“Our true nationality is mankind.”H.G.

ለፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ-ክፍል 2

ከፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ (ክፍል ሁለት)

“…..በዚህ አጋጣሚ ልገልጽልዎ የምፈቅደው እኔ የሂስን አዋጅ የተከተለ ገንቢ አቃቂርንና ትችትን በደስታ እንደምቀበል ነው፡፡ አንድ መጽሃፍ ሂስ እንዴት እንደሚደረግ በሩስያ፣ በጀርመን እና በ ዩ ኤስ ኤ ለበርካታ ዐመታት ተምሬአለሁ፤ አስተምሬአለሁም፡፡ የርስዎን ያልተቀበልኩት ግን ሂስም ትችትም ያልሆነ ቁንጽልና አፍራሽ ስላቅ በመሆኑ ነው፡፡ አንድ ሀቀኛ ሃያሲ የአንድን መጽሀፍ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ያቀርባል እንጂ ደካማ ብቻ የመሰለውን (ደሞ ለሱ ደካማ የሚመስለው ደካማም ላይሆን ይችላል፣) ነቅሶና ቆንጽሎ እያወጣ አይደረድርም……”

ውድ ፕሮፌስር ጌታቸው ኃይሌ፡ “ለውድ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ፣ የውውይቱ መንስኤ” በእሚል ርእስ ባለፈው ሳምንት ያቀረቡአቸውን  የትዕቢት ናዳዎችን፣ የብስጭት ውርጅብኞችንና የመከላከያ እሩምታዎችን ንቄ ትቼ፣ በእርስዎ ደረጃ ዝቅ ላለማለት ስል ከነሱ ውስጥ መልስ መስጠት ያለብኝን ብቻ በመጀመሪያ እሰጥና ወደ ቀድሞ ጥያቄዎቾ እመለሳለሁ፡፡ መልሶቼ ሁሉ ተደምረው የሌሎቹንም ግለሰቦች ሁሉ ጥያቄዎች ይመልሳሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በጥንቃቄና በቀና ልብ ያነበቡት ሰዎች ሁሉ መጽሀፉ ራሱ ጥያቄዎቻቸውን መልሶላቸዋል፡፡  መሪራስ አማን በላይ የግዕዝና ሱባ መዝገበ ቃላትን ቅጂ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲት የኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር ተቁዋም መስጠታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት አሰፍርና በሸር ተልእኮአችሁ አንድነት ምክንያት የሱ ሸር ደስ ስለአሰኞት አንድ ቴዎድሮስ ጸጋዬ ሰለተባለ ወደ እኔ ስለተላክ ጋዜጠኛ-ነኝ-ባይም ጥቂት እላለሁ፡፡ በተጨማሪም ከኔ የረጅም ዘመን ታሪክ ይልቅ የኢትዮጵያን ታሪክ የመቶ ዐመት ነው የሚሉትን ተገንጣይዎችና አስገንጣይዎች ታሪክ ስለ መምረጥዎ እና ‹‹የጠነዛ ገለጻ‹‹ ስለሚለው  ሀረግ ትንሽ መግለጫ እሰጣለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ አፈታሪክ ስለተከሰተበት አንድ ወቅት ትልቁ ባለታሪክ ክቡር ተክለጻድቅ መኩሪያ የጻፉትን እጠቅሳለሁ፡፡ ውድ አንባቢ ሆይ! መሪራስ አማን በላይ ባለ 441 ገጾች የሱባ እና የግዕዝ መዝገበቃላት ለህትመት አዘጋጅተው፣ አንድ ቅጂ ለ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቁዋም፣ ሰኔ 17 ቀን 2001 ዐመተ ምሕረት ማበርከታቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት እታች ሰፍሮአል፡፡ ሰርቲፊኬቱ ፎቶግራፍ ስለተነሳ በጉልህ አይታይም፡፡ ይህን አስደናቂ፣ ባለም ላይ ብቸኛ የሆነውን መዝገበ ቃላት መሪራስ አማን በላይ ያገኙት ከኑብያ፣ ሱዳን ነበር፡፡ ወሪጅናሌው በድሮ ዘመን የተጻፈው ብራና ላይ ነው፡፡  የጠፋውን ቁዋንቁዋችንን ያተረፈልንን ይህን መዝገበቃላት ለህትመት እንዲመች መሪራስ አማን በላይ አዘጋጅተው ነበር ለዩኒቨርሲቲው የዳረጉት፡፡ ፕሮፌሰር ጌታቸው ግን መጽሃፉን በዐይናቸው ሳያዩና በጃቸው ሳይዳስሱ፣ እንዲሁም ሳይመረምሩ  የሱባውን ፊደላትና ቁዋንቁዋውን አማን በላይ ራሱ የፈለስፈው ነው፣ ብለው ሰውዬውን ዋሾ ለማድረግና ከኑብያ የተገኘ ምንም መጽሃፍ የለውም ለማለት አውቀው ድርቅ ይላሉ፡፡ እሰቲ እግዚአብሄር ያሳያችሁ የአምላክ አእምሮ ካልሆነ በቀር የሰው ልጅ አእምሮ አንድ ጥንታዊ ከ 3000 ዐመት  በፊት የነበረንና የጠፋን ቁዋንቁዋ መዝገበቃላቱን ከነፊደሉ በ 441 ገጾች ይፈጥራል? የሱባው እንኩዋን ቀርቶ የግዕዙንስ ብቻ ቢሆን ለመሆኑ ሙሉ መዝገበቃለት ከሱባ ጋር እንዲስማማ አድርገው ከአእምሮአቸው አንቅተው መጻፍ የሚችሉት ምን አይነት ላእለሰብአ(superman) ቢሆኑ ነው?  አንባብያን ራሳችሁ ፍረዱ፡፡ ሃቁ ግን ይሀን ጥንታዊ የሱባ እና የግዕዝ መዝገበቃላት መሪራስ አማን ከሌሎች ብርቅዬ የብራና ጥቅሎች ጋር ያገኙት፣ በጀበል ኑባ፣ ኑብያ (ሱዳን) ነበር፡፡  ጥንታዊ ጽሁፎችን ከኑብያ ስለማግኘታቸው ይህ መዝገበቃላት ተጨማሪ መረጃ ነው፡፡  ለክፉም ለደጉም የምስክር ወረቀቱ እነሆ፡፡- ውድ ፕሮፌሰር ጌታቸው፣ ወደ ሁለተኛው ነጥቤ ልግባና፣ ያ ቴዎድሮስ ጸጋዬ የተባለ ሰው መልካም ጋዜጠኛ መስሎ ለሰላማዊ ውይይት ብሎ ወደ ቴሌቪዥን ስቱዲዎው ጋበዘኝ፡፡ እኔም ምንም የጎንዮሽ ተልእኮ የሌለው ሀቀኛ ጋዝጠኛ መስሎኝ ግብዣውን ተቀበልኩ፡፡ ለካስ እሱ ተልእኮው ሌላ ኖሮእል፡፡ ጥያቄ በጥያቄ ላይ እንደማዕበል እየደራረበብኝ ለመመለስ ስሞክር መልሴን ፈርቶ እያፈነኝ በውይይት ፈንታ አተሃራ ገጥሞኝ ከጋዜጠኛ ስነምግባር ውጪ ሞገተኝ፡፡ እኔን እዛ ጋብዞ ራሱ ብቻ እየተናገረ ሊያስቆጣኝ ሲሞክር እኔም ኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት ቁጣዬን እንዳላሳይ ተጠንቅቄ በተዕግስት አሳልፌ መተንፈሻ ባገኘሁ ቁጥር የምችለውን ያህል አስረድቼ ፕሮግራሙ አለቀ፡፡ በመጨረሻ ከስቱዲዮው ስሰናበት የኔን የተሻሉ ግጥሞችና ሌሎችም ሥራዎች ማወቅ አለማወቁን ጠየቅኩት፡፡ አዎን አውቃለሁ፤ አለኝ፡፡ ታዲያ ለምን እነሱንም ጠቅሰህ በቀና ኣላስተናገድከኝም አልኩት፡፡ አንተ ብዙ ተከታይዎች ስለአለህ እና ከዚህም በላይ ለመጻፍ እንደሚገባህ ለመጠቆም እና ተከታይዎችህ ያንተን መንገድ እንዳይከተሉ ነው፤ ሲል መለሰልኝ፡፡ ያለው አልተዋጠልኝም ነበር፡፡ የእሱን የእኩይ ተልእኮ የታዘቡት ኢትዮጵያውያን ህልቆመሳፍርት ተመልካቾች የጋዜጠኛ ግብረገብነት የሌለው ጋጠወጥ፣ እንግዳ ጋበዞ እንደማወያየት የሚነታረክ ስድ፣ ሰው ለቃለ-መጠይቅ ጠርቶ ከራሱ ጋር የሚያወራ እብሪተኛ፣ እያሉ በራሱ ፌስቡክ ወረዱበት፡፡ ኢትዮጵያም ስደውል በርካታ ሰዎች እንደተናደዱበት ተረዳሁ፡፡ ሁሉም የሚሉት ተልእኮ ይዞ ቀርቦ፣ አንተን ለማጋለጥ አቅዶ ራሱን አጋልጦ እና እሱ ራሱን አሳንሶ አንተን አገዘፈህ፣ ነው፡፡ ስለዚህ ፍቅሬን አሳነሰው፣ ብለው እርስዎ ደስ ሰለአሎት ነገሩ የተገላቢጦሽ መሆኑን ይረዱት፡፡ እኔ ከእርስዎ በሃሳብ ስላልተስማማሁ ብቻ እሱን መደገፎ በእኩይ አላማችሁ አንድ ዐይነት ሰዎች እንደሆናችሁ አርስዎ በተግባሮ አረጋግጠዋል፡፡ ሸርአችሁ እና መሰሪአዊ  የአእምሮ አካሄዳችሁ አንድ ዐይነት ስለሆነብኝ ምናልባት እርስዎ የላኩትም ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ፡፡ ህሊና ያለዎት ትልቅ ሰው ቢሆኑ ኖሮ  የኢትዮጵያን ሀዝብ አንድነትና ፍቅር በሚያንጸባርቅ ሀቀኛ መጽሀፍ ላይ ከሚያላግጥ የሸር መልእክተኛ ጋር አይሰለፉም ነበር፡፡ አሁን ግን ኢምንትነትዎን አስመስክረዋል፡፡ አሞሌ ጨው በዝናብ ሲማሙዋ ጂል ይስቃል፤ ብልህ ያለቅሳል፤ እንደተባለው ነው፡፡ ካንተ የ4000 ዐመት ታሪክ የእነዛ የኢትዮጵያ ታሪክ 100 ዐመት ብቻ ነው፣ የሚሉቱ ይሻለኛል፣ አልነበር የአሉት?  ይህ አባባልዎ እጅግ አስደማሚ ነው፡፡ ለእኩይ የፖለቲካ ግባቸው ብለው ታላቁንና ረጅሙን እንዲሁም ገናናውን እና አኩሪውን የኢትዮጵያን ታሪክ ከአሳነሱት እና ከአዋረዱት ተገንጣይና አስገንጣይ ኃይሎች ጋር ለመሰለፍ መምረጥዎ የርስዎን ኢትዮጵያዊነት ከዚህ ቀደም ላልጠረጠሩት ለሃቀኞቹ ኢትዮጵያወያን ዱብ እዳ ቢሆንም፣ ተደብቆ ይኖር የነበረውን እውነተኛ ማንነትዎን ዛሬ ይፋ ስለአወጡት፣ እውነትና ንጋት አያደር ይጠራል የተባለውን ሀቅ አስመስክረዋል፡፡ ሌላ እርስዎ ደጋግመው ያነሱትና ያብከነክኖት፣ አንዳንድ ኢትዮጲስት ነን የሚሉ ፈረንጆች ስለኢትዮጵያ ታሪክ የሰነዘሩትን የተሳሳተ አስተያየት ‹‹የጠነዛ‹‹ ማለቴ ነው፡፡ ይህንንም ስል በአእምሮዬ ውስጥ የነበረው  ኦሮሞዎች ለኢትዮጵያ ቁስ-አካል ስልጣኔ ያበረከቱት ምንም ፋይዳ የለም ብሎ ኦሮሞዎችን የተሳደበውን እንግሊዛዊው ኢ ኡልንዶርፍንና ስለኢትዮጵያ ያልጠለቀ ግንዛቤ የነበራቸውን፣ በስለላ የሚጠረጠሩትን አንዳንዶቹን ነበር፡፡ ርስዎ፣ ኡሉንዶርፍ ይሀን አቁዋሙን በሁዋላ ስላሻሻለ እንዲወቀስ አይገባም ባይ ነዎት፡፡ ሆኖም ሁዋላ በሰዎች ጫና ሃሳቡን ቢለውጥም መጀመሪያ የተፋውን ስድብ አያስረሳለትም፡፡ ከዛ በተረፈ ነቀፌታው ለስለላ ተግባር ኢትዮጵያን ከሚያጠኑቱ ውጪ፣ ሀገራችንን በቅንነት ሲመረምሩ  እድሜያቸውን ያሳለፉትን እነ ፕሮፌሰር ሰምነርን፣ የረጅም ዘመን ወዳጄን ሪቻርድ ፓንክረስትን፣ የሳቸውን ልጅ አሉላን፣ ሃሮልድ ማርከስን፣ ቱቢያናን፣ ላንፍራንኮ ሪቺን፣ ዋሊስ በጅን እና የመሳሰሉትን እይነካም፡፡ ይሀ በዚህ አጋጣሚ ግልጽ ይሁን፡፡ ደግሞም በዛ አባባሌ እኔ ለማለት የፈለኩት እኛ ኢትዮጵያውያን፣ ታሪካችንን ሁሌ ፈረንጆች እንዲያስተምሩን ከማድረግ ይልቅ የራሳችንን ምሁራን ኮትኩተን አሳድገን እነሱን መስማት ይገባናል ነው፡፡ ስለ አፈታሪክና ጽሁፈ-ታሪክ ትንሽ ለመናገር ፍቃዴ ነው፡፡ እነዚህን ሁለት የታሪክ ዐይነቶች የሚያዛምዳቸው አንድና አንደ ነገር አለ፡፡ ታሪክ ይባላል፡፡ ሁለቱም ታሪክ ናቸው፡፡ በጅምላዊ አባባል  ልነታቸው አንዱ የቃል፣ ሁለተኛው የጽሁፍ መሆኑ ነው፡፡ ጥንት በጽሁፍ ሰፍሮ የነበረው የኢትዮጵያ ታሪክ፣  በተለምዶ ዮዲት ጉዲት የምትባለዋ ፈላሻዋ አስቴር እኤአ በ878 ዐመተ ምሕረት አካባቢ የአክሱምን መንግሥት ከአፈረሰችበት ጊዜ ጀምሮ እሰከ አጼ አምደጽዮን ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ (እኢአ 1299) ማለትም ለ 421  ዐመታት ያህል ዳብዛው ጠፍቶ በቃል ወይም በአፈታሪክ ብቻ ይነገር ነበር፡፡ ታላቁን ንጉሠነገሥት አምደጽዮንን ይሀ ነገር አስግቶት፣ እንደ ክቡር ተክለጻድቅ መኩሪያ ትረካ፣ በድፍን ኢትዮጵያ የነበሩትን የኢትዮጵያን ታሪክ በ ቃል የሚያውቁትን ሊቃውንት አሰባስቦ አፈታሪኩን በመጽሃፍ አጽፎ፣ ጠፍቶ የነበረው ታሪካችን እነሆ፣ ብሎ ለኢትዮጵያ ህዝብ ታሪኩን እና ክብሩን መልሶለታል፡፡ ተክለጻዲቅ መኩሪያ እንደሚሉት የጥንቱ መጻህፍት የጠፉት በ ዮዲት ተቃጥለው ነበር፡፡ ስለዚህ አጼ አምደጽዮን እንደገና አጻፉአቸው፡፡ — “ስለዚህ ከዮዲት ወዲህ እስከ አጼ አምደጽዮን ድረስ ታሪክ የሚጠቀሰውና የሚተረከው “ከአዋቂዎች ቃል በቃል በወረደው ብቻ ነበር፡፡ ይህ ብልህ ንጉሥ እዙፋን ከወጣ ወዲህ ይህ “ቃል በቃል የሚነገረው ታሪክ በቶሎ ከብራና ላይ ሰፍሮ ለልጅ ልጅ እንዲተላለፍ ካልሆነ “ወደ ፊት ሊጠፋ እነደሚችል ተገነዘበ ማለት ነው፡፡ …… ስለዚህ ያለፈ ታሪክ የሚያውቁትን “ሊቃውንቱን ሰብስቦ ታሪክ እንዲጻፍ አዘዘ ይባላል፡፡”  (ተክለጻድቅ መኩሪያ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ ከዐጼ ይኩኖ አምላክ ስስከ ዐጼ ልብነ ድንግል፣ ገጽ 40) የተክለጻድቅ መኩሪያ ትረካ እንደሚለን ስለዛ ዘመን የሚያወጋው አሁን በመጽሀፍ ማህደር ውስጥ የተቆለፈው ለ 421 ዐመታት በቃል ሲነገር የነበረው ታሪካችን መሆኑ ነው፡፡ ይህ የሚያረጋግጠው፣ ታሪክ በቃልም ቢሆን ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ አፈታሪክን አቅልላችሁ የተሳለቃችሁት እርሶ ፕሮፌሰር ጌታቸውና መሰሎቾ እጅግ ተሳሰታችሁአል ማለት ነው፡፡ አፈታሪክ የታሪክ አንዱ ገጥታው ነውና፡፡ ከዚህ ቀጥሎ፣ ባለፈው ጊዜ ክፍል ሁለት ብዬ አቀርባለሁ ያልኩትን አቅርቤ ርስዎ ያነሱአቸውን በክፍል አንድ ላይ ያላካተትኩአቸውን ነጥቦች አሰፍራለሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ልገልጽልዎ የምፈቅደው እኔ የሂስን አዋጅ የተከተለ ገንቢ አቃቂርንና ትችትን በደስታ እንደምቀበል ነው፡፡ አንድ መጽሃፍ ሂስ እንዴት እንደሚደረግ በሩስያ፣ በጀርመን እና በ ዩ ኤስ ኤ ለበርካታ ዐመታት ተምሬአለሁ፤ አስተምሬአለሁም፡፡ የርስዎን ያልተቀበልኩት ግን ሂስም ትችትም ያልሆነ ቁንጽልና አፍራሽ ስላቅ በመሆኑ ነው፡፡ አንድ ሀቀኛ ሃያሲ የአንድን መጽሀፍ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ያቀርባል እንጂ ደካማ ብቻ የመሰለውን (ደሞ ለሱ ደካማ የሚመስለው ደካማም ላይሆን ይችላል፣) ነቅሶና ቆንጽሎ እያወጣ አይደረድርም፡፡ ስለቅድጅቱ ምንም ሳይል ጉድለት የመሰለውን ብቻ ከደረደረ አላማው ሂስ ማካሄድ ሳይሆን እንከን ቁፈራ ብቻ ይሆናል፡፡ ይህ የኔ የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛወ የዘር ምንጭ የተሰኘው መጽሀፌ በሂደት ላይ የአለ ነው እንጂ አንድ ቦታ የቆመ አይደለም፡፡ ገንቢ አስተያየቶች ከአንባቢ ሳገኝ እያሻሻልኩት የሚጉዋዝ ነው፡፡ ለምሳሌ ርስዎ ያነበቡት ቅጂ ውስጥ ያልነበረ በቅርቡ በታተመው ቅጂ ላይ የህዝብ አስተያየት አስጭሮት እንደገና አጠናቅሬ ያወጣሁት መረጃ አለ፡፡ ስለዚህ በአንባቢ ገንቢ አስተያየት መጽሃፉ ከጊዜ ወደጊዜ እየተሻሻለ ይሄዳል፡፡ ይህን ለርስዎ ምላሽ ያዘጋጀሁትን ጽሁፍ ባለፈው ሳምንት ላቀርበው ስል የርስዎ ክፍል ሁለት ቀድሞ ወጣ፡፡ የርስዎ ቀድሞ እንዲነበብና አንባቢውም ንባብ እንዳይደራረብበት አስቤ የኔን እንዲያዝ አደረግኩት፡፡ የርስዎን ጥያቄዎች በከፍል ሁለት እንደማስተናግድ በክፍል አንድ መጨረሻ በግልጽ ባስቀምጥም ይህን ልብ ያላሉና የቸኮሉ አንዳንድ አንባብያን ጥያቄዎቹን አላስተናገደም አሉኝ፡፡ እነሆ ከዚህ በታች ተስተናግደዋል፡፡ ቅደም ተከተላቸውን እንደተመቸኝ ነው ያደረግኩት፡፡ በቢጫ የቀለሙት እርስዎ የተቹዋቸው ናቸው፡፡ ጥቁሮቹ የኔ መልሶች ናቸው፡፡ ግን ከአማን በላይ መጻሕፍት አንዳቸውም እንደታሪክ ምንጭነት ለግምገማ ከሚያበቃ ደረጃ ላይ ያልደረሱ፥ አልፎ አልፎ በእውነት ታሪክ የተቀመሙ ልብ ወለድ ታሪኮች ናቸው።” ፕሮፌሰር ጌታቸው ሆይ! እርስዎ፣ እንዳው በጅምላው ልብወለድ፣ ልብወለድ ይላሉ እንጂ፣ ልብወለድ ምን እንደሆነ እና ከታሪክ በምን እንደሚለይ  እንኩዋን ከቶም አላብራሩም፡፡ በምሁራዊ ትነተና ህግ መሰረት አንደ ሰው ስለ አንድ ዐእምሮአዊ ሥራ ከመተንተኑ በፊት የሚተነትንበትን መንገድ (ስልት) እና ቃላት ምንነት በግልጽ ማስቀመጥ አለበት፡፡ የኔን እና የመሪራስን ሥራዎች እንዳው በደምሳሳው መሀይሞች እንደሚያደርጉት ሁሉ፣ እርስዎ ልብወለድ ብለው ፈረጁ እንጂ፡ ልብወለድ ማለት ምን እንደሆነ የተለያዩ የሥነጥበብ ጠበብት የተናገሩትን ገልጸው የኛ ሥራዎች እንዴት ልብወለዶች እንደሆኑ አላረጋገጡም፡፡  ስለዚህ ትችቶ ከመሀይማዊነት ተላቆ ምሁራዊ ይሆን ዘንድ እርስዎ ልብወለድ የሚሉትን ቃል ገልጽው ተንትነው፣ ልብወለድ ናቸው ያሉአቸውን የኔን እና የመሪራስ አማን በላይን መጻህፍት ጠቅሰው ገጽ በገጽ እያመሳከሩ ልብወ;ለድ መሆናቸውን ማስረጃ በማቅረብ ለአንባቢው ያረጋግጡ፡፡ ታዲያ ይህን ሲያደርጉ፣ መሪራሰ የጻፉአቸው እርስዎ ልብወለድ የሚሉአቸው፣ መሪራስ፣ እኔ እና አስተዋይ አንባቢዎች ግን ጠፍተው የተገኙ እውነተኛ ታሪካችን የምንላቸው መጻህፍት ቁጥር ወደ ስምንት እንደሚደርሱ እንዳይዘነጉ፡፡ በኔ ግምት መሪራስ አማን በላይና ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ብሔራዊ ሚቶሎጂ ደርሰዋል፡፡ ሚቶሎጂ፣ ያውም ብሄራዊ ሚቶሎጂ መድረስ ቀላል መስሎዎታል፡፡ ታሪክን ከመጻፍ ይልቅ ሚቶሎጀን ለመድረስ እጅግ ከባድ እንደሆነ አያውቁምን? እኔንና መሪራስ አማን በላይን ርስዎ ለዚህ ትልቅ ክብር ካበቁን እልል! ነው፡፡ እሰየው! ነው፡፡ እውነት እኛ  ብሔራዊ ሚቶሎጂ ከደረስን የኢትዮጰያ ህዘብ ታላላቅ ሀውልቶች ያቆምንልን ይሆናላ! ዐለም የጋራ ማንነቱን፣ የወል ምንጩን እና አንድነቱን ደርሶ ካበቃ ከ 3000 እና 4000 መታት በሁዋላ እኛ የአእምሮ ፈንጠዝያችን እንዲህ ረቅቆ እና መጥቆ በ21ኛው ክፍለዘመን ኢትዮጰያውያንን አንድ የሚያደርግ የጋራ ታሪክ እና ማንነት፣ በተጨማሪም ፍቅረ-ዝናብንና ሰላምን የሚያወርድ ሚቶሎጂ ወይም አፈታሪክ መጻፍ ከቻልን እጹብ፣ ድንቅ ነዋ! የእኛም የታላቅነት ደረጃ ከጥንቶቹ ሚቶሎጂ ፈጣሪዎች ከእነ ሆመር፣ ከእነ ፖልመሬኒያን እና ሌሎቹም ግዙፍ ሰዎች ጋር በ 21ኛወ ክፍለዘመን ሊመደብ ነዋ! እሰየው!!! እንደ አፍዎ ያድርግልና!!! ለማንኛውም ብሔራዊ ሚቶሎጂ ምን ማለት እንደሆነ በዝርዝር ገልጸው፣ የሚቶሎጂን ምንነት ያገኙበትን ምንጭ ጠቅሰው፣ የእኛ ጽሁፍ፣ ማለትም የመሪራስ ስምንት የታሪክ መጻህፍትና የኔ አንድ የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ እንዴት ሚቶሎጂ እንደሆኑ የመጻህፍቱን ስም እየጠቀሱ ገጽ በገጽ በቂ ማስረጃዎችን በመደርደር ለአንባብያን ያረጋግጡ፡፡ ከዚህም አያይዘው የግሪኩ፣ የህንዱ፣ የጣልያኑ፣ የእሰፔኑ፣ የፈረንሳዩ እና የጀርመኑ ሚቶሎጂ ከኛው እንዴት እንደሚለይና እንደሚመሳሰል ግልጥልጥ አድርገው አወዳድረውና አነጻጽረው አንባቢን ያሳምኑ፡፡ይህንንም ሲያደርጉ፣ ከመጽሃፉ ውስጥ ከእርስዎ አእምሮ በላይ የረቀቁትን አንዳንዶቹን አስደናቂ ክስቶቶች፣ ለምሳሌ ኦሮሞዎች፣ የጎጃም ዘረ-ደሸቶችና እነማይዎች አባታችን (ደሸት) እና ህይወት ከውሀ ውስጥ መነጩ ወይም ተገኙ የሚሉትን አንድ አረፍተ ነገር እና እኔም ከእዚሁ አነጋገራቸው ተነስቼ አባታቸው ውሀ ውስጥ ተጸንሶ ይሆናል፣ ያልኩትን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ነገሮችን ይዘርዝሩ… See more at:  fikre-tolossa-to-getachew-haile-2

0Shares
0