በ2008 ዓ.ም በተነደፈው የአዲስ አበባ መሪ ፕላን ላይ መግባባት ለመፍጠርና ለትግበራው አመቺ ሁኔታ ለማመቻቸት ከሁሉም ወረዳዎች ከተውጣጡ 300ሺህ በላይ ነዋሪዎች ውይይት እንደሚደረግ መገለጹን አዲስ ዘመን ጋዜጣ አስነብቧል፡፡፡፡

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሪ ፕላን ፕሮጀክት ፅሕፈት ቤት በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በሰጠው መረጃ  ገለጸ እንደተባለው  አዲስ አበባ በአሁኑ ወቅት እንደሌሎች የዓለማችን ከተሞች ውብና ደማቅ  ለማድረግ አዲስ መሪ ፕላን ተዘጋ ጅቶላታል፡፡ በመሪ ፕላኑ ላይ በርካታ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን፤ ህዝቡ በተደጋጋሚ ጊዜ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል እንደሚሆን ተስፋ ተጥሎበታል ተብሏል፡፡

መሪ ፕላኑን በተመለከተ እስከአሁን ድረስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የመከሩበት ስብሰባ ተካሂዷል፡፡ በመቀጠልም የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች በጉዳዩ ላይ የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡ በቅርቡም ከነዋሪዎች ጋር ውይይት እንደሚደረግ ጠቁሟል፡፡

መሪ ፕላኑ፤ ነዋሪዎች በተደጋጋሚ የሚያነሷውን የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣አረንጓዴ ቦታዎች፣ የመኖሪ ቤቶች፣  የከተማ ብክለት ማስጠበቂያዎች፣ የከተማ ኢኮኖሚ ልማት እና አያሌ ጉዳዮችን ለመመለስ ያግዛል፡፡ በከተማዋ ውስጥ ያሉትን ወንዞችም ከብክለት በማፅዳት የመዝናኛ ስፍራ ይደረጋሉ፡፡  አለፍ ሲል በጀልባ ለመንሸራሸር የሚያስችሉ ሥራዎች በከተማዋ ወንዞች ላይ  ይተገበራሉም ተብሏል፡፡

እንደ ፅሕፈት ቤቱ መረጃ ከሆነ፤ በዚህ መሪ ፕላን መሠረት አዲስ አበባ  የሚገነቡ  በርካታ ትልልቅ ሕንፃዎች  የሚካተቱ ሲሆን፤ ለመኖሪያ፣ ለንገድና ሌሎች ቅይጥ አገልግሎት እንዲውሉ የሚያስገድድ መመሪያም ተግባራዊ ይሆናል፡፡

በመሪ ፕላኑ መሠረት፤ በአሁኑ ወቅት ለእግረኛ መተላለፊያ ምቹ ባልሆነው የአዲስ አበባ ቀላል የባቡር መስመር እና ቀለበት መንገዶችን በቅርብ ርቀት ለማቋረጥ የሚያስችል ድልድይ ከባቡር መስመሩ በላይ ይገነባል፡፡  በቀለበት መንገዶችም ሆነ በቀላል የባቡር መስመሩ ላይ  እንደ አስፈላጊነቱ በአየር ላይና በመሬት ውስጥ ለማቋረጥ የሚያስችሉ መተላለፊያዎችም ይገነባሉ ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባን ሁኔታ የሚከታተሉ እንዳሉት ከተማዋ ያሉዋት ወንዞች ደርቀዋል። ከመጸዳጃ ቤት የሚወጣ ፍሳሽ መድፊያ ሲሆኑ የተቀሩትም የተበከሉ ናቸው። እናም እቅዱ ጽድቁ ቀርቶልኝ በወጉ እንዲሉ ነው ።

እትዮጵያን ነውስ ፖርታል እንደዘገበው  ፎቶ ዛጎል

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *