የጋምቤላ ክልል አስገራሚ ዜና አሰምቷል። በክልሉ የትምሀርት ቢሮ ሃላፊውን ጨምሮ ዘጠኝ ክፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የተጭበረበረ የትምህርት ማስርጃ እንዳለባቸው የመንግስት ሚዲያዎች ይፋ አድርገዋል። የትምህርት ሚኒስቴርና የክልሉ የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን በትብብር የማጣራቱን ስራ እንደሰሩ ነው የተገለጸው። ውሳኔው የጥልቅ ተሃድሶው ውጤት ነው ተብሏል። በፌደራል ደረጃ ያሉ ባለስልጣናት መካከል ከህንድና ከተለያዩ ” የትምህርት ተቋማት” በውክልና ጭምር ዲግሪ የሰበሰቡትን ጥልቁ ተሃድሶ ይፈትሻቸው ይሆን? ፋና የሚከተለውን ዘግቧል።
የጋምቤላ ክልል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተገኘባቸው 9 የክልሉ ስራ አስፈፃሚዎችን ከኃላፊነት አባረረ። የኮሚሽኑ ኃላፊ ኮሚሽነር ኡሞድ ኡጁሉ፥ የጋምቤላ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ባካሄደው የጥልቅ ተሃድሶ መድረክ በክልሉ ብቁ አመራሮችን ለመለየት እንዲቻል ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የተወሰደ እርምጃ ነው።

ኮሚሽኑ ይህን ተከትሎ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ባካሄደው የማጣራት ስራ ከ201 የክልሉ ከፍተኛ ስራ አስፈፃሚዎች ዘጠኙ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ይዘው ተገኝተዋል። በመሆኑም ኮሚሽኑ እነዚህ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ይዘው የተገኙ ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች የትምህርትቢሮ ኃላፊውን ጨምሮ ከስራቸው እንዲባረሩ መደርጉን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

በዚህም መሰረት በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ከኃላፊነታቸው የተነሱት የክልሉ የስራ ኃላፊዎች

1. ኚሙሉ ኦጋኒ፦ የክልሉ ዋና ኦዲት መስሪያ ቤቱ ምክትል ኦዲተር

2. ጋትዊች ዋር፦ የክልሉ የኮንስትራክስን ቢሮ ኃላፊ

3. ፖል ጆክ፦ የክልሉ መገናኛ ብዙኃን መረጃ ነፃነት ኤጀንሲ ዳይሬክተር

4. ሳይመን ጋትልዋክ፦ የክልሉ መስተዳደር የአስተዳደርና ማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ

5. ቱት ጆክ፦ የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

6. ቾል ኮር፦ የክልሉ መስተዳደር ምክር ቤት የመሰረተ ልማት አማካሪ

7. ሜሪ ኛንዌር ዶክ፦ በጤናና ጤና ነክ ሴቶች ኤጄንሲ የሴቶች ዩኒት አስተባባሪ

8. ኙዌች ጋችሉል፦ የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት የሴቶች ዩኒት ኃላፊ

9. ኛዬር ሉልዴንግ፦ በክልሉ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የመንገድ ዩኒት አስተባባሪ ናቸው።

በዚህ የወንጀል ድርጊት የተሳተፉት ግለሰቦች ወደፊት በህግ እንደሚጠየቁ የጋምቤላ ክልል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽነሩ አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ተናግረዋል። በቀጣይም ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ የስራ አስፈፃሚዎች እና ባለሙያዎች ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል። እስከአሁንም የ328 ግለሰቦች የትምህርት ማስረጃ ማጣሪያ እየተደረገ መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

ምንጭ፦ ኢቢሲ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *