የኔልሶን ማንደላን ለቅሶና ቀብር ሳይ በጣም ተገረምሁ ብቻ ሳይሆን እፍሪቃዊ መሆኑ ራሱ አኰራኝ። ከዚህም ተነሥቼ፣ታሪክን ወደኋላ መለስ ብዬ በኅሊናዬ መስተዋት ቃኝቼ ሳበቃ፣ ጊዜው እንደዛሬ ሁኖ ቢያመችለት ኖሮ፣ እንደሳቸው ሊለቀስለት የሚገባ ሰው በአፍሪቃ ምድር ከዚህ በፊት ታይቶ አይታወቅም ብዬ ራሴን በራሴ ደጋግሜ ጠየቅሁ።ኔልሰን ማንዴላ የሚደነቁት፣ በቀለሙ በመጀነንና፥ በዘመናዊ መሣርያው በመተማመን፣ በበላይነት ረግጬው ልግዛው ብሎ፣ ለብዙ ዘመናት በሥልጣን ላይ ሁኖ ያሠቃይ የነበረውን ጨቋኙን የነጮች ግዛት ከነሥርዐቱ አሸንፈው፣ ለሀገራቸው ጥቊር ሕዝብ የድል ዋንጫ አጐናፅፈው፣ ነፃነቱንና ክብሩን ስለመለሱለት ነው። ግፈኞቹን የድሮ ጠላቶቻቸውንም እንደመበቀል ፈንታ በፍቅር ያዟቸው። ሁሉም የደቡብ አፍሪቃ ዜጋ በጐሣና በዘር፤ በሃይማኖትና በቀለም ሳይለያይና ሳይከፋፈል፣ ታዲያ በመቻቻል፣ ባንድነትና በፍቅር ተቀራርቦ እንዳንድ ሀገር ሕዝብ እንዲኖር አደረጉ። ለኻያ ሰባት ዓመታት በእስራት ራሳቸውን በመሠዋት፣ ጠላታቸውን በማሸነፍ፣ ራሳቸውንና ሀገራቸውን ያኰሩ ደግና ብልህ መሪ፣ ሰውን በማንነቱና በእምነቱ ሳይሆን በሙያውና በችሎታው የሚፈርጁ፤ ጠላትን እንኳ የሚራሩና የሚወዱ ሰው ነበሩ። ይኸንን በዐይነ ኅሊናዬ መላልሼ ካሰላሰልሁ በኋላ፣ የዓለምን ታሪክ ደግሞ ቃኝቼ ሳበቃ አንድ እጅግ በጣም ታላቅ ሰው አገኘሁ። አፄ ምኒልክ።menilek-ii-great

Related stories   “ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

(ባለ 51 ገጽ ሰፊ ትንታኔ) – RE-PUBLISHED Amharic Article By Haile Larebo

debirhan.com

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *