ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ-

በአሁኑ ጊዜ ለኢትዮጱያ ህዝቦችና መሬታቸው ለመበታተን በዘመነ ወልዳአብ ወልደማሪያም ተነስቶ ተቀባይነት አጥቶ ከስሞ የቀረ ። በኃላም በሀወሐት አማራር ብቅ ብቅ እያለ የመጣ ፣አሁን ደግሞ ከዘመናት በኃላ አዳዲስ ጽንፈኛ ባንዳዎች ወጣትችና ጥቂት አዛውንቶች የዘመናት የቆዬ አባት አያቶቻቸው የባንዳነት ዝናር ለወጣቶች በማስታጠቅ ፣ ማህበረ አግአዝያን በሚል የተዘባረቀ ትንተና አገርና ህዝብ የሚበታትን ፣ብሎም የሀይማኖት ፣የባህል ጦርነት የሚቀሰቅሱ ፣በኤርትራና በትግራይ የሚገኙ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዏችና የክርስትና ሀይማኖት ተቆርቋሪ መስለው በፌስ ቡክ ፣በዩቲብ ወዘተ በመርዝ የተለወሰ መልእክታቸው እያሳራጩ ይገኛሉ ።

እነዚህ አገርንና ህዝብን ለመበታተን እየተፈላሰፉ ያሉ የዘመናችን ጽንፎኞች እነማን ናቸው ?

1ኛ) በግንባር ቀደምትነት የተሰለፈው ተስፋጽዬን የተባለ ኤርትራዊ አንድ ጊዜ ከጀብሀ ፣ አንድ ጊዜ ከሸአብያ እየተሰለፈ የኖረ ፣ አንድ ጊዜ ደግሞ ከውጭ ሀገር ወደ አዲስ አበባ እየተመላለሰ ራሱ በዩቲብ ሰአታትን ጊዜ የፈጀው እንደገለጸው ከህወሓት አማራር ስብሀት ነጋ እና ሌሎች እየተገናኜ ስለ የአግአዝያን አላማ ይወያይ እንደነበረ እና ከሌሎች ሙሁራኖች ነን ከሚሉ የትግራይ ተወላጅ በድህረገጽ እንደሚገናኝ ይተነትናል ።
ተስፋጽዬን ቀደምትነት ተባባሪዎቼ ናቸው ከሚሏቸው በግንባር ቀደምትነት በዩቲቡ እንደገለጸው በትግራይ የአግአዚያን ቁንጮ አድርጎ እንዳስቀመጠው መሀሪ የውሀንስ የመቀሌ ዩንቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ አስተማሪ መሆኑ ይጠቀሳል ። በተጨማሪም የማይናቅ ቁጥር ያላቸው ጽንፈኛ የትግራይ ሙሁራኖች አጨብጫቢዏች እንዳሉም ተሰፈጽዮን ይገልጻል ።

2ኛ) ተስፋጽዮን በዩቲብ እንደገለጸው በኤርትራም ትግርኛ ተናጋሪዏች የአግአዚያን ደጋፊዏች አንደሉት ይናገራል ።

ተስፋጽዮን እንደሚለው የአግአዝያን አላማ

1ኛ የትግራይና የኤርትራ ትግርኛ ተናጋሪዎች ክርስትና ሀይማኖት ብቻ የሚያምኑ በአንድ ትግራይ ትግርኝ አደራጅተው ቀይባኽር በመቆጣጠር ጠንካራ የሰሜን መንግስት መመስረት ይላል ፣

2ኛ የአፋር የሳሆ ፣ የሚኒአምር ፣የትግረ ፣ የኩናማ ፣የምስልምና ዘርና እምነት ያላቸው መጥፋት አለባቸው፣ በትግራይ ትግርኝ መንግስት አይካተቱም ፣ትግራይ ትግርኝ ብቻ መሆን አለባቸው ልዩ ፍጡራን ስለሆኑ ይላል ። በተለይ ምስልምና እምነት ተከታዮች ጭራሹ መጥፋት አለባቸው ይላል ።

3ኛ ተስፍጽዮንና ጽንፈኛ የአግአዝያን ሴጣኖች ከሌሎች ኢትየጱያውያን በተለይ ደግሞ ከአማራ የጥንት ጠላቶች ስለሆኑ ይቅርና ከነሱ ልንኖርስ ይቅር ለአይናችንም ማየት የለብንም መጥፋት አለባቸው ይላል እብዱ ተስፋጽዮን ኤርትረዊ ።

4ኛ የኤርትራና የትግራይ ትግርኛ ተናጋሪ ክርስትና ሀይማኖት ብቻ የሚከተሉ ወይ የሚያምኑ ሀይለኛ ወታደራዊ ሀይል በመመስረት ቀይባህርን ከጫፍ እስከ ጫፍ በመቆጣጠር የማይደፈር የሰሜን ትግራይ ትግርኝ ሰራዊት እናንጻለን ። ይላሉ የአግአዝያን ትግራይ ትግርኝ እብዶች ።

የተከበራችሁ የኢትየጱያውያን ወገኖች እኔ የትግራይ ህዝብና የኤርትራ ህዝብ ሀይማኖት በማይለይ አንድ ሆኖ ተቃቅፎ ወንድም እህት ሆኖ ሊኖር አልቃወምም ። ከአሁን በፊትም እኛ እናውቅልሀለን የሚሉ የነበሩ ህወሐት ፣ ሸዓብያ ፣ ጀብሀ ሌሎችም የፈጠሩት መነጣጠል ነው እንጅ ኤርትራውያንና የትግራይ ህዝብ ከመላው የኢትዮጱያ ህዝበ አንድ የነበረ በጋብቻ በባህል በሀይማኖት ተሳስሮ አብሮ ሲኖር የነበረ ነው ። ይህ ሲሆን ግን ሁለቱ የሰሜን ኢትዮጱያ ክፍለ ሀገራት ኢትየጱያውያን ለመሆን ከሆነ በአንድ የሚያብሩት ኢትዮጱያዊ እሴታቸው ሳይሸረሸር ከሆነ የሚተቃቀፉት ማንም ዜጋ የሚቃወመው አይደለም ይህ አስተሳሰብ ግን ከሁሉም የኦሮሞ አፋር ፣ሱማል ፣አማራ ፣ደቡብ ወዘተ ሀይማኖት በማይለይ መኖር ያለበት አንድነትና መተቃቀፍ መሆን አለበት ።

ሁለቱ ትግርኛ ተናጋሪዏች ከጠባብ አስተሳሰብ ተነስተው ለሌሎች ኢትየጱያውያን የሚያገሉና ጥላቻ የሚያስፋፉ ፣ የሌሎች እምነቶች እና ቢሄር እንደጠላት የሚመለከቱ ወይ የሚያቋሽሹ የሀይማኖት የዘር ግጭት የሚቀሰቅሱ ፣ ከሆኑ ግን የአክራሪውና ጽንፈኛ የተስፋጽዮነ ኤርትራዊ አላማ ተከታዮች ከመሆን ውጭ ሌላ ሊባሉ አይችሉም ።

ለመሆኑ ተስፋጽዮን ኤርትራዊና ተከታዮቹ አግአዝያን አንስተውት ያሉ ኃላ ቀርና ጽንፈኛ አጀንዳ አሁን የተጠነሰሰ ነው ? ወይ የቆዬ አጀንዳ ይሆናል ? እስቲ ንመልከት ፣

ይሀ አጀንዳ በ1950 ዓመተ ምህረት አንስተውት የነበሩ ወለደአብ ወልደማርያም ነበሩ ። እሳቸው ግን የሀይማኖት ልዩነት አያንጸባርቁም ነበሩ ። ባንጸባርቁም ግን ኃላ ያደርጉት የነበረ መደጋገፍ ለክርስትያኖች ያደላ ነበር ። ወልደአብ ወልደማርያም የነበራቸው ፍላጎት የግዛት መስፋፋት ነበር ። እሱም መተማን ፣ ወልቃይት ጸገደ ፣የሰሜን ተራራዏች እስከ ወልድያ ፣አፋር ፣ኤርትራ ፣ትግራይ ፣ቀይባህር ያጠቃለለ ትግራይ ትግርኝ ጠንካራ የሰሜን መንግስት እንመሰርታለን በሚል ጸረ ኢትየጱያውያን በተለይ ደግሞ ጸረ የአማራ ቢሄር ስርአት ለመመስረት ሀሳብ ነበራቸው ። እንዳውም ለአማራ ቢሄር ከነበራቸው ጥላቻ ” የአማራ ህዝብ ይቅርና ሊመሩህ ልትመራቸውም አስቸጋሪዎች ናቸው ፣በመሆኑም ከአማራ አብሮ ለመኖር አይቻልሞ” ይሉ ነበር ።
የወልደአብ ወልደማርያም አቋምና ሙኞት ግን በትግራይ ተወላጅች ጠንካራ ኢትዮጱያዊነት ወኔ ፍቅር በተሞላበት ተቃውሞ በማሳየታቸው አለተሳካም ። በተለይ ደግም የወልደአብ ወልደማርያም ጠባብና አስፋፊ እስትራተጂ ተቃውመው ካፈረሱባቸው የማይምበረከኩ ኢትየጱያውያን እነ አቶ ገሰሰው አየለ ፣ አቶ ስዩም ገብረኪዳን ፣ ኃለም በወጫለ 25 ወገኖች ተረሽነው በበልዚን ከተቃጠሉት አንዱ የሆነ ፣ግራዝማች ሐዱሽ ኑሩሑሴን ሰወስቱ ከሽሬ ሌሎችም ነበሩ ። ከዛ በኃላ የወልደአብ ወለደማርያም አስፋፊ አለማ በኤርትራ ትግርኛ ተናጋሪዎች ተንጠልጥሎ ወይ ታጥሮ ቀረ ።

ሌላ የትግራይ ትግርኝ ጠባብና የመገንጠል አቋም የተንጸባረቀው ህወሐት ከተመሰረተ በኃላ ትግራይን ለመገንጠል ስትራተጅ ያስቀመጠ ነጻ ሀገር ( ነጻ ርፓፕሊክ ትግራይ ) ለመመስረት ነው የምንታገለው የሚለው ፕሮግራም ( ማኒፌስቶ ) ጥቂት የህወሐት አማራር የነደፉት ፕሮግራም ከወለደአብ ወለደማርያም አቋም ተመሳሳይነት የነበረው ነው ።

ከሚያመሳስሉት ነጥቦች አንዱ የህወሐት አመራር ምንም ታሪካዊ መንደርደሪያ ወይ መነሻ የሌላቸው ስለኤርትራ ከኤርትራውያን በላይ ተቆርቋሪ ሆነው ኤርትራ ለመገንጠል ከ1967 ዓ ም እስከ 1987 ዓ ም ጠበቃ መሆን ብቻ ሳይሆን የኤርትራ ቡዱኖች በደርግ እንዳይሸነፉ በ10 ሽዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ወጣቶች ወደ ኤርትራ በረሀ ሳህል በመስገባት በጸረ ደርግ ጦርነት በመማገድ ቡዙ ሽዏች ያልወለዱዋቸው ወጣቶች ለመስዋእት ዳርገው ሀገራችን ከመገነጣጠል አልፈው የባህር ባለቤትነታችን አሳጥተውናል ።

የህወሐት መሪዎች በኤርትራ ይወስዱት ለነበሩ አቋም ይቃወሙ ለነበሩ ታጋዮች ጸረ አመራር ተብለው ቡዙ ጉዳት አድርሰዋል ። የህወሐት አማራርም ከወለደአብ ወለደማርያም እሚያመሳስላቸው በወቅቱ ጸረ የደርግ ስርአት ይታገል ከነበረው ኢህአፓ ቡዙ የህወሐት ታጋይ ከኢህአፓ ጋር አብረን እንታገል ብሎ ጥያቄ ሲያነሳ ከአማራ ፓርቲ አብረን አንታገልም ፣እንዳው እኛ ኢትዮጱያውያን አይደለንም ለሀገራዊ ነጻነት ነው የምንታገለው ብለው የመገንጠል ጥያቄ ያነሱት ።

ተስፋጽዮንና የሱ አጃቢ የሆኑ አግአዝያንም አጠናክረው ጽንፈኛ በሆነ አገላለጽ እየነገሩን ያሉ የወልደአብ ወልደማርያምና የህወሐት አማራር የነበረ አቋምና እስትራተጁ ነው ።

በህወሐት አመራር ውስጥ ከጥንት ጀምረው ከኢትዮጱያ ፓርቲዏች ከማበር ይልቅ ከኤርትራ ፓርቲዏች ጋር አንድነት ፈጥረን ጠንካራ ትግራይ ትግርኚ ጠንካራ መንግስት መመስረት አለብን ፣የወልደአብ ወልደማርያም አቋም ትክክል ነው የሚሉና የሚሰብኩ ግለሰዏች ነበሩ ። አሁንም የትግራይ ትግርኝ ትግርኛ ተናጋሪዏች ክርስቲያኖች የበላይነት የሚሰብክ ተስፋጽዮን ኢርትራዊ አዲስ አበባ እየተመላለሰ ለስብሐት ነጋና ከሌሎች እንደሚገናኝ በዩቲብ እያሳራጨ ይገኛል ።በመሆኑም እነዚህ ፍጡራን በሽታው አለተዋቸውም ማለት ነው ያሰኛል ።

የተከበራችሁ ኢትዮጱያውያን እነ ተስፋጽዮን ኤርትራዊና በትግራይ የሚገኙ ጥቂት ሙሁራኖች ፣በተጨማሪ ያረጁ ያፈጁ አዛውንቶች ወደ ኃላ አንድ ትውልድ ተመልሰው ቢሀር ከቢሄር የሚገነጣጥል ፣ የሚያጋጭ ፣ ከክርስትና አማኒያን ካልሆነ ሌሎች የሙስሊም አማኒያን ከመሬት ገጽ የሚያጠፋ ኢትዮጱያዊነታቸው የካዱ ፣ ከትግርኛ ተናጋሪ ክርስትያን ውጭ እንደ ብሄረ አማራ ሌሎችም የሚያገልና በጠላትነት የሚፈርጅ ፣ አመለካከትና ስትራተጂ ሊያነግሱ ለሚፈልጉ እነማን ብለን ብንጠራቸው ይሻላል?
ስለ እነዚህ በታኞችና ጽንፈኞችና ጸረ ህዝቦች አሰያየም በሚመለከት የኢትዮጱያ ህዝብ ስም ይስጣቸው ። በበኩሌም አሁን ካሉት መጥፎ አለም አቀፍ ወንጀሎኞች ጋር ጎን አሰልፌ ስም እንዳልሰጣቸው የባሱ የተበላሹና የወረዱ በመሆናቸው ለነሱ የሚገልጽ ስም አጥንቸ ለወደፊት ለአንባብያን ግልጽ አደርጋለሁ ።

በመጨረሻ ግን ለሙሁራን እማሳስበው የተስፋጽዬን ኤርትራዊ አስተሳሰበና የወረደ ስትራተጂ ተከትላችሁ ለትግራይ ወጣት እያዳናገራችሁ ያለችዩ የመቀሌ ዩንቨርስቲ ማህበረሰብ ሽፋን ተከትላችሁ የምታዳናግሩ በተጨማሪም በተለያዬ የስራ መስክና በገዥዏች ስር ተወሽቃችሁ አገር በሀይማኖት በዘር የምትከፋፍሉ ሀገራዊ ሞራል የሌላችሁ ከእርኩስ ተግባራቹ ብትቆጠቡ የተሻለ ይሆናል ።

ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ ፣  02.05. 2009 ዓ ም ፣ ይቀጥላል

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *