“ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ትልቁ በሽታዬ ፣ የችግሮቼ ሁሉ ስር” ሲል ራሱን እንደገመገመ የሚናገረው ኢህአዴግ፣ በከፍ መንገድ ወዲያውኑ ለህግ ማቅረብ በሚያስችል ደረጃ ችግር አለባቸው ተብለው የተለዩ አመራሮች አለመኖራቸውን አስታወቀ። ለጊዜው ለህግ የሚቀርቡ ባይኖሩም ተጨማሪ የማጣራት ስራ የሚያስፈለጋቸው ጉዳዮች ተገኝተዋል። በዚሁ መነሻ በተጠረጠሩት ባለስልጣን ላይ እስከ ቤተሰብ የዘለቀ ምርመራ ይደረጋል።

ድርጅቱ ለጊዜው በከፋ ደረጃ ህግ ፊት የሚቀርቡ ባለስልጣናት አለመኖራቸውን በተገለጸበት ዜና ፣ ” ሚኒስትሮችን ጨምሮ የአብዛኛው አመራር ችግር ስልጣንን የዕለት ተዕለት ህይወት መመሪያ አድርጎ መጠቀም ነው” ሲል ያሰምርበታል። ፋና በኢህአዴግ ፅህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪው አቶ ተፈራ ደርበውን ጠቅሶ ባሰራጨው ዜና የማጣራት ስራው መቼና እንዴት እንደሚጣራ አላወሳም። በስልጣን መባለግ ጋር በተያያዘ ህዝብ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳለው፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ከአገሪቱ  በህገወጥ መንገድ መውጣቱ፣ ባለስልጣናትና በዙሪያቸው ያሉ ከፍተኛ ሃብት መሰበሰባቸው የአደባባይ ሚስጢር እንደሆነ ለዓመታት ሲነገርና ሲተቆም መቆየቱ የሚታውስ ነው።

Related stories   ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!

ሙሉ የፋና ዜና እንዲህ ይነበባል።

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢህአዴግ) ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም የግል ሃብት ያፈሩ አካላትን ወደ ህግ ማቅረብ የሚያስችል ተጨማሪ ማጣራት እያደረገ መሆኑን ገለፀ።

በኢህአዴግ ፅህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪው አቶ ተፈራ ደርበው ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፥ በእስካሁኑ የጥልቅ ተሃድሶ ግምገማ ሚኒስትሮችን ጨምሮ የአብዛኛው አመራር ችግር ስልጣንን የእለት ተዕለተ ህይወት መምሪያ አድርጎ መጠቀም ነው። ድርጅቱ ስልጣንን የግል ሃብት ማፍሪያ አድርገው ተጠቅመዋል ተብለው በተጠረጠሩ ባላስልጣናት ላይ እስከ ቤተሰቦቻቸው የደረሰ ምርመራ እንዲካሄድ መወሰኑንም ተናግረዋል።

“ህዝብ የሚያነሳቸው ቅሬታዎች መጥራት ስላለባቸው በሀሜት እና አሉባልታ ግለሰብ አመራሩ ላይ የሚነሱ ጉዳዮች ሳይቀሩ ህዝቡ በነፃነት እንዲያነሳቸው ለማድረግ ተሞክሯልም” ነው ያሉት። መንግስትም ሆነ መንግስትን የሚመራው ድርጅት ስልጣንን አላግባብብ መጠቀም ትልቁ በሽታየ፤ የችግሮቼ ሁሉ ስር ብሎ ገምግሟል።

Related stories   "በፕሮፓጋንዳ እስካሁን የተወናበድኩት ይበቃኛል ብሎ ቆም ብሎ ማሰብም ይገባል ... ወጣቱን ያለ እድሜው ህይወቱን ይቀጩታል"ሌ.ጀ ዮሐንስ

ይሁን እንጂ ጥልቅ በተባለው ግምገማ ስልጣንን የሀብት ማፍሪያ፣ የብልፅግና መሰረት ያደረገ ተሿሚ አልተገኘም ወይ? የሚል ጥያቄ ይነሳል። አስተባባሪው “በግምገማዎቹ በከፋ መንገድ ወዲያውኑ ለህግ ማቅረብ በሚያስችል ደረጃ ችግር ያለባቸው ተብለው የተለዩ አመራሮች የሉም፤ ነገር ግን ተጨማሪ የማጣራት ስራ የሚጠይቁ ጉዳዮች እንዳሉ ተለይተዋል” ብለዋል። ጥቆማዎቹ ተጣርተው ሲጠናቀቁም ተጨባጭ የህግ ተጠያቂነት የሚኖራቸው እንደሚኖሩም ገልጸዋል።

አቶ ተፈራ እንደተናገሩት፥ ሙስና በረቀቅ መንገድ የሚፈፀም ተግባር በመሆኑ ከግምገማው ማግስት ለፍርድ የሚቀርቡ ሹማምንት ባይገኙም የበለጠ ማጣራት ይካሄድባቸው የተባሉ ግን አሉ። እነዚህም ጉዳይን ለማስፈፀም በአይነት የሚሰጥ ስጦታን፣ ጥሬ ገንዘብን በእጅ መንሻነት በመቀበል ተግባር የተገመገሙ ሲሆን፥ በዚህ ተግባር የተጠረጠሩትን ከሃላፊነት ከማንሳት ጀምሮ ሌሎች ፖለቲካዊ እርምጃዎች ተወስዶባቸዋል ብለዋል።

Related stories   "ኢትዮጵያን የውስጥና የውጭ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው ሊያጠፏት የተነሱበት ወቅት ላይ እንገኛለን፤ ሁሉም አንድ መሆን ይገባዋል – የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም

በግምገማው ያልተደረሰበት በስልጣን መሳሪያነት የተከማቸ ሀብት መኖሩ የአደባባይ ምስጢር ነው የሚሉ አሉ። ኢህአዴግም ከ15 አመታት በኋላ የተካሄደው ተሃድሶ፤ በአስራ አምስት አመታት እና ከዚያ በላይ በሆነ ጊዜ የተፈፀመ ተግባር በፖለቲካ እና ግለሰባዊ ግምገማ ብቻ ሊደረስበት አይችልምና መስቀለኛ ማጣራት ይካሄድ የሚል ውሳኔን አሳልፌያለሁ ይላል።

አሁን ላይ የእያንዳንዱ ተሿሚ ባለስልጣን የሀብት መጠን መመዝገቡንም ነው አቶ ተፈራ ደርበው የገለፁት። በመሆኑም ህዝቡ በግለሰብ ደረጃ የተሿሚዎች የሀብት መጠንን የማወቅ መብት አለው፤ አመራሩ ከተመዘገበ ሀብቱ ውጭ ሌላ ተገቢ ያልሆነ ሀብት አካብቷል ብለው ካሰቡም ለሚመለከተው አካል መጠቆም እንደሚችሉም ጠቅሰዋል። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የመንግስት ተሿሚ ባለስልጣን የሀብት መጠን መረጃን ከፌደራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ማግኘት እንደሚችልም ተናግረዋል።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *