የሱዳንን መንግስት ለመጣል የአልሲሲ መንግስት ደቡብ ሱዳንን መጠቀም ይፈልጋል። የሱዳንና የግብፅ የቀደመ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲሻክር ካደረጉት ምክንያቶች መካከል አንዱ ተደርጎ የሚወሰደው ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ሱዳን ለኢትዮጵያ ድጋፏን መስጠቷ ነው። ሁለቱ ሀገራት ከዚህም በተጨማሪ የቆየ የግዛት ይገባኛል ውዝግብ ላይ ያሉ መሆናቸውም ሌላኛው የግንኙነታቸው መሻከር አንዱ ምክንያት ተደርጎ የሚጠቀስ ነው። በሰሜናዊ ሱዳን እና በደቡባዊ ግብፅ የምትገኘው ሀላይብ ግዛት የሁለቱ ሀገራት የውዝግብ መንስኤ ናት። 13 ሺህ ሰኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ያላት ይህች ግዛት ቀደም ሲል በሁለቱ ሀገራት በጋራ ስትተዳደር የቆየች ሲሆን ሆኖም እ.ኤ.አ ከ2000 ጀምሮ የሱዳን የፀጥታ ኃይሎች ለቀው ለመውጣት በመገደዳቸው ሙሉ ግዛቷን ግብፅ ማስተዳደርን እስከዛሬም ድረስ ቀጥላበታለች። ከዚህ በኋላም ሱዳን የግዛት ይገባኛል ጥያቄው በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲያልቅ ጥረት ስታደርግ ብትቆይም ግብፅ ፈቃደኝነትን ባለማሳየቷ ጥረቱ ሁሉ መክኖ ቀርቷል።

ሱዳን ቀደም ሲል ከሀላይብ ግዛት ይገባኛል ጥያቄ ጋር እንደዚሁም ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ሱዳን ለኢትዮጵያ ያሳየችው ድጋፍ ግብፅን ያስቀየማት መሆኑን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ፕሬዝዳንት አልሲሲ ቀደም ሲል የኤርትራውን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን፣ የጂቡቲውን ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ካይሮ ጠርተው ያነጋገሩ ሲሆን ባለፈው ማከስኞ ደግሞ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪየር ወደ ካይሮ አምርተዋል። የሳልቫኪየርን የካይሮ ጉብኝት አስመልክቶ ዘገባውን ያሰራጨው ሱዳን ትሪብዩን የአልሲሲ መንግስት የአልበሽርን መንግስት ለመጣል ደቡብ ሱዳን የአማፅያን ማሰልጠኛ ቦታን የሚፈልጉ መሆኑን አመልክቷል። የግብፅን የሳልቫኪየር ሚስጥራዊ ስምምነት የተቃወመው የደቡብ ሱዳን ነፃነት አርሚ ለደቡብ ሱዳን የዜና ወኪል በሰጠው ማብራሪያ የሁለቱን ሀገራት ሚስጥራዊ ስምምነት ተቃውሟል።   በግብፅ ደጋፊነት የሳልቫኪየር መንግስት መጠናከር የሀይል ሚዛኑን እንደሚያስቀይር የተረዳው ይህ ታጣቂ ሀይል ጠበቅ ያለ ተቃውሞውን አሰምቷል። “የአልሲሲና የሳልቫኪየር ግንኙነት ለግብፅ ብሔራዊ ጥቅም ነው።” ያለው ይህ ታጣቂ ሀይል ሪክ ማቻርን የመሳሰሉ ተቃማዊዎች ለማስወገድም ያለመ መሆኑን ጨምሮ አመልክቷል። አልሲሲ ከዚህ ቀደም ከኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ጋር በነበራቸው የሁለትዮሽ ቆይታ ኡጋንዳ ለሱዳን አማፅያን የስልጠና ካምፕ እንዲሰጡ ጥያቄ ያቀረቡ መሆኑን  ዘገባዎች ያመለክታሉ። በሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነትን ለማቀጣጠል በግብፅ የተመረጡት ሀይሎች የሰሜናዊ ሱዳን ህዝብ ነፃ ንቅናቄ (SPLM- North) እና የዳርፎር አማፅያን መሆናቸውን የሱዳን ትሪብዩን ዘገባ ያመለክታል።

Related stories   “ጣልያኖችም ሆኑ እንግሊዞች ቅኝ ግዛትን ለማስቀጠል ህዝቡን በዘር መከፋፈልን እንደ አንድ ስልት ይጠቀሙ ነበር” -አቶ ታቦር ገረሱ ዱኪ

ከሱዳን ባሻገር ግብፅ ሌላኛው ውዝግብ ውስጥ የገባችበት ጉዳይ የሳዑዲ ከአረቢያ ጋር ያላት ግንኙነት ነው። ከግብፅ አብዮት በኋላ ግብፅ ከገባችበት ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንድትወጣ ለማገዝ ሳዑዲ አረቢያ ሰፊ የፋይናንስ ድጋፍ ስታደርግ ቆይታለች።  ይሁንና የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች ውጥረት ውስጥ መግባት ግድ ብሎታል። የመጀመሪያው በቀይ ባህር አካባቢ ባሉ ደሴቶች የተነሳው የግዛት ይገባኛል ጥያቄ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሶርያ የእርስ በእርስ ጦርነት የአልሲሲ መንግሰት የያዘው አቋም ነው። በሶርያ የእርስ በእርስ ጦርነት በአሜሪካ በሚመራው ጎራ በኩል ሳዑዲ አረቢያ የሶርያ አማፅያንን የምትደግፍ ሲሆን ይሁንና ግብፅ በተባበሩት መንግስታት በሩስያ ለሚደገፈው የበሽር አላሳድ መንግስት ድጋፏን መስጠቷ የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ይፋ መውጣት መነሻ ሆኖ ተመልክቷል።  በዚያው ሰሞን የሳዑዲ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ በመገኘት ህዳሴውን ግድብ መጎብኘቱ በበርካታ ግብፃዊያን ባለስልጣናትና ሚዲያዎች ብዙ ጫጫታን ፈጥሮ ከርሟል። ሳዑዲ አረቢያም የኢትዮጵያን ህዳሴ ግድብ በገንዘብ ለመደገፍ አስባለች በማለትም የግብፅ ሚዲያዎች በሰፊው ሲያናፍሱ ከርመዋል።

Related stories   “የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች አለመምጣት የሚያጎለው አንዳችም ነገር የለም፤ እኛም አንጠብቃቸውም” ፕሮፌሰር በየነ

በሁለቱ ሀገራት ግዛት ይገባኛል የተነሳባቸውን ሁለት የቀይ ባህር ደሴቶችን ለሳዑዲ ለመስጠት አልሲሲ ከዚህ ቀደም ወስነው የነበረ ቢሆንም ባልተጠበቀ ሁኔታ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ በውሳኔያቸው እንዳይገፉበት አድርጓቸዋል። ከሳዑዲ አረቢያ ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ ጉብኝት በኋላ ግን የሁለቱ ሀገራት የደሴቶቹ ይገባኛል ጥያቄ መልሶ ወደ መድረክ መጥቷል። ጉዳዩም ከአልሲሲ ካቢኔ፣እስከ ፓርላማው ብሎም እስከ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ድረስ ዋነኛ አጀንዳ ሆኗል።

Related stories   “ጣልያኖችም ሆኑ እንግሊዞች ቅኝ ግዛትን ለማስቀጠል ህዝቡን በዘር መከፋፈልን እንደ አንድ ስልት ይጠቀሙ ነበር” -አቶ ታቦር ገረሱ ዱኪ

Sendekenews paper.

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *