1. ፕሬዚዳንት ኦባማ ዩኒቨርሲቲ ከመግባታቸው በፊት ጓደኞቻቸው “ቤሪ” እያሉ እያቆላመጡ ነበር የሚጠሯቸው። በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ግን በሙሉ ስማቸው “ባራክ” እየተባሉ እንዲጠሩ ይፈልጉ ነበር ተብሏል። አያታቸው ደግመፐ “ባር” እያሉ ነው የሚጠሯቸው።

2. “ባራክ” በስዋህሊ ቋንቋ “የተባረከ” ማለት ነው።

3. በግራ እጃቸው ነው የሚበሉት፤ የሚፅፉትም። ግራኛ ሰዎች በቀኝ የአዕምሯቸው ክፍል ነው የሚያስቡት፤ በዚህም አስተሳሰባቸው የበሰለ ነው ይባላል። ባራክ ኦባማስ ግራኛ ስለሆኑ ይሆን ልዕለ ሀያሏን ሀገር በብቃት የመሩት?

4. ባራክ ኦባማ እና ባለቤታቸው ሚሼል ኦባማ ባለፈው የፈረንጆቹ አመት 2016 ከ4 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ አግኝተዋል። የገቢያቸው ምንጭም “Dreams from My Father” የሚል ርዕስ ያለው የኦባማ መፅሀፍ ሽያጭ ነው።

5. ኦባማ ሚሼልን በመጀመሪያ የፍቅር ቀጠሮ የጋበዟት የስፓይክ ሊን “Do the Right Thing” ፊልም ነው።

6. “Casablanca” እና “One Flew Over the Cuckoo’s Nest” የኦባማ ተመራጭ ፊልሞች ናቸው።

7. አፍሪካዊ ደም ያላቸው ኦባማ የሃሪ ፖተርን ሁሉንም መፅሃፍት አንብበዋል።

8. የዓለም የቦክስ ሻምፒዮናውና ባለፈው አመት 2016 b74 አመቱ ከዚህ አለም በሞት የተለየው መሀመድ አሊ ፊርማ ያረፈባቸው በርካታ ቀይ ጓንቶችም አሏቸው።

9. ሲ ኤን ኤን እና የተለያዩ የስፖርት ቻናሎችን መመልከት የሚወዱት ኦባማ የቅርጫት ኳስ አድናቂ ናቸው።

10. የኦባማ ምርጥ መፅሃፍ ሞቢ ዲክ የፃፈው Herman Melville ነው።

11. ከእንግሊዝኛ በተጨማሪ ስፓኒሽኛ አቀላጥፈው መናገር ይችላሉ።

12. የምግብ ምርጫቸው ሚሼል የምትስራላቸው ከቅቤ፣ አይብ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ፐርስሊ፣ ወይን እና ሌሎች ግብአቶች የሚዘጋጅ ሽሪምፕ ሊንጉይ የተሰኘ ምግብ ነው።
በመቅሰስ ስአት ደግሞ የለውዝ ቼኮሌት መመገብ ይወዳሉ።

ኦባማ ጥቁር ሻይም የሚወዱ ሲሆን፥ ቡናም ይጠጣሉ። አልኮል ግን ብዙም አይደፍሩም ተብሏል።

13. ኦባማ ፖለቲከኛ ባይሆኑ ኖሮ የስነ ህንፃ ባለሙያ የመሆን ፍላጎት ነበራቸው።

14. የቃላት ድርደራ ጨዋታ እና ካርታ መጫወት ይወዳሉ።

15. ሱሪያቸውን ዝቅ አድርገው የሚሄዱ ወንዶችን እንደሚጠሉም ገልፀው ነበር።

16. ማክ ላፕቶፕ ይጠቀማሉ፤ ፎርድ ይነዳሉ።

17. 1 ሺህ 500 የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ የሃርት ስቻፍነር ከረቫት ያደርጋሉ።

18. 11 ጥንድ ጥቁር ቆዳ ጫማዎች አሏቸው፤ እነዚህኑ ጫማዎችንም ነው ደጋግመው የሚጫሟቸው።

19. በጣም የሚያደንቁት አርቲስት የአለማችን ታዋቂውን ስፔናዊ ሰአሊ ፓውሎ ፒካሶ ነው።

20. ባራክ ኦባማ በቺካጎ በሚገኝ ፀጉር ቤት በሳምንተ አንድ ጊዜ ፀጉራቸውን ይስተካከላሉ። ፀጉራቸውን የሚያስተካክላቸውም ዛሪፍ የሚሰኝ ሲሆን፥ ለአንድ ጊዜ መስተንግዶ 21 ዶላር ይከፍላሉ።

ባራክ ኦባማ ከዋይት ሀውስ ሲወጡ ከ7 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ በሚያወጣ ቤት በወር 22 ሺህ ዶላር ኪራይ እየከፈሉ መኖር ይጀምራሉ።

FBC – source

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *