የአሚሪካ የዴሞክራሲ፣ የሰብአዊ መንቶችና የሰራተኛና ጉዳይ ምክትል ሰከሬታሪ ቶም ማሊንዎስኪ በነገው ቀን አዲስ አበባ ይገባሉ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የመርጃ ዴስክ 12.12.16 ይፋ ባደረገው ማስታወቂያ እንዳመለከተው  ሃላፊው ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙት መንግስትን፣ የሲቪል ማህበረሰብና የተቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶችን ለማነጋገር ነው።

ቀደም ባሉት ጊዚያት ሲካሄዱ የነብሩ ንግግሮች ቀጣይ እንደሆነ የተነገረለት ይህ ጉዞ ለአራት ቀን የሚደረግ ነው።  አሜሪካ አሁን በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋትና አለመረጋጋቱን ለማስታገስ በመንግስት በኩል እየተወሰደ ያለው አርምጃ  ስጋት እንደፈጠረባት በተደጋጋሚ መግለሷ አይዘንጋም። በተለይም በተቃዋሚ ፓርቲ አመራርና ደጋፊዎች፣ በጋዜጠኞች እንዲሁም ጥያቄ ባነሱ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚካሄደው የጅምላ እስር ወደ ሰላማዊ ንግግርና ውይይት እንዲቀየር ስትጎተጉት መቆየቷም የሚታወስ ነው።

የአስቸኳይ አዋጁና አሱኑ ተከትሎ በኢንተርኔት፣ በስልክና በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተወሰደውን የእግድ ውሳኔም ስትቃወም ነው የሰነበተችው። የኢህአዴግ ወዳጅ የሆነችው አሜሪካ እጅግ ዲፕሎማቲክ የሆነ የጽሁፍ መግለጫ ከማውጣት  / ከንፈር መጠጣ/ የዘለለ አቋም ባለመያዝዋ ስትተች ነው የኖርችው። የአሁኑ ጉዞ ውጤት ምን ውጤት እንደሚያስከትል ባይታውቅም፣ በሁለቱ መካከል ያለው ግንኙነት በቀድሞው መልኩ ስለመሆኑ ጥርጣሬ አላቸው። በተለይም አዲሱ የትራምፕ አስተዳደር ስራውን ሲጀምር ነገሮች ሊቀየሩ እንደሚችሉ ቅድመ ግምት አለ። በመንግስት በኩል አሁን እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎች ሁሉ አገሪቱን ወደ ነበረችበት ሁኔታ ለመመልስ ሲሆን፣ በተጓዳኝ ” በጥልቅ ተሃድሶ” የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ እየሰራ በመሆኑ ሁሉም ነገር ትክክል ነው። መተነኛ የሚባሉ የአፈጻጸም ችግር ቢኖር!!

አሜሪካ ቀደም ሲል አውጥታው የነበረውን የጉዞ ማስጠንቀቂያ ማራዘሙዋ የሚታወስ ነው። መንግስት አሁን በሚደረገው ንግግር ይህንኑ ጉዳይ ያነሳል ተበሎ የጠበቃል። የአሚሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ  ገጹ ያወጣው ማስታወቂያ የሚከተለው ነው።

Media Note

Office of the Spokesperson
Washington, DC
December 12, 2016

Assistant Secretary for Democracy, Human Rights, and Labor Affairs Tom Malinowski will travel to Ethiopia from December 14-17. During his visit, he will meet with government officials as part of a continued dialogue on human rights and governance. He will also meet with members of civil society, political party representatives, and local government officials during the visit.

Related stories   መሬት ወስደው ካላለሙት በመንጠቅ ለአልሚ ባለሀብቶችና ለወጣቶች እንደሚሰጥ ተጠቆመ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *