የዛጎል ዜና፡- የአሚሪካ ኤምባሲ ያውጣው መግለጫና ታም ማሊኖውስኪ ተናገሩት የተባለው ብዙም የሚስማሙ አይመስልም። ረቡዕ ታኅሣስ 5/2007 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የገባውን ለዑክ የመሩት ባለስልጣን ኢትዮጵያን በሚተከተክ ማሰሮ በመመሰል ከዓመት በፊት ያስጠነቀቁትንና የተከራከሩበትን አንስተዋል። በዚሁ ንግግራቸው ማሰሮው ከታፈን መንተከተኩ አያቆምም፤ እንደውም ይገነፍላል።
ባለፈው ዓመት ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ሲነጋገሩ ታም ማሊኖውስኪ ” አገሪቱ አሁን ያለችበት ሂደት በእሳት ላይ ተጥዶ እንደሚንተከተክ ማሰሮ ይመስላል። እናም እንዲህ የሚንተከተክ ማሰሮ ለማስተንፈስ ያለው ምርጫ ክዳኑን ማንሳት ብቻ ነው፤ ያ ካልተደረገ መንተከተኩ አያቆምም። በዛ ከቀጠለ ደግሞ መገንፈሉ አይቀርም። ከዚያ በሁዋላ የሆነው ሁላችንም እናውቀዋለን” እንደ ቪኦኤ ዘገባ
ከታህሳስ 15 ቀን 2007 ዓም ጀምሮ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ስላደረጉት ንግግር መግለጫ ለመስጠት ተቀምጠው ከዓመት በፊት ተከራከረኩበት ያሉትን የ”ነብይ” አይነት ማስጠንቀቂያ ማስቀደማቸው አኤምባሲው ካወጣው የተለመደ መግለጫ ጋር ብዙም የሚስማማ አይመስልም። ይሁን እንጂ ንግግሩ ከዚህ ቀደም ከተደረጉት ይልቅ ግልጽ፣ ጥልቅና ሁሉን አቀፍ እንደሆነ ተመልክቷል። ነገር ግን ግልጽ፣ ጥልቅና ሁሉን አቀፍ ከመባሉ ውጪ ሁሉም ጉዳይ ለጊዜው የተድበሰበሰ እንደሆነ ጉዳዩን የሚከታተሉ ይገለጻሉ። ” ይህ የአሜሪካኖች አካሄድ ነው። ውጤቱ ማየቱ ይሻላል ” የሚሉም አሉ።
በዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ታም ማሊኖውስኪ የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቡድን ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢትዮጵያ አስተዳደርና ሰብዓዊ መብቶችን በሚመለከቱ ስፋት ያላቸው ጉዳዮች ላይ በግልፅነት ለመወያያት እንደተስማሙ የንግግሩ ጊዜና መርሃ ግብር ከተጠናቀቀ በሁዋል አዲስ አበባ ያለው የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ አውጥቷል።ቪኦኤ መግለጫን አስመልክቶ የሚከተለውን አትሟል።
በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ የሚመሩት የሁለቱ ሃገሮች ቡድኖች ያደረጓቸው ውይይቶች የኢትዮጵያ መንግሥት የሃገሪቱን የምርጫ አያያዝ ለማሻሻል የገባውን ቃል እንዲገፋበት ማሳሰብን ጨምሮ ስፋት ባላቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ኤምባሲው አክሎ አመልክቷል፡፡
በተጨማሪም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት ሕገ-መንግሥታዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ ለውይይት ሁኔታዎች አንዲመቻቹ፣ ጠንካራ መገናኛ ብዙኃን እንዲኖሩም ውይይቱ ትኩረት አድርጎ መነጋገሩን መግለጫው ጠቁሟል፡፡
መሠረታዊ ነፃነቶች እንዲከበሩ በማድረግ የጥላቻ ንግግሮችን ለመቆጣጠር እንዲቻል፣ የሲቪል ማኅበረሰብ አስፈላጊ ጫና ለመልካም አስተዳደርና ለዓመታዊው የዩናይትድ ስቴትስ የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት ያለውን ጥቅም አንስተው የሁለቱ ሀገሮች ቡድኖች መክረዋል፡፡
በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሂሩት ዘመዴነህና በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ጉዳይ ፈፃሚ ፒተር ቨርማን ተባባሪ ሊቀመንበርነት የተመራው ይህ ሰባተኛው የሥራ ቡድን ስብስባ ወደፊት በሚያደርጓቸው ውይይቶች በግልፅነት ለመነጋገር መስማማታቸውን የኤምባሲው መግለጫ አመልክቷል፡፡
በተመሳሳይ ዜና አሜሪካ የጣለችውን የጉዞ ማስጠንቀቂያ እንድታነሳ ጥያቄ መቅረቡን ያመለከቱ ክፍሎች፣ ግልጽ ያለ ምላሽ ባይሰጥም ጉዳዩን እንደሚመለከቱት ቃል መግባታቸውን አመልክተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *