ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

የ ” መሬት ስብ ” ልንዝቅ? ነዳጅ – ከ45 ዓመት በላይ ተስፋ!!

– ለወትሮው ገሃድ የማይነገረው የነዳጅ ቁፋሮ ጉዳይ

በኢትዮጵያ ኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት መገኘቱ ይፋ የሆነው እ.ኤ.አ. በ1972 ቴኔኮ ተብሎ በሚጠራ የአሜሪካ ኩባንያ አማከይነት ነበር፡፡ ከ40 ዓመታት በፊት በንጉሱ ዘመን የተገኘው የተፈጥሮ ሀብት ጥቅም ላይ አለመዋሉ በዘርፉ የተሰማሩትንና ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ዜጎች የሚንገበገቡበት ጉዳይ እንደሆነ በተለያዩ ጊዚያት በተለያዩ ሚዲያዎች የትገለጸ ጉዳይ ነው።
ከጋዝ ክምችቱ በዓመት ከአምስት እስከ ሰባት ሚሊዮን ቶን የሚደርስ ቡታጋዝ፣ ናፍጣ፣ ነጭ ጋዝና ቤንዚን ማምረት እንደሚቻል በጥናት የተደገፈ መርጃ እንዳለ በይፋ የሚታወቅ ጉዳይ ነው። ይሁንኑ “የመሬት ውስጥ ስብ” ጥቅም ላይ ለማዋል ሴኮር የተባለ የአሜሪካ ፣ ሜታኖል ጆይንት ስቶክና ስትሮይ ትራንስ ጋዝ ከተባሉ የሩሲያ፣ ሳይ ቴክ ኢንተርናሽናል የሚባል የዮርዳኖስ፣ እንዲሁም ፔትሮናስ የተሰኘው የማሌዥያ፣ ፔትሮትራንስ የተሰኘ የቻይና፣ እንዲሁም መሰረቱ ሆንግ ኮንግ የሆነና እንደ ጀርመን ሬዲዮ ገለጻ ንብረትነቱ የትግራይ መልሶ ማቋቋም እንደሆነ የሚታማው ሳውዝ ዌስት የተሰኘኩባንያዎች በካሉብና ሂላላ የሚገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ለማልማት የተለያዩ ስምምነቶች ያደረጉ ናቸው። አንዳቸውም ግን የታሰበውን ግብ እውን አላደረጉም። በካሉብና በሂላላ የሚገኘው የተፈጥሮ ጋዝ ጠቅላላ ክምችት 116 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ የሚገመት እንደሆነም ሪፖርተር በውቅቱ መዘገቡ የሚታወስ ነው።
እነዚሁ ኩባንያዎች በተለያዩ ምክንያቶች ውላቸው እየተቋረጠ፣ አንዳንዴም ውላቸውን ባለማክበር እየተከሰሱ መሰናበታቸው ይታወሳል። ፔትሮናስ ለሰባት ዓመታት ቁፋሮ ሲያካሂድ 500 ሚሊዮን ዶላር ግድም ወጪ ማድረጉ ይታወሳል።
ከዚህ በሁዋላ ነው እንግዲህ ታህሳስ 6 ቀን 2009 ዓም የመንግስት ዜና አገልግሎት ፖሊ ግሩፕ የተባለ የቻይና ኮርፖሪሽን በ3.7 ቢሊዮን ዶላር እያከናወኑት ያለው የነዳጅ ፍለጋ ውጤት ማስገኘቱን የጠቆሙት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም የኮርፖሪሽኑን ኃላፊዎች ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው አነጋግረዋል። የኮርፖሬሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ቡ ዩሎንግ በኦጋዴን አካባቢ የጋዝና የቤንዚን ፍለጋ ሥራው ውጤት አስገኝቷል ማለታቸው ተሰምቷል። ስራው በመጪው አራት ዓመታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ተጠቁሟል። ለወትሮው የጸጥታና የነጻ አውጪ ጥያቄ የሚቀርብበት ኦጋዴን እና የዘየት ቁፋሮን አስመልክቶ  የጀርምን ድምጽ የሚከተለውን ዘገባ በ 14.10.2010 ዘግቦ ነበር። በዘገባው ንብረትነቱ የትግራይ መለሶ ማቁቋም እንደሆነ የሚነገርለት የሳውዝ ዌስት ኢንጂነሪንግን ዋና ስራ አስፈጻሚ ማናገሩ አይዘነጋም። ሊንኩን ከፍተው ያድምጡ።
የ ” መሬት ስብ ” ልንዝቅ? ነዳጅ – ከ45 ዓመት በላይ ተስፋ!!
በተመሳስይ ቪኦኤ የሚከተለውን ብሎ ነበር
ላለፉት ሰባት አመታት በኢትዮጵያ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ላይ የቆየው የማሌዢያ ኩባንያ ፔትሮናስ በኢትዮጵያ ስራውን አቁሞ ከሀገር እየወጣ ነው። የነዳጅ ኩባንያው በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል በተለይ በኦጋዴን አካባቢ ለሰባት አመታት ያህል ነዳጅ ሲፈልግ ቆይቷል።

Related stories   "የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎችን ላለመላክ የወሰነው የማይታዘዝና የማያጎበድድ መንግሥት ይመጣል የሚል ስጋት ነው"አንዳርጋቸው ፅጌ

በክረምቱ ወራት ፔትሮናስ ለሰራተኞቹ የስንብት ደብዳቤ ከሰጠ በኋላ ድርጅቱ ኢትዮጵያን ለቆ እንደሚወጣ ግልጽ እየሆነ ቢመጣም፤ በይፋ ድርጅቱ እስካሁን መግለጫ አልሰጠም ነበር። በአዲስ አበባ ፔትሮናስ የዝግ ስብሰባ አድርጎ፤ ስራው መጠናቀቁንና ሳውዝ ዌስት ኤነርጂ ለተባለ ኢትዮጵያዊ ኩባንያ የነዳጅ ፍለጋ ያከናውንባቸው በነበሩት ስፍራዎችና ቁሳቁሶች ተረክቦ ስራ እንዲጀምር ስምምነት ላይ መደረሱን አስታውቋል።

የ South West Energy ስራ አስፈጻሚ አቶ ቴዎድሮስ አሸናፊ ለካፒታል ጋዜጣ ሲናገሩ “ይሄ ለ South West Energy ትልቅ እድል ነው። የነዳጅ ፍለጋና ምርቱን ለማስፋፋት ያስችለዋል” ብለዋል። ሳውዝ ዌስት ኤነርጂ በኢትዮጵያ በነዳጅ ዘይት ፍለጋ ከተሰማሩ ጥቂት አገር በቀል ድርጅቶች አንዱ ነው። ድርጅቱ ከፔትሮናስ ጋር የደረሰውን ስምምነት አስመልክቶ ዝርዝር መረጃ አልተሰጠም።
ፔትሮናስ በኢትዮጵያ እስካሁን ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንዳወጣ የሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። የካሉብና ሂላላ መሬቶች ላይ ፍለጋ ለማድረግ ለቀድሞው ማእድንና ኤነርጂ ሚኒስትር ከ80 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከፍሏል ይላል ዘገባው።
ይሄንን ያህል ገንዘብ የወጣበትን ስራ ለምን እንዳቆመ ፔትሮናስ በግልጽ የተናገረው የለም። ሪፖርተር ጋዜጣ የፔትሮናስ የነዳጅ ፍለጋ ባለሙያዎችን ጠቅሶ “በኦጋዴንና በገናሌ አካባቢ በቆፈሩት የፍለጋ ጉድጓድ የጋዝ ፍሰት ማግኘታቸውን ገልጸው፤ ይሁንና የጋዝ ፍሰቱ መጠነኛ እንደሆነ ተናግረዋል” ሲል ዘግቧል።
የሳውዝ ዌስት ኢነርጂ ስራ አስኪያጅ ቴዎድሮስ አሸናፊን ለማነጋገር ፈልገን በጉዳዩ አስተያየት መስጠት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል። ከዘገባዎች እንደተረዳንው ድርጅቱ ከ200 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለነዳጅ ማውጫ መድቦ ይንቀሳቀሳል።
በኦጋዴን አካባቢ የነዳጅ ማውጣት ስራ እግጅ አስቸጋሪ በሆነ የአየር ጸባይና የጸጥታ ሁኔታ የሚከናወን ነው። ከአምስት አመታት በፊት ቻይናዊያንና ኢትዮጵያዊያን በስራቸው ላይ ሳሉ በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ታጣቂዎች ጥቃት አድርሰው በርካታ ሰዎችን ገድለዋል።
ፔትሮናስም ሆነ ሌሎች የነዳጅ ዘይት አውጭ ድርጅቶች በአካባቢው እንዳይንቀሳቀሱና ፍለጋ እንዳያከናውኑ የሚጠይቀው ኦብነግ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ሳውዝ ዌስት ኤነርጂ የህወሃት የንግድ ድርጅት ነው፤ በአካባቢው የሚገኘውን ሀብት ከኦጋዴን ህዝቦች ለመውሰድ የሚጥሩ ሃይሎችን በሙሉ እንቃወማለን ብሏል።
http://amharic.voanews.com/a/ethiopia-oil-10-12-10-104815044/1462112.html

0Shares
0
Read previous post:
ተመስገን ተከቦ ለ3 ደቂቃ ወንድሙን አየ፤ታሟል

ላለፉት 10 ቀናት ደብዛው ጠፍቶ የሰነበተው እና በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዝዋይ ማረሚያ...

Close