ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የት እና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ቤተሰቦቹ በተለያዩ ሚዲያዎች ገልጸዋል። ቤተሰቦቹ ለአሜሪካ ሬዲዮና ለጀርመን ድምጽ እንዳሉት ዝዋይ ማረሚያ ቤት እንደወትሮው ምግብ ለማድረስ ሲሄዱ ነው ተመስገን አለመኖሩን ያወቁት።
እንደ ወንደሙ ገለጻ ተመስገን ያለበትን ለማወቅ የመጨረሻው አካል የሚባሉትን ክፍሎች አናግሮ ምላሽ አላገኘም። የጤና ችግር ያጋጠመውና በቂ ህክምና አለማግኘቱ የተነገረለት ደሳለኝ በአመክሮ የእስር ጊዜውን ካገባደደ ወራት አልፈውታል።
ጠንካራ ትችት በማቅረብ የሚታወቀው ተመስገን የት እንዳለ የተጠየቁና ለጉዳዩ ቀጥተኛ አግባብ ያላቸው ባለስልጣን ” ዘዋይ እንዳለ ነው የማውቀው ” ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል። እሳቸው ይህን ቢሉም ቤተሰቦች በተደጋጋሚ ዝዋይ ሄደው ” እዚህ የለም” ተብለዋል። ስንቅ ይዘው ተመልሰዋል። እናም ተመስገን የት ነው? በዚሁ ተመስገን ጠፋ በተባለበት ሳምንት ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብቶች ቀን ማክበሯ የታውሳል።

የጅርመን ድምጽ ይህንን ዘግቧል – በሚያቀርባቸዉ ጽሑፎቹና ሃሳቦች ጥፋተኛ ተብሎ የሦስት ዓመት እስር የተፈረደበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደስአለኝ፤ ቤተሰቦቹ የተለያየ ፍርድ ቤት ቢፈልጉትም የለም እየተባሉ መመለስ ከጀመሩ ስድስተኛ ቀን እንደሞላቸዉ ለዶይቼ ቬለ ገለጹ።

Related stories   ምዕራባውያን የዘመናችን ሻይሎክ አረብ እስፕሪንግ የአረብ ዊንተር ሲሆን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *