ከአንድ ናይጄሪያዊ ግለሰብ ሆድ ውስጥ ከአንድ ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝኑ 84 እሽግ ኮኬይን የተሰኘ አደንዛዥ እፅ በምኒሊክ ሆስፒታል በቀዶ ህክምና እንዲወጣለት ተደርጓል።

ግለሰቡ አዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ሆዱን በመታመሙ ነው ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል የተወሰደው።

በዚሁ ጊዜም የሆስፒታሉ የህክምና ባለሞያዎች በሆዱ አደንዛዥ እጽ መኖሩን በማረጋጋጣቸው ከ3 ሰአት በላይ በፈጀ ቀዶ ጥገና ህክምና በማድረግ 84 እሽግ እጹን ከሆዱ ማውጣት ችለዋል።

ግለሰቡ በአሁኑ ጊዜ የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ሲሆን፥ የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቡድንም የግለሰቡን ማገገም ተከትሎ የምርመራ ስራ እንደሚጀምር አስታውቋል።

ከፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የተገኘ መረጃ እንዳመለከተው፥ አደንዛዥ እጹ መነሻው ከብራዚል ሆኖ በቦሌ ኤርፖርት ትራንዚትነት ወደ ተለያዩ አገራት እንደሚሰራጭ ነው።

እጹን የሚቀበል ቡድን በአዲስ አበባ መኖሩም በምርመራ መረጋገጡን መረጃው ያመለክታል። ዜናው የፋና ነው

 

 

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *