ከቶውንም ትውልድ ላፍታም የማይረሳው ጸጋዬ ገ/መድህን

“ዱሮ ዱሮ፤ ሰው በሰው ነው አሉ ራሱን ፈልጎ ሚያገኝ የራሱን ጉድለት፣ የራሱን ማንነትና ምንነት የሚረዳው የሌላውን ቀርቦ መርምሮ አጥንቶ ነው ይባላል ። እኛ ግን በተቀራረብን ቁጥር እንተጣጣለን እንጠፋፋለን አንገናኝም በተጠጋጋን ቁጥር እንራራቃለን የቃላት ክምችት ኳኳታ ብቻ ነን የግስ ግሳንግስ እርባታ ቀፎዎች ለዚህም ነው እንደአሸዋ ባህር በቃላት ውጥንቅጥ! በቋንቋ ሽብር በግስ ግሳንግስ ተጥለቅልቀን! በቁምና በቅዠት አፋዊ ውዝግብ ስንንኳኳ የቀረን! ላንግባባ! ቤታችን በቃላት ግሳንግስ ታጥኖ ታፍጎ ለህሊናችን መተናፈሻ ቀዳዳ የጠፋብን ለዚሁ ነው በዘፈቀደ ከየፍልስፍናው የአንቡላ ጭልጭ ፉት ያልነውን ጠራዝ ነጠቅ የቋንቋ ብልጭታ ሌትና ቀን እያንባቧቸርን ስናስጎነብት አንድያችንን ተጠፋፋን ዓይናችንም እንደ አንደበታችን ግሳንግስ የደም ፍትወትን ለመደ! የአይን ወረት ጭዳ የሰሰቀኑን ሱስ ለመደ! ዓይናችን ጭምር! የሰው ትራፊ – የሰው ዕድፍ – የሰው ጥንብ ማስተዋል ምሳችን ሆነ! የሰዉን ጣር እንባ መሻት- የሰው ሰቀቀን ማነፍነፍ – ውሎ አድሮ ባህላችን ሆነ! ሌላው ካላደፈ የኛ ንፅህና! ሌላው ካልተጎሳቆለ የእኛ ጥጋብ ጎልቶ አልታየን አለ! ዓይናችንን የደም ፍትወት – የሰው ሰቀቀን ጭዳ አስለምደን አይለከፉት ልክፍት ተለከፍን! አዎን ፈራን! የነፍሳችንን አንደበት ዘጋን! ሰብአዊነታችንን ራሳችን – ከውስጣችን ነደን አክስመን ሰው የምንለው ሰብአዊ ፍጡር ቢጤአችን እያደር ከቶም አልገባን አለ”
እናት ዓለም ጠኑ
ፀጋዬ ገብረመድሕን

አቶ ጓንጉል ተሻገር በፌስ ቡክ ገጻቸው ለጥፈው ስላስታወሱን እናመሰግናለን

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *