በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ ወቅቱ የኢትዮጵያ ችግር አጣዳፊ መፍትሔ የሚሻው ነው አሉ፡፡ እንደ መፍትሔ ካሉዋቸው መካከል አንዱና ዋነኝ ቁልፍ የሆኑ እስረኞች መፍታት ነው ብለዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን ይህን የገለፁት ለቪኦኤ ብቻ በሰጡት ቃለ ምልልስ ሲሆን በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከመንግሥት ባለሥልጣናት ከፖለቲካ ተቃዋሚ መሪዎችና ከሲቪል ማህበረሰብ መሪዎች ጋር መወያየታቸው ይታወቃል፡፡