በአሜሪካ ጉብኝት በሚያደርጉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ ዝልፊያ የፈፀሙ ግለሰቦች በአገሪቱ በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው ፍርድ ቤት እየቀረቡ ነው በማለት ፋና ብሮዲካስቲንግ ያሰራጨው የሃሰት ዜና የአገዛዙን ግራ መጋባት የሚያጋልጥ እንደሆነ ተገለጸ

የፋና ብሮዲካስትንግ ዓርብ ታህሳስ 14፣ 2009 ዓመተምህረት ከአገሪቱ ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር አገኘሁት ብሎ ባሰራጨው በዚህ የሃሰት ዜና ላይ ከኢትዮጵያ ሳታላይት ቴለቪዥንና ሬዲዮ ጋዘጠኛ ከመሳይ ከበደ ጋር ቃለ መጠይቅ ያካሄደው አንደኛው ተከሳሽ ቴዎድሮስ ካብተይመር እንዳረጋገጠው የትግራይ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆኖ በማገልገል ላይ የሚገኘው የህወሃት ሹም ዶር አዲስ አለም ባሌማ ተደበደብኩ በማለት በግሉ የግብረ ሃይሉ አባል በሆነው ተከሳሽ ላይ ከመሠረተው መሠረተ ብስ ክስ ሌላ በቬርጅንያ መንግሥት የተከፈተ ምንም አይነት ክስ እንደሌለ አረጋግጦአል።

አሜሪካ የህግ የበላይነት የሰፈነባትአገር በመሆኗ ማንም ሰው እንኳን ነፍሰ ገዳይ በሆኑ የህወሃት ባለሥልጣኖች አይነቱ ላይ ቀርቶ በገዛ አገሯ ፕሬዝዳንት ላይ እንኳ ቢያሰማ በወንጀል የሚከሰስባት አይደለችም ያለው ወጣት ቴዎድሮስ ካብትይመር በአሜሪካ የሰፈነውን ይህን የዜጎች ነጻነት የማያውቅ ኢትዮጵያዊ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ ስለሌለ በህወሃት የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር የተሰራጨው ዜና ማንንም ሊያደናግር አይችልም ብሎአል።

Related stories   “ጣልያኖችም ሆኑ እንግሊዞች ቅኝ ግዛትን ለማስቀጠል ህዝቡን በዘር መከፋፈልን እንደ አንድ ስልት ይጠቀሙ ነበር” -አቶ ታቦር ገረሱ ዱኪ

በአጋዚ ነፍሰ ገዳዮች ልዩ ጥበቃና የታዘዙትን በሚፈርዱ ዳኞች አማካይነት አገር ውስጥ እንደፈጣሪ መፈራትን የለመዱ የህወሃት ባለሥልጣኖች በምዕራቡ አለም ተበትኖ የሚኖረው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ በሚፈጽሙት ወንጀል ምክንያት ዱካቸውን እየተከታተለ ሲያሸማቅቃቸው በለመዱት መንገድ የምዕራቡ ፍርድ ቤቶች በእድሜ ይፍታህ የሚቀጡላቸው እየመሰላቸው ከፍተኛ የአገር ሃብት እያፈሰሱ ጠበቃ በመቅጠር ወደ ፍርድ ቤት ይሮጣሉ ብሎአል ቴዎድሮስ ካብትይመር።

ዶር አዲስአለም ባሌማ ዋሽንግተን ዲስ ላይ ያዋረደውንና አንገት ያስደፋውን የዲስ ግብረሃይል አባል በክስ ፍርድ ቤት ለማቆም ለጠበቃ የከፈለው ብዙ  ሺ ዶላር ከኢትዮጵያ ደሃ ህዝብ በግብር ሥም የተሰበሰበ እንደሆነ ይታወቃል። ሼህ አላሙዲንና የህወሃት አገዛዝ ተቃውሞ ያደረሱባቸውን የዲያስፖራ አባላት ለመክሰስ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የከፈቱት የክስ መዝገብ ያለምንም መንዛዛት ውድቅ እየተደረገባቸው ኖሮአል።

የህወሃት አገዛዝ ላይ በውጪ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ እየፈጠረ ያለው ጫናና ተቃውሞ በአሜሪካ መንግሥት ሳይቀር እውቅና እያገኘ መምጣቱና አገር ውስጥ እየተካሄደ ላለው ሁለገብ ትግል ከፍተኛ አጋዢ ሃይል መሆኑ አገዛዙን እረፍት እየነሳው መምጣቱን ሃይለማሪያም ደሳለኝ የተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ከሰጠው ምስክርነት ለማረጋገጥ ተችሎአል።

Related stories   “በአጣዬ እና አካባቢው በተፈፀመው ወንጀል ተጠያቂ የሚሆኑ አካላት ለፍርድ ይቀርባሉ” ኮማንድ ፖስቱ

አባይ ሚዲያ  ትንሳኤ ሬዲዮን ጠቅሶ እንደዘገበው-

የፋና ዜና ይህ ነው

በአሜሪካ ጉብኝት በሚያደርጉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ ዝልፊያ የፈፀሙ ግለሰቦች በአገሪቱ በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው ፍርድ ቤት እየቀረቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ከተፈረጁ ድርጅቶች ከግንቦት ሰባት እና ኦነግ ጋር በትብብር በመስራት በኢትዮጵያ መንግስትና ባለስልጣናት ላይ ዝልፊያ በሚፈጽሙ ግለሰቦች ላይ በአሜሪካ የቨርጂንያ ግዛት መንግስት ክስ በመመስረት ፍርድ ቤት ማቅረብ ጀመረ።

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ወደ አሜሪካ ጉብኝት በሚያደርጉበት በተለያዩ ጊዜያት ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር የአሜሪካን ሰላምና ፀጥታ ባደፈረሱ የግንቦት ሰባት እና ኦነግ አባላት ላይ ጠንካራ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ የቨርጂንያ ግዛት መንግስት ወደ ፍርድ ቤት ማቅረቡን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ላይ አተኩሮ ከዩናይትድ ስቴትስ በኢንተርኔት የሚሰራጨውን ቲጂ ቴሌቪዥንን ጠቅሶ ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ቀንደኛ የግንቦት ሰባት እና ኦነግ አባላት የቀድሞው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ሬድዋን ሁሴን እና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር አዲስአለም ባሌማን ጨምሮ በተለያየ ጊዜ ወደ አሜሪካ ያመሩ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ ፀያፍ ስድብ እና ህገወጥ ድርጊት መፈፀማቸውን አንስቷል።

Related stories   በሳሊቫኪርና በሪክ ማቻር መካከል እያገረሸ ያለውን ቅራኔ እየተባባሰ በመምጣቱ በደቡብ ሱዳን አዲስ ግጭት እንዳያገረሽ ተሰግቷል

ራሳቸውን “የዋሽንግተን ዲሲ ግብረ ኃይል” ብለው የሚጠሩ የግንቦት 7 ሽብር ቡድን መሪዎች ቴዎድሮስ ካብትይመር፣ ኤርሚያስ እሸቱ እና ጌታቸው ሞርኪ መኮንን በአሜሪካ የማያስጠይቅ የመሰላቸው ፈር የለቀቀ ተቃውሞ መሳይ ህገ ወጥ ተግባር በፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ እና ክስ እንዲመሰረትባቸው አድርጓል ነው የተባለው።

የቨርጂኒያ መንግስት ቴዎድሮስ ካብትይመር የተባለውን ግለሰብ ክስ መስርቶበት ፍርድ ቤት አቅርቦታል።

ሶስቱም የግብረ ሀይሉ መሪዎች የአከባቢውን ሠላምና ፀጥታን በማደፍረስ ወንጀል፣ በግለሰቦች ላይ ጥቃት በማድረስና ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ በመቃወም በህዝቡ ላይ ፍርሃትና ድንጋጤ በመፍጠር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል።

የግብረ ሀይሉ መሪ ነን የሚሉት እና በፀያፍ ስድባቸው የሚታወቁት እነዚህ ግለሰቦች የተከሰሱበት ወንጀል በፈረንጆቹ ጥር 27 ቀን 2017 በላውደን ካውንቲ ፍርድ ቤት እንደሚታይም ነው የተመለከተው።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *