች ሲመልሱ በቀልድ እያዋዙ ነው። ” ማርጀት ችግሩ እዚህ ላይ ነው” ሲሉ ከባድ ጥያቄዎች እንደቀረባላቸው ጠቆሙ። አያያዙና ” ካስትሮ ተገላገለ” ሲሉ አከሉ። የኦሮሞም ሆነ የአጠቃላይ የፖለቲካ ድርጅቶች አለመግባባትና አሁን ያለው የኢትዮጵያ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ሲናገሩ ” እጅግ በጣም ያሰጋኛል” በማለት ነው።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

በልጅነታቸው ሁለት ድርጅቶች አሁን ድረስ እሳቸውን ሊገብቸው ባልቻለ ልዩነት ተጋጭተው ለወታደሩ መንግስት በስልጣን መቀመጥ በር እንደከፈቱ ያወሱት ሊንጮ ለታ፣ ሁሉም ካለፈው ስህተትና ችግር አለመማሩ አሳሳቢ ነው ብለዋል።

የበደኖውን እልቂት አስመልክቶ ለተጠየቁት፣ አብዛኛው ወንጀል የተፈጸመው ስልጣን ላይ ባለው ወገን ነው። የመጀመሪያው የመንደር ምርጫ ሲመጣ ሆን ተብሎ ኦሮሞን ከአጎራባቾቹና በውስጡ ካሉት ማህበረሰቦች ጋር ለማጣላት ታስቦ የተከወነ ወንጀል እንደነበር የፋ ሲያደርጉ፣ አስቀደመው “በአርባ ጉጉ የአስተዳደር መዋቅሩ ሙሉ በሙሉ ከኦነግ ውጪ ስለነበር ተጠያቂው ቦታው ሲያስተዳደር የነበረው አካል ነው” አሉና በወቅቱ የኦነግ አንዱ አመራር ስለነበሩ ” በመርህ ደረጃ ኦነግ ማንኛውንም ብሔር እንደ ጠላት ፈርጆ ለጥቃት ግልጽ እንዲሆን አድርገን አናውቅም። የሚያደርጉትንም ሃይሎች እንቃወም ነበር… ግን አሁን ይህንን ማን ያጣራዋል?” ሲሉ አስረግጠው ተናገሩ። ” ግን አሁን ይህን ማንሳት ያቀራርባል? አብሮ ለመስራት ያግዛል? ማንንስ ይጠቅማል? የድሮውን ስናነሳ አሁን የሚሆነውን ለማስረሳት ካልሆነ!”

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

ስለ ሰነደቅ አላማ ያራሳቸውን እምነት በግልጽ ሲናገሩ ” ይህ ከጀርባዬ ያለው ሰንደቅ ዓላማ ታሪክ አለው። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ  የኦሮሞ ልጆች ሞተውለታል” ሌንጮ ቀጠሉ ” ሰንደቅ ዓላማ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ጸድቆ አያውቅም” ሲሉ በየስዓተ ማህበሩ ምልክት እንደሚለጠፍበት አመለከቱ። “እናም አሉ” ሌንጮ ” ወደድንም ጠላንም ” የሚል ማሳሰቢያ አቅርበው የኦሮሚያ ባንዲራ ከዚህ ባንዲራ ጋር እንደሚሆን አትጠራጠሩ።

Related stories   Egypt-Sudan alliance shifting in row with Ethiopia over Nile dam

አርጅተዋልና ስለመሸዋወድ እንደማያወሩ አቶ ሊንጮ አሁንም አስፈግገው ተናገሩ። ” ጫነቃዬ አይችልም ወታደር አላዘምትም” ያሉት ሌንጮ፣ እሳቸው የሚመሩት ኦዲኤፍ ሰራዊት የሚባል ነገር የለውም። ሲውዲን ያደረጉትን ንግግር  ያድምጡ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *