“Our true nationality is mankind.”H.G.

የመንግስት ታጣቂዎች ወደ መንደራቸው እንዳይገቡ በመከልከላቸው የአራት ቀበሌ ነዋሪዎች ቤቶቻቸው መቃጥሉን ተናገሩ፤ መንግስት ‘ሃሰት ነው’ይላል

በደልን ለመቋቋም በሚል ” የወሎ ማህበረሰብ አንድነት” በሚል የተደራጁ ስለመኖራቸው፣ እነዚሁ ክፍሎች የታጠቁ የመንግስት ሃይሎች ወደ አካባቢያቸው ዘልቆ እንዳይገባ በማድረጋቸው ሳቢያ ግጭት መቀሰቀሱ ተጠቆመ። የመንግስት ወገን በበኩሉ ” ግጭት የሚባል ነገር ሰለመኖሩ የሚታወቅ ነገር የለም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የአራት ቀበሌዎች የመኖሪያ ቤቶችና ንብረት መቃጠሉን በዚህም ሰፊ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ቢናገሩም አሁንም ከመንግስት ወገን ” የልማት ስራን ለማስቀጠል ውይይት ላይ ነን” የሚል ምላሽ ነው የተሰጠው።

ዶቼቨሌ እንደዘገበው በአማራ ክልል  የኦሮሚያ ልዩ ዞን  ከሚሴ በሃርጡማ ፉርሴ ወረዳ፣ በራሳሙሬ ቀበሌ በነዋሪዎችና በፀጥታ አስከባሪዎች መካከል ግጭት ተነስቷል። ባለፈው ሰኞ በደረሰው ግጭት ፀጥታ አስከባሪዎች በአራት ቀበሌዎች ዉስጥ የሚገኙ የመኖሪያ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ማቃጠላቸውን  ዘገባው አመልክቷል። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ጸጥታ አስከባሪዎቹ እርምጃውን የወሰዱት የአካባቢው ህዝብ “አልተባበረንም”  በሚል ነው።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

ስማቸው እንዳይጠቅስ የጠየቁን ሌላ የሃርጡማ ፉርሴ ነዋሬ በሰኞው ግጭት አንድ ሰው መሞቱንና  አንድ ግለሰብ ቆስሎ ሆስፒታል እንደሚገኝ ተናግረዋል ። በግጭቱ አንድ የቀበሌ አስተዳደር ጉዳት እንደደረሰባቸውም  የዶቼቬለ ዘገባ ያስረዳል።

” የፀጥታ አስከባርዎች፣ የአሸባሪዎችን ዓላማ ታራምዳላችሁ። እንዲሁም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አባል ናቸሁ። በማለት ግለሰቦችን ወስደው በመግረፋቸዉ ፣ በእስር ቤት  በብልታቸዉ ላይ ከባድ ነገር በማንጠልጠላቸዉና ተመሳሳይ ድርጊት በመፈጸሙ  ህዝቡ ‘ የወሎ ማህበረሰብ አንድነት’ የሚባል ድርጅት አቋቁሞ በተቻላቸዉ መጠን የመንግስት ፀጥታ አስከባሪዎች ወደ አከባቢው እንዳይገቡ በማድረጉ ለግጭቱ መንስኤ ነው” ሲሉ በዘገባው የተጠቀሱ ግለሰብ ተናግረዋል።

Related stories   “…ለዛሬ ብለን ነገን ከምናበላሽ፣ ለነገ ስንል ዛሬን እንሠዋ” አብይ አህመድ

“ይህ ድርጅት ማነዉ ያቋቋመዉ? እንዴትስ ልቋቋም ቻለ?”  በሚል ለተጠየቁት ፣ “…ማህበረሰቡ ተስማምቶ ነዉ። ምክንያቱም በኦሮሚያ ዉስጥ ያሉት ‘ቄሮዎች’ ችግር ስላጋጠማቸዉ የቀሩት የማህበረሰቡ አካል ወንድሞቻችን ተበድለዋል የሚል ስሜት ተስምቷቸዉ ነዉ። መንግስትም በሰላም ወጥተው በሚገቡ ግለሰቦች ላይ የእስርና የማሰቃየት ርምጃ መዉሰድ ሲጀምር ማህበረሰቡ ወደ መሣርያ ለማንሳት ተገደደ” ሲሉ መልሰዋል።

ወታደሮች በ 12 መክናዎች ደረሰው ሄጂራ፣ ራሳ፣ ዋጮታና ጃባስባ በሚባሉ  አራት ቀቤሌዎች የመኖሪያ ቤቶችን እንዳቃጠሉና  በቃጠሎውም የቤት እንስሳትና የተለያዩ ንብረቶች መዉደማቸውን እኝህ ግለሰብ ይናገራሉ። ዶቼቨሌ ያናገራቸው የከሚሴ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሰሎሞን ካብትይመር ግን “በማህበረሰቡና በፀጥታ አስከባሪዎች መካከል የተፈጠረ ግጭት የለም” ብለዋል።

“በተባለዉ መልክ የተፈጠረ ግጭት የለም። እኔም አሁንም በሃርጡማ ወረዳ ነዉ ያለሁት። የልማት ኮንፊረንስ ለማካሄድ ዝግጅት ላይ እንገኛለን” ያሉት ሃላፊው፣  “ቤት ተቃጠለ የሚባለዉን አልሰማሁም መረጃዉም የለኝም” ሲሉ ተናግረዋል።   ለወደፊት አከባቢዉን መንከባከብ በተመለከተ እንዴት መከናወን እንዳለበት ውይይት እየተደረገ መሆኑንንና ከዚህ የተለየ መረጃ እንደሌላቸው አክለው ሃላፊው ተናገረዋል።

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

ከዚሁ ዜና ጋር በተያያዘ በዶቼቬሌ ድረ ገጽ ላይ አስተያየት መሰጠቱን ያመለከተው ዘገባ አስተያየተ ሰጪዎቹ የከሚሴ ነዋሪ መሆናቸውን አመልክተዋል። በአስተያየታቸው  “እኛ ጋር ፍፁም ሰላም ነው። ከሚሴ ዛሬም ነገም የሰላም መዲና ናት” ሌላው ወገን ደግሞ “አሁን እዛው  ከሚሴ ነኝ። የታጠቀ ሠራዊት ልጆቻችሁን አምጡ ብለው የህዝብ ቤቶችን እያቃጠሉ ነው፤ ያሳዝናል” ሲሉ እናውቃለን የሚሉትን ምስክርነት ሰጥተዋል።

ምንጭ

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0